የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 1
ቂሊቲ ማረ/ቤት ማእከል የሲቪል ሠራተኞች፣ የሥራ ልብስና ጫማዎች የእግር ኮስ፣ የመርብ ኮስ፣ፊሸካ እንዲሁም ለሕግ ታራሚዎች አግልግሎት የሚውል ዩኒፎርም በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ አሸናፊ ድርጅቶች መግዛት ይፈልጋል።
በዚሁ መሠረት፦
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ የሚፈልጉ ሁሉ፣ በሥራው መስክ ህጋዊ የንግደ ፈቃድ ያላቸው የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር በእቃ ግዢ አገልግሎት አቅራቢያዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ የተጨማሪ እሴት ታክስ/ቫት/ እንዲሁም ቲን ቁጥር (Tin Number) ተመዝጋቢ የሆነ ግብር ስለመክፈሉ የተሞላ ማስረጃ ሊያቀርቡ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል።
- የጨረታ ቁጥር 1 ለሕግ ታራሚዎች እና አልባሳት የሲቪል ሠራተኖች የሥራ ልብስና ጫማዎች ለጨረታው ማስከበሪያ የውል ብር 10,000./አሥር ሺሀ ብር /በባንክ በተመሰከረለት ሲፒኦ(CPO) ከጨረታው ሰነዳቸው ጋር አያይዞ ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች አነዱ በሌላ ተጫራች ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ ተቀባይነት የለውም።
- ተጫራቾች የዋጋ ማቅረቢያ/ፕሮፎርማቸው /በሰም የታሸገ ኤንቨሎፕ አሽገው ማቅረብ አለባቸው።
- የጨረታ ቁጥር 1 ታኀሣሥ 18 ቀን 2016 ዓ/ም ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት የጨረታ ሰነዳቸውን በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ የገዢ ክንውን ቡድን ቢሮ ቁጥር 02 ማስገባት ይችላሉ። ጨረታው በዚሁ እለት ከረፋዱ 4፡15 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በማረ/ቤቱ የስብሰባ አዳራሽ ይከፈታል።
- አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉበት እቃዎች በራሳቸው ትራንስፖርት ለቃሊቲ ማረሚያ ማእከል/አዲሱ ማረሚያ ማእከል አባ ሳሙኤል/በሚገኘው ግ/ቤታቸው ማስረከብ አለባቸው ማረ/ቤቱ የሚገዛቸው እቃዎች በጨረታ ሰነዱ ተዘርዝረው ቀርበዋል።
- ተጫራቾች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነዱ ለእያንዳንዳቸው የማይመለስ በ 100.00/አንድ መቶ ብር በመክፈል ቃሊቲ በሚገኘው በኢትዮጲያ ንግድ ባንክ አካውንት ቁጥር 1000000791188 ቃሊቲ ማ/ቤ እደ/ጥ/ማእከል በሚል ገንዘቡን ገቢ ካደረጉ በኃላ የጨረታ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ።
- ተጫራቾች ጨረታው ሰነድ ከተከፈለ በኃላ ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ ላይ ለውጥ ማድረግ እንዲሁም ከጨረታው ራሳቸውን ማግለል አይችሉም።
- ተጫራቾች ፕሮፎርማቸው ላይ ዋጋ ሲጽፉ ስርዝ የሌለበት ጎላ ብሎ የሚነበብ ጽሑፍ መሆን ይገባዋል።በአሃዝና በፊደል መጽፍ የጠበቅባቸዋል።
- መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ከገኝ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰርዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፦ቃሊቲ ክራውን ሆቴል ፊት ለፊት ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር፦
011-4-39-76-61/011-439-49-16 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ
የቃሊቲ ማረሚያ ቤት ማእከል
