Tender Detail

Tender Details

  • Deadline22 Dec 2023, 4:23 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Accounting & Auditing

የጨረታ ማስታወቂያ የጨረታ ቁጥር፡ SSNT-T429


የኢትዮጲያ አየር መንገድ የተለያዩ የአበባ ዲኮር አገልግሎት ሰጪ ድርጅቶችን በጨረታ አወዳድሮ ለሁለት ዓመት በኮንትራት በስምምነት ማሰራት ይፈልጋል። ስለሆነም ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ማስረጃዎች /ሰነዶች ማሞላት ይኖርባቸዋል።

  1. በአበባ ዲኮር ለ5 ዓመት እና ከዛ በላይ የስራ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያለው የንግድ ሚኒስቴር የምዝገባ ወረቀት ያለው የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆነ እና የዘመኑን ግብር የከፈለ ተጫራች በጨረታው መሳተፍ ይችላል።
  2. የጨረታ ማስከበሪያ ብር 10,000 /አስር ሺ ብረ/ በባንክ የተረጋገጠ ቼክ /ሲፒኦ/ በባንክ ጋራንቲ ማስያዝ ይኖርባቸዋል። አሸናፊው ከተለየ በኃላ በጨረታው ለተሸነፉት ተጫራቾች ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪይ ወዲያውኑ የመላሽ ይሆናል 
  3. ተጫራቾች ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ታህሳስ 22 ቀን 2016 ዓ/ም በአቅራቢያቸው ከሚገኝ የኢትዩጲያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ የማይመለስ 100.00/አንድ መቶ ብር/ በመክፈል በሂሳብ ቁጥር 10006958277 (E-99) ለኢትዩጲያ አየር መንገድ ጨረታ ቁጥር (SSNT-T429) በሚል ገቢ ማድረግ ይኖርባቸዋል። ተጫራቾች የከፈሉበትን የገቢ ደረሰኝ (Deposit slip) ስካን በማድረግ ከታች በተጠቀሰው የኢ ሜይል አድራሻ በመላክ የጨረታ ሰነዱን በኢሜል ያገኛሉ።
  4. ተጫራቾች በጨረታው ደንብ መሠረት የመጫረቻ ሠነዳቸውን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ለኢትዮጲያ አየር መንገድ ስትራቴጂክ ሶርሲንግ ነን ቴክኒካል ክፍል እስከ ታህሳስ 22 ቀን 2016 ዓ/ም ከቀኑ 5፡00 ሰዓት ድረስ ማቅረብ አለባቸው። ጨረታው ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኑበት በተመሳሳይ ቀን 9፡30 ሰዓት የኢትዮጲያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና መሥሪያ ቤት በበረራ ኦፕሪሽን ህንጻ አጠገብ በሚገኘው በጨረታ መክፈቻ አዳራሽ ውስጥ ይከፈታል።

ለተጨማሪ ማብራሪያ ፡የኢትዮጲያ አየር መንገድ 

ቦሌ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ 

ስትራቴጂክ ሶርሲንግ ነን ቴክኒካል ክፍል 

በስልክ ቁጥር 0115178025 በመደወል መጠየቅ ይቻላል።

ኢሜል HELENN@ethiopianairlines.com 

አየር መንገዱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

Save Tender