የጨረታ ማስታወቂያ የጨረታ ቁጥር DCE/TR/179/2023
የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ለዋና መ/ቤት እና አዲስ አበባ ዙሪያ ለሚገኙ ፕሮጅክቶች የመጫንና የማራገፍ ሥራ አገልግሎት የሚሰጥ ከ10-50 ክብደት ማንሳት የሚችል ፎርክ ሊፍት ግዥ ለመፈጸም ተጫራቾችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
| ተ ቁ | የማሽኑ አይነት | የፕሮጀክት ስም | የጨርት ቁጥር | የጨረታ መዝጊያ ቀን እና ሰዓት | የጨረታ መክፈቻ ቀን እና ሰዓት | የጨረታ ማስከበሪያ |
| 1 | ከ10-50 ክብደት ማንሳት የሚችል ፎርክ ሊፍት | ለዋና መ/ቤት እና አዲስ አበባ ዙሪያ ለሚገኙ ፕሮጅክቶቸ | DCE/TR/17/2023 | ታህሳስ 25/2016 ዓ/ም 4፡00 ሰዓት | ታህሳስ 25/2016 ዓ/ም 4፡15 ሰዓት | 20,000.00 |
ስለሆነም፡
- ተጫራቾች አገባብነት ያለው የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ ወረቀት የአቅራቢዎች ምዝገባ ምስክር ወረቀት የአቅራቢዎች ምዝገባ ሰርተፊኬት ተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT)፣ የታደሰ ታክስ ክሊራንስ እና የግብር መለያ ቁጥር (TIN) የብቃት ማረጋገጫ ፍቃድ እንዲሁም የጨረታ ማስከበሪያ ቢድ ቦንድ በድርጅታችን ትክክለኛ ስም(Defense Construction Enterprise) ስም የተዘጋጀና የመሳሰሉ ማስረጃዎችን ወዘተ የያዘ ይሆናል።
- ተጫራቾች ለሚጫረቱበት ፎርክ ሊፍት የባለቤትነት ማረጋገጫ ሊብሬ ወይም ሠነዶች ማረጋገጫ ምዝገባ ኤጀንሲ የተረጋገጠ የባሊቤትነት ማረጋገጫ ሰነድ ህጋዊ ውክልና እንዲሁም ማሽኑ ለማከራየት ከሚመለከተው መንግስታው አካል የተሰጠ ማረጋገጫ ፈቃድ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- እያንዳንዱ ተጫራች የጨረታ ማሰከበሪያው እንደ ተጫራቹ ምርጫ በቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ በባንክ ዋስትና (Unconditional Bank Guarantee) ወይም በባንክ የተሰጠ የተረጋገጠ ቼክ (CPO) ብር 20,000.00(ሃያ ሺህ ብር) ማስያዝ አለበት። የመንገድ ድርጅቶች ዋስትና ተቀባይነት አይኖረውም። ዋስትናው ጸንቶ የሚቆይው ለ120 ቀናት መሆን ይኖርበታል። እንዲሁም የመደን ድርጅቶች ቢቀርብ የማንቀበል መሆኑ ከወዲሁ እናሳስባለን።
- ተጫራቾች የሚያቀርቡበትን ዋጋ በጨረታ ሠነዱ በተጠቀሰው ብዛት እና ዝርዝር መሠረት መሆን ይኖርበታል።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ዘወትር በሥራ ሰዓት ወሎ ሠፈር አካባቢ በሚገኘው የመከላከያ ኮንስትራክሽን ዋና መ/ቤት ግዥና አቅርቦት አስተዳደር መምሪያ ቢሮ መግዛት ይችላል።
- ጨረታው በሰንጠርዡ በተገለጸ መሠረት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ መሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል።
- አከራይ የነዳጅ ወጪ በራሱ የሚሸፍን ሲሆን ፎርክ ሊፍቱን ከነሹፎሩ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስከፍሉትን የቀን ዋጋ ለይተው ማቅረብ አለባቸው።
- ኢንተርፕራይዙ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡ ውሎ ሰፈር የቀድሞው ኖሬላ ግቢ የቀጥታ ስልክ ቁጥር 0114-40-34-34 0114-42-22-70/71/72
E-mail አድራሻ info@dce.et.com የድህረ ገጽ አድራሻ www.dce.et.com
ፓ.ሳ.ቁ.3414 ፋክስ ቁ 0114- 40-04-71/0114-42-07-46
የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ
