የኦሮሚያ ሲቪል ምዝገባ ኤጀንሲ ከዚህ በሠንጠረዥ ውስጥ የተዘረዘሩትን ዕቃዎችን በ2016 በጀት ዓመት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
የኦሮሚያ ሲቪል ምዝገባ ኤጀንሲ ከዚህ በሠንጠረዥ ውስጥ የተዘረዘሩትን ዕቃዎችን በ2016 በጀት ዓመት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በም እሆኑም በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች።
ሀ በመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ድረገጽ በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ ውይም ከገንዘብ እና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር/ቢሮ የተሰጣቸው የምዝገባ ሠርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ።
ለ የተጨማሪ እሴት ታክስ ሠርተፍኬት የግብር ከፋይ ሠርተፍኬት እና የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
ሐ በሚወዳደሩበት ዘርፍ የተሰማቱበትን የታደሰ ንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ ።
መ በእንግሊዘኛ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 400.00 /አራት መቶ ብር/ በመክፈል ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራብ ሰዓት ለ15 /አሥራ አምስት / ተከታታይ ቀናት ከኤጀንሲው ፋይናስ ክፍል መግዛት ይችላሉ።
ሠ ተጫራቾች ለእያንዳዱ የጥቅል /የሎት/ ዝርዝር ዕቃዎች የጨረታ ማስከበሪያ በጨረታ ሰነድ ውሥጥ የተቀመጡ የብር መጠን በባንክ ክፍያ ማዘዣ የተረጋገጠ /CPO/ ወይም ቅድመ ሁኔታ ያላስቀመጠ የባንክ ዋስትና ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
ረ ተጫራቾች ለሁሉም የግዥ አይነት ቴክኑካል እና ፋይናሽያል ሰነድ ለየብቻ በፖስታ አሽገው ማቅረብ አለባቸው።
ሰ ተጫራቾች መወዳደሪያ ሰነዳቸው በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ በኤጀንሲው ግዥ ፋይናስ እና ንብረት አስተዳደር በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ እስከ 15/02/2016 ዓ/ም ከቀኑ 5፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
ሸ ጨረታው በ15/2/2016 ዓ.ም ከቀኑ 5፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚያው ዕለት ከቀኑ 5፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኦሮሚያ ሲቪል ምዝገባ ኤጀንሲ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ውስጥ ይከፈታል።
ቀ ኤጀንሲው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ወይም በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው። ለተጨማሪ መረጃ አድራሻ ኦሮሚያብ ሲቪል ምዝገባ ኤጀንሲ ሳር ቤት ከጨፌ ኦሮሚያ ጽ/ቤት ጎን
ስልክ ቁጥር፦ 0923049806/09266756518
| Lot No | Item No | Description | Unit of Mea surement | Quantity |
| 1 | 1.1 | Biometric Tablet | PCS | 600 |
| 1.2 | Heavy Duty Scanners | PCS | 2 | |
| 1.3 | Projector | PCS | 1 | |
| 1.4 | sMART sCREEN | PCS | 1 | |
| 1.5 | Laptop Computers | PCS | 4 | |
| 1.6 | Wi.Fi router | PCS | 2 | |
| 1.7 | Network and Mainte nance Kit | PCS | 1 |
