የተተው እቃዎች ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር ግ22/2016
በኢትዮጲያ ጉምሩክ ኮሚሽን የሞጆ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት አስመጪዎች በጉምሩክ አዋጅ ቁጥር 859/2006 እና በተሻሻለው የጉምሩክ አዋጅ ቁጥር 1160/2011 መሰረት የተተው ወይም ይተወሩሱ እቃዎችን በእቃ አወጋገድ መመሪያ ቁጥር 167/2012 መሠረት የተተው ንብረቶችን ማለትም ጎማ ከነከመነዳሪ(TRANGLE BAND TYER WITH TUBE TR691)S 12.00R20PR ፤ሴራሚክ ፤ ELECTRICAL MOTOR GROUND BUMPER WITH FLOOR 230W& OHERES ፣ የግንባታ እቃ (FIRE DUMPER & ALUMINUM AIR MASTER) COLD ROOM REFRIGERATION UNIT ፣ ካርቶን ፣ STAINLES STEEL HOUSING FOR DYEING MACHINE እቃዎች በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል ። በዚህም መሠረት ጨረታውን በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለመጫረት የሚፈልጉና ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሞሉ የጫራቾች በጨረታው መሳተፍ የሚችሉ መሆኑን እንገልጻለን።
- ተጫራቾች የእቃዎቹን ዝርዝር፣ ዓይነት ፣ብዛት የጨረታ ሠነድ እና መመሪያ መግልጫ እንዲሁም የጨረታ ዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ ዘወትር ከሰኞ እስከ ሐሙስ ከጠዋቱ 2፡00 እስከ ቀኑ 6፡00 ከሰዓት በኃላ ከቀኑ 7፡00 እስከ ቀኑ 10፡30 እና ዓርብ ከጠዋቱ 2፡00 እስከ ቀኑ 5፡00 ከሰዓት በኃላ ከቀኑ 7፡30 እስከ ቀኑ 10፡30 እንዲሁም ቅዳሜ ከጠዋቱ 2፡00 እስከ ቀኑ 5፡30 የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል ከቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ገሚ ሂሳቦች ቡድን መውሰድ ይችላሉ።
- ተጫራቾች በጨረታ ከሚሸጠው እቃ ጋር በዘርፉ የጸና ንግድ ፈቃድ ያላቸው ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት እና የዘመኑን ግብር የከፈለ ለመሆኑ ከግብር ሰብሳቢ መ/ቤት የተሰጠ ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው። ሆኖም ግምታዊ ዋጋቸው ከብር 500,000.00 በታች የሆኑ ማንኛውንም እቃ ለመግዛት የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሠርተፍኬት ማቅረብ ሳያስፈልግ መወዳደር ይችላሉ።
- ማንኛውም ተጫራች ለጨረታው ማስከበሪያ የሚሆን የሚጫረትበትን ጠቅላላ ዋጋ 5% ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ cpo ጨረታ ከመከፈቱ በፊት በቅድሚያ ማስያዝ ይኖርበታል። ተጫራቾች የሚያስይዙት cpo በቅርንጫፍ ጽ/ቤት ሰም ETHOPIAN CUSTOMS COMMISSION MODJO BRANC OFFICE በሚል ሲሆን በኢትዮጲያ ንግድ ባንክ ከአዲስ አበባ፤ አዳማ እና ሞጆ ቅርነጫፎች መዘጋጀት አለበት። ተሳታፊዎች ዋጋ መሙላት የሚቹሉት ከቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ተዘጋጅቶ ማህተም ያረፈበት ሠንድ ላይ ብቻ መሆን የኖርበታል።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ በመግዛት የሚወዳደሩበትን እቃ አስቀድሞ ማየት ያለባቸው ሲሆን እቃውን ሳያዩ ለሚሞሉት ዋጋ ቅ/ጽ/ቤቱ ኃላፊነቱን አይወስድም በጨረታ ተሽጦ የተወሰደ እቃ ተመላሽ አይደረግም፤ ለእቃውም የተከፈለ ገንዘብ አይመለስም።
