የሐራጅ ሽይአጭ ማስታወቂያ
በፍ/ባለመብተ ኤልያሰ ተምሳለ እና በፍ/ባለእዳ እነ አቶ ኢሳያሰ አሰፍ መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም
ጉዳይ የፌደራል የመጀመሪያ ደርጃ ፍ/ቤት በመ/ቁጥር 176735 በ18/7/2010 ዓ.ም እና በመ/ቁ 61424 በ08/5/2010 ዓ.ም በዋለው ችሎት በሰጠው ትእዛዝ መሠረት በጉለሌ ክ/ከተማ ወረዳ 8 የቤ/ቁ 315 የሆነው ቤት የቦታው ስፋት 179 ካ.ሜ የሆነው የሐራጅ ሽያጭ መነሻ ዋጋ ብር 55,652.23(ሃምሳ አምስት ሺህ ስድስት መቶ ሃምሳ ሁለት ከ23 ሳንቲም ብር) ሆኖ የትራንዛክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ጥር 10 ቀን 2016 ዓ.ም በሐራጅ ይሸጣል፡፡ የተጫራቾች ምዝገባ በ5፡00 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል፡፡
የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፌደራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ዳይሬክቶሬት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጣቸው ሦስት የስራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈጽጽ ዳይሬክቶሬት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3፡00 ጀምሮ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፖርት ንብረቱ ባለበት ቦታ ድርስ በመውሰድ መጎብኘት የሚችሉ ሲሆን፤ እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን ግምት 1/4 ኛውን በንግድ ባንክ በተረጋገጠ c.p.o ማስያዝ ይኖርበታል፡፡ ከ1/4ኛ አስበልጦም ሆነ አሳንሶ c.p.o የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም፡፡ በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበት ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ/አ/ዳ/ስም c.p.o አሰርተው በኢትዮጲያ ንግድ ባንክ በተከፈተ አሰርቶ ሙሉ ገንዘቡን በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት፡፡ የፍ/አ/ዳይሬክቶሬት ንብረቱን በህጋዊ መንገድ በሐራጅ ስለመሸጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመጻፍ ባለፈ ስም የማዛወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልጻለን፡፡
በኢፌዲሪ የፌዴራል ፍ/ቤቶች የፍርድ አፈጻጸ ዳይሬክቶሬት
