የጨረታ ማስታወቂያ የጨረታ ቁጥር 006/2016
ሎሜ አዳማ የገበሬዎች ሕብረት ስራ ዩኒዬን በምስራቅ ሽዋ ዞን ሞጆ ከተማ አካባባ የዘመናዊ የዶሮ ማርቢያ፣ ማሳደጊያ የሚሆን አንድ ሼድ፤ ማስፈልፈያ /ሃቸሪ/ የሚውል አንድ ሼድ እና ለቢሮ አገልግሎት የሚውል 3 ክፍል ያለው አንድ አነስተኛ ብሎክ እና የመጸዳጃ ቤት ማሠራት ይፈልጋል።
ስለሆነም ከዚህ ቀጥሎ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሞሉ ተጫቾች መወዳደር ይችላሉ።
- የግንባታ ተጫራቾች ደረጃ 7 እና ከዚያ በላይ የሆኑ ጠቅላላ ወይም የህንጸ ተቆራጭ ሆነው፡ የታደሰ የንግድ ፈቃድ የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆኑን የሚያረጋግጥ ሠነድ ማቅረብ የሚችሉ፣ በሰሩዋቸው ፕሮጅክቶች በጥራ እና በተባለው ጊዜ ስለመጨረሳቸው ማስርጃ የሚያቀርቡ መሆን አለባቸው።
- እያንዳንዱ ተቆራጭ መወዳደር የሚችለው በ2015 ዓ/ም ሥራ የስራና በእጅ ላይ ካለመ ከእቃ መጨመር ጋር ተያይዞ ያለ ውዝግብ እየሰራ ያለና ከ75 ፐርሰንት በላይ መድረሱን ማረጋገጫ ሲያቀርቡ ይሆናል።
- ተጫራቾች የጨረታ ሠነዱን ለመግዛት ሲመጡ፡ ተጨማሪ እሴት ታክስ ሠርተፊኬት እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ሠርተፊኬት፣ የንግደ ፍቃድ የንገድ ምዝገባ የኮንስትራክሽን ብቃት ማረጋገጫ ዋናውን ይዘው መቅርብ ይኖርባቸዋል
- የጨረታ ማስከበሪያ ብር 100.00 /አንድ መቶ ሺህ ብር/ በባንክ የተመሠከረለት ሠርተፊኬት (CPO) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ጋራንቲ ወይም በጥሬ ገንዘብ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- የጨረታ ማስከበሪያ ጊዜ ጨረታው ከተከፈተበት ቀን አንስቶ ለ90/ዘጠና ቀናት ይሆናል።
- ተጫራቾች ሌሎች ተጫራቾች ባቀረቡት ዋጋ ላይ ተንተርሰው ዋጋ ማቅርብ አይችሉም።
- ተጫራቾች የቴክኒክና የፋይናንስ ዶክመንቶችን ኮፒ እና ኦርጅናል በማለት ለየብቻ ላይተው በሰም በታሽገ ኤንቨሎፕ ጠቅልለው ሁሉንም ደግሞ በእናት ፓስታ በማሸግ ማቅረብ አለባቸው።
- የጨርታ መክፈቻ ጊዜ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ ቀናቶች ሲሆን የመክፈቻው ቀን በዓል ከሆን በሚቀጥለው የስራ ቀን በ4፡00 ሰዓት ላይ ታሽጎ በ4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በሎሜ አዳማ ይገበሪዎች ህብረት ስራ ዩኒዬን መሰብሰቢያ አዳራሽ የሚከፈት ይሆናል።
- ተጫራቾች የጨረታ ሠነዱን ኦሮሚያ ክልል ሞጆ ከተማ ሉሜ አዳማ የገበሬዎች ህብረት ስራ ዩኒየን ጽ/ቤት ድረስ በመገኘት ብር 400 /አራት መቶ ብር/ በመክፈል መግዛት የሚችሊ ይሆናል።
- ተጫራቾች የገዙትን ሰነድ ሞልተው ማስገባት ያለባቸው ሁሉም ሞጆ በሚገኘው የሉሜ አዳማ ገበሬዎች ህብረት ስራ ዩኒዬን ባስቀመጠው የዩኒዬኑ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ነው።
- በጨረታው የሚሳተፉ ሑሉ የሚያቀርቡበት ሰነድ በደንብ የሚነበብ፣ ስርዝ ድልዝ የሌለው ሌሎች ዋና ያልሆኑ ነገሮች ያልተካተቱበት መሆን አለበት
- አሸናፊዎች ማሸናፍቸው ሲረጋገጥ አንዋል ተርን ኦቭር፣ የሰራተኞች ግብርና ጡረታ መከፈሉን ስልጣን ካለው መስሪያ ቤት በደብዳቤ ያወጣሉ አሰሪው መስራያቤት ማጣራት ያደርጋል።
- ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 0935993526/0911970983/0911399595 በመደወል ማግኘት ይችላሉ።
- መስሪያ ቤቱ/ዩኒዬኑ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ሉሜ አዳማ የገበሬዎች ሕብረት ስራ ዩኒዬን