- የግልጽ ጨረታ ተሳታፊ ተጫራቾች እያንዳንዱን እቃዎች ለመግዛት የሚያቀርቡት የመጫረቻ ዋጋ የሞሉበት ሠነድ በተራ ቁጥር 2 የተገለጽትን ማስረጃዎች ኮፒ እና የቀረቡት የመጫረቻ ዋጋ 5% ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ cpo በኤንቨሎፕ ወይም በፖስታ በማሽግ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ8 ተከታታይ ቀናት እስከ የመጨረሻው ቀን ጠዋት 4፡45 ድረስ በቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይችላል። የጨረታ ሳጥኑ ከታሸግ በኃላ የሚመጡ የመጫረቻ ሰነዶች ተቀባየነት አይኖራቸውም።
- የጨረታ ማስታወቂያ በአዲ ዘመን ጋዜጣ ላይ የወጣበትን ቀንን ጨምሮ በ18ኛው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 4፡45 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ እለት ጠዋት 5፡00 ላይ ተጫራቾች ወይንም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ለጨረታ ባዘጋጀው ቢሮ ውስጥ ይከፈታል።
- ማንኛውም በግልጽ ጨረታ የሚሳተፍ ተጫራች ጨረታው ከተከፈተ በኃላ ዋጋ መቀየር ወይንም የሌላ ተጫራቾችን ዋጋ ተንተርሶ ዋጋ አሻሽሎ ማቅረብ አይችልም በጨረታ ሽያጭ ውድድር ላይ የእቃው አስመጪ ወይም ባለቤት እና ቤተሰብ የነበሩ ሰዎች በጨረታው መሳተፍ አይችሉም፤ ጨረታው ከተከፈተ በኃላ እራሱን ከጨረታ ውድድር ማግለል አይቻልም እና የሰጠው የመወዳደሪያ ዋጋ የጨረታው ግምገማ ተጠናቆ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ የጨረታዊን ውጤት እስከሚያሳውቅ ድረስጸንቶ ይቆያል።
- የግልጽ ጨረታው አሸናፊ ጨረታውን ስለማሸነፋቸው ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ በ5 /አምስት/ቀናት ውስጥ ያሸነፉትን እቃ ዋጋ ገቢ መማድረግ እቃውን መረከብ አለበት በ5/አምስት/ቀናት ውስጥ ገንዘቡ ገቢ ካልተደረገ ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ cpo ያስያዙት ገንዘብ ለመንግሥት ገቢ ይደረጋል።
- በተራ ቁጥር 8 በተቀመጠው ጊዜ ውስጥ ያሸነፉበትን እቃ ዋጋ ገቢ አድርጎ እቃውን ያላነሳ /ያልተረከበ / እንደሆነ ለሚቆይበት በተጨማሪ ጊዜ የመጋዘን ኪራይ ይከፍላል። ሆኖም እቃው በ2/ሁለት/ ወራት ውስጥ ካልወጣ እንደተተው ተቆጥሮ በጨረታ ሸያጭ ይወገዳል።
- አሸናፊው ተጫራች እቃዎችን ለመርከብና ለማጎጎዝ የሚያስፈልጉ ወጪዎች ሁሉ ራሱ ይሸፍናል
- ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ለጨረታ ያቀረበውን እቃ ብዛት ለመጨመርም ሆነ ለመቀነስ ሙሉ መብት አለው። በጨረታ ተሽጦ በጨረታ አሽናፊው የተወሰደ እቃ አይመለስም።
- ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ እቃዎቹን ለመሸጥ የተሻለ አማራጭ ወይም ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰርዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ለተጨማሪ ማብራሪያ በሥልክ ቁጥር 022-236-90-94 ላይ ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
በገቢዎች ሚኒስቴር ጉምሩክ ኮሚሽን የሞጆ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት
