Tender Detail

Tender Details

  • Deadline24 Dec 2023, 11:48 PM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Accounting & Auditing

የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 001/2016


የባሌ ዞን ማረሚያ ቤት ጽ/ቤት በማረሚያ ቤቱ ለሚገኘው የሕግ ታራሚዎች አግልግሎት የሚውሉ የምግብ እህሎች፣ ማጣፈጫ ቅመማ ቅመሞች እና የማገዶ እንጨት በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

ስለዚህ ቀጥሎ የተዘረዘሩትን የጨረታ መስፈርቶች የሚያሞሉ የንግድ ድርጅቶች በጨረታው መወዳደር ይችላሉ።

ተጫራቾች በሚወዳደሩበት ዘርፍ ለ2016 ዓ/ም የታደስ ሕጋዊ የንግድ ፈቃዳቸው (Trade license)፣ የንግድ ምዝገባ ወረቀት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT)፣ የግብር ከፋይ መለያ (TIN) ሰርተፊኬት። የአቅራቢነት ምዝገባ ማስረጃ (supplier list) ይኖርባቸዋል። 
ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ በወጣበት የሥራ ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የሥራ ቀናት የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 50 (ሃምሳ ብር) ከመክፈል ከባሌ ዞን ማረሚያ ቤት ከቢሮ ቁጥር 5 መግዛት ይችላሉ።
ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ 15,000.00 (አሥራ አምስት ሺህ ብር) የያዘ ሲፒኦ ብቻ እውቅና ካለው ባንክ በማቅረብ መወዳደር አለባቸው።
ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ እና የቴክኒካል ኦርጅናል ሰነድ (ለ2016 ዓ/ም የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ፈቃዳቸውን (Trade license)፣ የንግድ ምዝገባ ወረቀ፣ የተጨማሪ ታክስ (VAT) ፣ ከግብር ከፋይ መለያ (TIN) ሰርተፊኬት፣ የአቅራቢነት ምዝገባ ማስረጃ (supplier list) ማቅረብ አለባቸው።
ተጫራቾች ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት የሥራ ቀን ጀምሮ የሚጫረቱባቸውን ሰነዶች በመግዛት ኦሪጅናል ፋይናንሻል (ዋጋ የተሞላበት) ሰነድ ፋይናንሻል ኮፒ ሰነድ እንዲሁም ቴክኒካል ኦሪጅናል ሰነድ ሦስቱንም ሰነድ በተለያዩ ፓስታዎች አሽገው ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ዘወትር በሥራ ሰዓት የጨረታው ሳጥን እስከሚታሸግበት እለት እና ሰዓት ድረስ ማስገባት ይችላሉ።
እያንዳንዱ ሰነድ እና የታሸገ ፖስታ ላይ ድርጅቱ ኃላፊ ፊርማ እና ማህተም መኖር አለበት።
ጨረታው በማስታወቂያ ከወጣበት በ16ኛው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ እለት ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። እለቱ በዓል ወይም ዝግ ከሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን ጨረታው ይከፈታል።
በጥቃቅን እና አነስተኛ ንግድ ተደራጅተው የበሰለ ምግብ ለማቅረብ የሚቀርቡ ማህበራት ቅድሚያ ይሰጣቸዋል።
ተጫራቾች ማሸነፋቸው በደብዳቤ ከተገለጽላቸው ከ5 ቀን በኃላ ከ6ኛው ቀን ጀምሮ ባሉት የሥራ ቀናት ውስጥ በመ/ቤቱ ቀርበው ውል መፈራረም አለባቸው።
መ/ቤቱ በአሁኑ ከዚህ ጨረታ በፊት ተወዳድረው እያቀረቡ ያሉትን አቅራቢዎች እንዳስፈላጊነቱ ውል በማደስ ለቀጣይ 6 ወራት የማስቀጠል መብቱ የተጠበቀ ነው።
ቢሮው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰርዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር፦ 022 244 0023/0932311224 ደውለው ይጠይቁ  

የባሌ ዞን ማረሚያ ቤት ጽ/ቤት

ሮቤ
 

Save Tender