ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
ፍልውሃ አገልግሎት ድርጅት ከዚህ በታች የተገለጽውን አቃ/አገልግሎት ግዥ ለመፈጽም ተጫራቾች በግልጽ የጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
በዚህ መሰረት፦
ለመጀመሪያ ጊዜ ጨረታ የሚወጡ የዕቃ/የአገልግሎ ግዥ
ሎት 1 የውጪ ኦዲተር አገልግሎት
ሎት 2 የዓሣ አቅርቦት ግዥ
ሎት 3 ተቆልቶ የተፈጨ ቡና አቅርቦት ግዥ
ሎት 4 ሮል ወረቀት 80,60 ግዥ
ተጫራቾች የሚከተሉትን መመሪያዎች ማሞላት ተግባራዊ ማድረግ አለባቸው
- ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩበት ሕጋዊና የታደሰ የ2016 ዓ/ም የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር ስለመክፈላቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
- ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ ስለመሆናቸው የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ TIN እና VAT ሠርተርፍኬት ያላቸው የገቢዎች ክሊራንስና ጨረታ ለመሳተፍ ከሀገር ውስጥ የተሰጣቸውን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣ ከገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር በአቅራቢዎች ዝርዝር የምዝገባ ፈቃድ የተመዘገቡና የቅርብ ጊዜ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
- ማንኛውም ተጫራች ለሎት 2፣3 እና 4 ግዥ የጨረታ ማስከበሪያ ብር 10,000.00/አስር ሺ ብር/ እና ለሎት 1 ግዥ የጨረታ ማስከበሪያ ብር 20,000.00(ሃያ ሺ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ/CPO/ ብቻ ማስያዝ አለባቸው።
- ለእያንዳንዱ ጨረታ ሰነድ መግዣ የማይመለስ ብር 100.00/አንድ መቶ ብር/ በድርጅታችን አዲሱ ፍልውሃ ሆቴል እንግዳ መቀበያ በመክፈል ከድርጅቱ ግዢ አቅርቦት ቡድን መሪ ቢሮ ቀርበው የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የሚሰጡት ዋጋ ከቫት በፊትና ከነቫቱ ተብሎ በኢትዮጲያ ብር መገለጽና መሆን አለበት ። ተጫራቾች በጨረታ ሰነዶቻቸው ላይ ስማቸውን፣ ሙሉ አድራሻቸውን፤ ፊርማቸውንና ማህተም አሞልተው ማቅረብ አለባቸው።
- ጨረታው ከተከፈተ በኃላ በጨረታ ሠነድ ላይ የተሰጠ ዋጋን መለወጥ አይቻልም። ዕቃው የሚቀርብበት ጊዜ፣ቦታው ጽንቶ የሚቆይበት ጊዜ መገለጽ አለበት።
- ጨረታው ከተከፈተ በኃላ ለማሸነፍ እንዲረዳዎት ለማንኛውም ኃላፊና ሠራተኛ መደለያ የሰጠ ተጫራች ከጨረታ የሚሰረዝ ሲሆን አሸንፎም ውል ቢዋዋል ውሉ ይሰረዛል።
- ድርጅታችን የዋጋ ለውጥ ሳይኖር በመጠን ወይም በዋጋ እስከ 25% በመጨመር መግዛት እንደማይችል በቅድሚያ መታወቅ ይኖርበታል።
- ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ ከቫት በፊት ወይም ከቫት ጋር በግልጽ በመሙላት በስም በታሸገ ኤንቨሎፕ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 30/4/2016 ዓ/ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ። ጨረታው ጠዋት በዕለቱ 4፡30 ይከፈታል።
- ተጫራቾች በሚጫረቱበት የግዥ አይነት መሠረት የተሞላ የቴክኒካል ሰንድ እና ፋይናሽያል በተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ (Bid document)መሰረት ጨረታ ሰነዳቹሁን ማስገባት ይኖርባችኃል። የጨረታው ቴክኒካል ፕሮፓዛል ሰንድ ልብቻው የጨረታ ማስከበሪያ /CPO/ ለብቻው እና ፋይናሽያል ሰነድ ለብቻው በጨረታ ሣጥኑ ማስገባት አለባቸው።
- የጨረታ ሂደቱ የቴክኒክ ግምገማ ድርጅቱ በሚያወጣው መስፍርት መሰረት ቴክኒካል ሠነድ ግምገማና ድርጅታዊ ብቃት ግምገማ እና ናሙና ጥራት ግምገማ ውጤት (60%) እና የፋይንሻያል ዋጋ ግምገማ ውጤት (40%) ሲሆን ድምር ውጤት ከ100% አሸናፊ የሚላይ መሆኑን ማወቅ አለባቸሁ። ነገር ግን ቴክኒካል ግምገማ ሰነድ ወይም ደርጅታዊ ብቃት ያላለፈ ተጫራች ድርጅት ፍይናንሽያል ሠነድ እንደማይከፍል እንዲታወቅ። የመገምገሚያ መስፈርቶች በሚሰጠው የጨረታ ሰነድ ማየት ይቻላል።
ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ፦ ስልክ ቁጥር 0115519100/011553 07 67/0115157373
የፍልውሃ አገልግሎት ድርጅት
