Tender Detail

Tender Details

  • Deadline25 Dec 2023, 5:16 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Accounting & Auditing

ወንበር ጠረጴዛና ሌሎች ተዛማች የቢሮ ዕቃዎችን ለመግዛት የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር ኢ.ግ .ሥ .ኮ/ብግጨ /04/2016


የኢትዮጲያ የግብርና ሥራዎች ኮርፓሬሽን በ2016 በጀት ዓመት ለቢሮ አገልግሎት የሚውል ወንበር፤ጠረጴዛ፤ ሼልፍ ሌሎች ተዛማች የቢሮ ዕቃዎችን ከጨረታ ሰነዱ ጋር በተያያዘው ቴክኒካል መስፈርት መሠረት ማቅረብ የሚችሉ ተጫራቾችን በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል። በመሆኑም በጨረታው ለማሳተፍ የሚፈልጉ በዘርፉ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር ለምክፈላቸው ማስረጃ የቫት እና ቲን ተመዝጋቢ፤ ከገቢዎች ክሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ ተጫራቾች ዘወትር በሥራ ሰዓት ሳሪስ አቦ በሚገኘው ፋፋ የምግብ አ/ማ ጀርባ በሚገኘው የኮርፓሬሽኑ ዋና መ/ቤት ቢሮ ቁጥር 110 ቀርበው የተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ የማይመለሰ ብር 200.00/ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ። ተጫራቾች ለጨረታው ዋስትና ማስከበሪያ ብር 60,000/ ስልሳ ሺ ብር/ በሲፖኦ ወይም በባንክ ጋራንቲ (Unconditional) ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል። የጨረታው ዋጋ ለ60 ቀናት የጽና መሆን ይኖርበታል። ጨረታው ታኅሣሥ 23 ቀን 2016 ዓ/ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኮፓሬሽኑ የስብሰባ አዳራሽ ይከፈታል። ኮርፓሬሽኑ የተሻለ ዘዴ ካገኝ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰርዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ ማብራራያ፦ ስልከ ቁጥር 0114709095 ወይም 011442-36-08

ፍክስ 0114 42 13 12

አዲስ አበባ ኢትዮጲያ

የኢትዮጲያ የግብርና ሥራዎች ኮርፓሬሽን 
 

Save Tender