Tender Detail

Tender Details

  • Deadline14 Dec 2023, 3:58 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Accounting & Auditing

የጨረታ ማስታወቂያ በጉምሩክ ኮሚሽን የሀዋሳ ቅ/ጽ/ቤት የተተውና የተወረሱ ዕቃዎች ሽያጭ የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 25/2016


የሐዋሳ ጉምሩክ ኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤት በሐዋሳ ማዕከላዊ መጋዘን የተተወና ተወርሰው የሚገገኙ የመገናኛ መሳሪያዎች የኤሌክትሪክ እቃዎች፣ የመዋቢያና የንጽህና መጠበቂያ እቃዎች፣ አልባሳት የሞተር ሳይክል መለዋወጫዋች እና ደረቅ ጫት ባሉበት ሁኔታ በግልጽና በሃራጅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

በመሆኑም በጨረታው መወዳደር ይሚፈጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሞላት ይኖርባቸዋል።

  1.  የግልጽ ጨረታ ተሳታፊ ተጫራቾች በዘርፉ የታደስ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (TIN) እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ ስለመሆኑ ከግብር ሰብሳቢ መ/ቤት የተሰጠ ማስረጃ ማቅርብ የሚችሉ። ግምታዊ ዋጋው ከብር 500 ሺህ በታች የሆነውን ማንኛውንም እቃ ለመግዛት የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተኬት ማቅረብ አያስፈልግም።
  2. የደረቀ ተጫራቾች በዘርፉ የላኪነት ፈቅድ ማቅርብ ይኖርባቸዋል።
  3. ማንኛውም ተጫራች የጨረታውን ሰነድ በጨረታ ማስታወቂያው ላይ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ ጠዋት ከ2፡00 እስከ 6፡00፣ ከሰዓት ከ7፡00 እስከ 11፡00 ሰዓት፣ ቅዳሜ ከ2፡00 እስከ 6፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ/ በመክፈል በቅ/ጽ/ቤቲ ከገቢ ሂሳብና ዋስትና አስተዳደር ቡድን መውሰድ ይችላሉ።
  4. ማንኛውም የግልጽ ጨረታ ተጫራች ለጨረታው ማስከበሪያ የሚሆን የሚጫረትበትን ጠቅላላ ዋጋ 5% (አምስት በመቶ) በኢትዮጲያ ንግድ በንክ የተመሰከረለትን (CPO)፣ የጨረታ ሰነድ እና አጠቃላይ መረጃዎችን ጨረታው ከመከፈቱ በፊት በጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርበታል።
  5. ለደረቅ ጫት እና የመዋቢያና የንጽህና መጠበቂያ እቃዎች ሃራጅ ጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን ለእያንዳንዱ ኮድ ብር 100,000( አንድ መቶ ሺ ብር ) እንዲሁም ለኤሌክትሪክ እቃዎች ሃራጅ ጨረታ ለኮዱ 50,000 /ሃምሳ ሺህ/ ብር በኢዩጲያ ንግድ ባንክ የተመሰከረለትን (CPO) ማቅረብ ይኖርበታል።
  6. ተጫራቾች ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የጨረታ ሰነዱን በመግዛት እስከ 5ኛው /አምስተኛው/ ቀን ድረስ የንብረቶቹን ናሙና በመደበኛ የስራ ሰዓት በሀዋሳ ማዕከላዊ መጋዘን ማየት የሚቻሉ ሲሆን ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን በ6ኛው /ስድስተኛው/ ቀን የግልጽ ጨረታ ጠዋት 4፡00 ሰዓት የጨረታ ሳጥኑ ታሽጎ በ4፡05 ሰዓት አዲሱ መጋዘን ይካሄዳል። የሃራጅ ጨረታ የግልጽ ጨረታ ከተጠናቀቀ ከ10 ደቂቃ በኃላ ይካሄዳል።
  7. ነገር ግን ጨረታው በበዓል/እሁድ/ቀን የሚውል ከሆነ ጨረታው የሚካሄደው በተመሳሳይ ሰዓት የሚቀጠለው የስራ ቀናት ይሆናል።
  8. ማንኛውም የግልጽ ጨረታ ተጫራቾች የሚወዳደሩባቸውን እቃዎች ዋጋ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ተያይዞ በቀረበው ቅጽ ላይ ተጫራቹ ያቀረበው ዋጋ በሚለው ርእስ ስር በተሰጠው ክፍት ቦት ከነቫት በሚለው መስምር በጨረታ ሰነዱ ግልጽ በሆነ መልክ በመሙላት በታሸገ ኤንቨሎፕ ወይም ፓስታ ማቅረብ አለባቸው ከዚህ ሰነድ ውጭ በሌላ ሰነድ ተሞልቶ የሚቀርብን ዋጋ ቅ/ጽ/ቤቱ ለመቀበል አይገደድም ።
  9. ማንኛውም የግልጽ ጨረታ ተጫራች ጨረታው ከተከፈተ በኃላ በጨረታ ሰነድ ላይ የሰጠውን ዋጋና መግለጫ መለወጥ እና ማሻሻል አይችልም።
  10. ማንኛውም ተጫራች የሰጠው የመወዳደሪያ ዋጋ የጨረታው ሂደት ተጠናቆ ቅ/ጽ ቤቱ የጨረታውን ውጤት እስከሚያሳውቅ ድረስ ጸንቶ ይቆያል።
  11. ማንኛውም ተጫራች ጨረታው ከተከፈተ በኃላ ራሱን ከጨረታ ውድድር ማግለል አይችልም።
  12. በጨረታው ለተሸነፉ ተጫራቾች ያስያዙት CPO በሶስት የስራ ቀናት ውስጥ የሚመለስላቸው ሲሆን አሸናፊው ያስያዘው ዋስትና ኝ ከሽያጭ ጋር የሚታሰብለት ይሆናል።
  13. ተጫራቾች እቃውን ሳያዩ ዋጋ ሲሰጡና ችግር ቢፈጠር ቅ/ጽ/ቤቱ ተጠያቂ አይሆንም።
  14. ለጨረታው የቀረበው እቃ ሽያጭ የሚፈጸመው ባለበት ሁኔታ ነው።
  15. አሸናፊ ተጫራቾች ማሸነፋቸው በውስጥ ማስታወቂያ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ በ5/አምስት/ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ገንዘብ ገቢ በማድረግ እቃዎችን ማንሳት ይኖርባቸዋል። ይህንን ባያደርጉ ጨረታው ተሰርዞ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለቅ/ጽ/ቤቱ ገቢ ተደርጎ እቃው በድጋሚ በጨረታ ላይ ይወጣል።
  16. ቅ/ጽ/ቤቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለበለጠ መረጃ የስልክ ቁጥር፦ 046 212 53 96

በጉምሩክ ኮሚሽን የሀዋሳ ቅ/ጽ/ቤት 

Save Tender