የጨረታ ማስታወቂያ
በኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ የኢትዮጲያ ፕላስቲክ ኢንዱስትሪ የስራተኛ ጫማዎችን እና አልባሳት በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፣ በመሆኑም ተጫራቾች፡
- በኢንዱስትሪው ሰፕላይ ቼን ማኔጅመንት ቡድን ቢሮ በመምጣት ዝረዝር መረጃ የተጫራቾችን መመሪያ እና የዕቃዎችን ዓይነትና መጠን የያዘ ለእያንዳንዱ ሎት ሰነድ የሚመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) ከፍለው መውሰድ ይችላሉ።
- በዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ ላይ ተጫራቹ የዕቃው ዋጋ በሚለው አምድ ስር የሚሸጡበትን የነጠላ ዋጋ በአሃዝ ያለስርዝ ድልዝ ገልጸው በታሸግ ኢቨሎፕ የኢንዱስትሪው ሰፕላይ ቼን ማኔጅመንት ቡድን ቢሮ በተዘጋጅው የጨረታ ሳጥን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ቀናት ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
- ጠጫራቹ የዕቃዎችን የተናጥል ዋ ማቅረብ ይኖርበታል።
- ትክክለኛ የተጫራች ስምና አድራሻ በታሸገው ኢንቨሎፕ እና በመጫረቻ ሰነድ ላይ መግለጽ ይኖርበታል።
- ተጫራቾች የእቃዎቹን ለተቀመጠው የነጠላ ዋጋ ድምር የጨረታ መነሻ ዋጋ 2 በመቶ (2%) የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ (GPO) ከጨረታ ሰነዱ ጋር በማያያዝ ሳጥኑ ውስጥ ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- የጨረታ ሳጥኑ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15ኛው ቀን ጠዋት በ4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዛው ዕለት 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኢንዲስትሪው መሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል።ሆኖም ተጫራቹ በራሱ ምርጫ ጨረታው በሚከፈትበት ጊዜ ሳይገኝ ቢቀር የጨረታውን መከፈት አያስተጎግለውም።
- ተጫራቾች የጨረታውን ውጤት በኢንዲስትሪው ማስታወቂያ ላይ ከወጣ ቀን ጀምሮ ቅሬታ ካላቸው በ5 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ብጽሁፍ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥራችን 0116670485/011852286 ደውሎ መጠየቅ ይችላሉ።
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነድ ላይ በየገጽ ስምና ፊርማ ማስገባት አለባቸው
- ተጫራቾች የቫት ሠርተፍኬት የዘመኑን የታደሰ የንግድ ፈቃድ እና የግብር ከፋይ ሠርተፍኬት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ኢንዱስትሪው የተሻል መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻችን በመገናኝ ወደ ገርጁ በሚወስደው መንገድ ከአምጬ ዝቅ ብሎ ኒያላ ሞተርስ ፊት
ለፊት ስልክ ቁጥር 0116670485
ኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ የኢትዮጲያ ፕላሰቲክ ኢንዱስትሪ
አዲስ አበባ
