braና ማተሚያ ቤት ድርጅት የተለያያኡ አይነት የህትመት ወረቀቶችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
በዚህም መሠረት በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተገለፁትን መስፈርቶች በማሟላት መሳተፍ ትችላላችሁ።
1ኛ በዘርፉ በዘመኑ የታደሰ የንግድ ምዝገባ ማቅረብ የሚችሉ።
2ኛ የዘመኑን ግብር የከፈሉና ለዚህም ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
3ኛ የግብር ከፋይነት መለያ ሠርተፍኬት ማቅረብ ይሀሚችሉ።
4ኛ የቫት የመዝጋቢ የሆኑና ሠርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ።
5ኛ ግብር የመክፈል ግዴታቸውን የተወጡ መሆኑን የሚያረጋግጥ ከግብር ሰብሳቢው ባለስልጣን ጨረታ ላይ መሳተፍ እንዲችሉ የተሰጠ ክሊራንስ/ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
6ኛ በመንግስት ግዥና ንብረት ማሰወገድ ኤጀንሲ በአቅራቢነት ለመመዝገባቸው ማስረጃ ያላቸው።
7ኛ ተጫራቾችች ለጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር ሁለት መቶ /200.00/ በመክፈል ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ ያሥራ ቀናት /ቅዳሜ ግማሽ ቀንን ጨምሮ/ ወሎ ሰፈር በሚገኘው ዋና መሥሪያ ቤት ቢሮ ቁጥር 32 በአካል በመምጣት የጨረታ ሰነድ መግዛት ይችላሉ።
8ኛ ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን ያቀረቡበትን ዋጋ 2% በሲፒኦ /CPO/ ማስያዝ ይኖርቸዋል።
9ኛ ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ የማስረከቢያ ጊዜ መጥቀስ አለባቸው።
10ኛ ተጫራቾች በጨረታው ያሸነፏቸውን ዕቃዎች ድርጅቶች መጋዘን ድረስ ማድረስ አለባቸው።
11ኛ ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት 11ኛው የሥራ ቀን እስከ 8፡00 ሰዓት /ከሰዓት/ ድረስ በሰም በታሸገ ፖስታ ለጨረታ ማስገቢያ በተዘጋጀውየጨረሣጥን ውስጥ ማስገበት አለባቸው። ጨረታ ተጫራቾች በተገኙበት ማስታወቂያው በወጣ በ 11ኛው ቀን 8፡00 /ከሰዓት / ታሽጎ 8፡30/ከሰዓት በድርጅቱ የስብሰባ አዳራሽ ይከፈታል።
12ኛ ድርጅትቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሽዐ፦ከወሎ ሰፈር ወደ ጎተራ በሚወስደው መንገድ 700 ሜትር ገባ ብሎ በስተግራ በኩል።
ስልክ ቁጥር ፦0114426480።
