Tender Detail

Tender Details

  • Deadline10 Dec 2023, 12:12 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Accounting & Auditing

የጨረታ ማስታወቂያ የጨረታ ቁጥር DCE/SF/168/2023


የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ለቆሬ ኮሌጅ ግንባታ ፕሮጅክት አገልግሎት የሚውል supplyand fix Aluminum work for sky Lighy; Entrance canopy sun Breaker Aluminum cladding; Aluminum Louver;Aluminum pergola Aluminum panel partition wall; Aluminum composite panel Doors Aluminum curtain wall Aluminum coposite wall claddinf Aluminum cut out pattern ግዥ ለመፈጸም ተጫራቾችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

ተ.ቁ  የዕቃው ዓይነት   የፕሮጀክት ስም   የጨረታ ቁጥር  የጨረታ መዘጊያ ቀን እና ሰዓት  የጨረታ መክፈቻ ቀን እና ሰዓት  የጨረታ ማስከበሪያ 
1 Supply and Fix Aluminum Work  ቆሬ ዋር ኮሌጅ ፕሮጀክት  DCE/SF/168/2023 ጥር 02/2016 ዓ/ም 4፡00 ሰዓት  ጥር 02/2016 ዓ/ም 4፡15 ሰዓት   100,000።00

ስለሆነም፡

  1. ተጫራቾች በዘርፍ የተሰማሩ መሆኑን የሚገልጽ የታደስ የንግድ ፈቃድ ፤ የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቅት፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉበት ማስረጃ፣ ለተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡበትን የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣ በጨረታ ለመሳተፍ የሚሰጥ የታደሰ የምስክር ወረቀት (ታክስ ክሊራንስ) እና የአገር ውስጥ ተጫራቾች በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ መሆኑን የሚያረጋግጥ ኮፒ ወዘት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
  2. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር 100,000.00(አንድ መቶ ሺህ ብር) በባንክ የተረጋገጠ (CPO) ወይም ከታወቀ ባንክ በሁኔታ ላየ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና (Unconditional Bank Gurantee) ለ120 (ለመቶ አያ) Calendar days ጸንቶ የሚቆይ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  3. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር ለያንዳንዱ ጨረታ ቁጥር 200 00/ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ዘወትር ብሥራ ሠዓት ወሎ ሠፈር አካባቢ በሚገኘው የመከላከያ ኮንስትራክሽን ዋና መ/ቤት የግዢና አቅርቦት አስተዳደር መምሪያ ቢሮ መግዛት ይችላሉ።
  4. ተጫራቾች የሚወዳደሩባቸውን ዕቃዎች ናሙና ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  5. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ በጨረታሰነድ በተያያዘ ዝርዝር እና ብዛት መሠረት መሆን ይኖርበታል።
  6. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የጨረታ ቴክኒካል ሰነድ እና ዋጋ በታሸገ ኤንቨሎፕ ከላይ በሰንጠረዡ  በተገለጸው ቀንና ሰዓት በኢንተርፕራይዙ የግዥና አቅርቦት አስተዳደር መምሪያ ቢሮ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  7. ጨረታው በሰንጠርዡ በተገለጸው መሠረት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል።
  8. ኢንተርፕራይዙ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ፡

የቀጥታ ስልክ ቁጥር 0114-40-34-34 ማዞሪያ 0114-42-22-70/71/72

E-mail & info@dce-et-.com የድረ ገጽ አድራሻ www dce-et.com

ፓ ሳ ቁ 3414 ፋክስ ቁ 0114-40- 04-71/0114-42-07-46 

ወሎ ሰፈር የቀድሞው ኖሬላ ግቢ

የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ 

 

Save Tender