Tender Detail

Tender Details

  • Deadline08 Sep 2023, 1:50 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Accounting & Auditing

በደ/ብ/ብ/ሕ/ክ።መንግስት የአማሮ ወረዳ ፋይናስ ጽ/ቤት ለወረዳው ሴክተር መሰርያ ቤቶች በ2016 በጀት ዓመት የጽህፈት መሣሪያና ሌሎች አላቂ ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።


በጨረታው ለመሳተፍ ማሟላት የሚገባቸው መስፈርቶች።

1. በዘርፉ ንግድ ፈቃድ የዘመኑ ግብር ተከፍሎ የታደሰ ቲን ቁጥር ሰርተፍኬት የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀቅት የአቅራቢነት ምዝገባ ምስክር ወረቀቅት ቫት ተመዝጋቢነት ምስክር ወረቀት ያለውና የሚያቀርብ።

2. ጨረታ የሚካሄድበት ቦታ አ/ል/ወ/ፋ/ጽ/ቤት ግዥ ን/አስ/ዋ/ሥ/ሂደት ቢሮ ቁጥር8

3. ተፈላጊ የጽህፈት መሳሪያና ሌሎች አላቂ ዕቃዎችን የሚያቀርብበትን ዋጋ በዋጋ ማቅረቢያ ፕሮፎርማ ሞልቶ ከተፈላጊ መረጃዎች ፎቶ ኮፒ ጋር በፖስታ አሽጎ የሚያቀርብ።

4. የጨረታ ሰነድ የማይመለስ 50 /ሃምሳ ብር ብቻ/ ለአማሮ ልዩ ወረዳ ገቢዎች ባለስልጣን ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በመክፈል ጨረታው ከወጣበት ዕለት ጀምሮ እስከ 15ኛው ቀን ድረስ ዘወተር በሥራ ሰዓት ከፋይናስ ጽ/ቤት ግ/ን/አስ/ሥራ/ሂደት ቢሮ ቁጥር- 8መውሰድ ይቻላል።

5. የጨረታው ሣጥን የሚታሸግበትና የሚከፈትበት ቀናት ሰዓት በተመለከተ ይህ ማስታወቂቅያ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ወደ ፊት የሚቆቅጠር በ15ኛው ቀን 8፡00 ሰዓት ታሽገው በዕለቱ በ8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። ዕለቱ  በሳምንቱ ዕረፍት ወይም በህዝብ በዓል ላይ ከዋለ በሚወጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል።

6. የጨረታው አሸናፊ አሸናፊነቱ ይፋ ከሆነበት ዕለት ጀምሮ ለ7 የሥራ ቀናት ለቅሬታ አቤቱታ ጊዜ ሰጥቶ ከ8ኛው እስከ 15ኛው ቀን ድረስ የጠቅላላ ዋጋ 10% የውል ማስከበሪያ ይዞ በመቅረብ ውል ካልተፈራረመ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው ሲፒኦአ ለመንግስት ውርስ በማድረግ ለአፈፀሙ ለክልል ግዥ ኤጀንሲ ሪፖርት እናደርጋለን።

7. የጨረታው ማስከበሪያ 10,000.00 /አስር ሺህ ብር ብቻ/ በጥሬ ገንዘብ ወይም በሲፒኦአ የሚያስይዝ መሆን አለበት።

8. አሸናፊ ድርጅት ያሸነፈውን ዕቃዎችን ሁሉንም ወጪ ችሎ እስከ አማሮ ልዩ ወረዳ ፋይናስ ጽ/ቤት እጋዝን ድረስ አቅርቦ ማስረከብ አለበት።

9. በጨረታ ሰነድ ላይ ናሙና የሚጠየቁትን ዕቃዎችንና ሌሎችም ያልተጠየቁትም ኦርጅናልና 1ኛ ደረጃ ትክክለኛ ማቅረብ አለበት።

10. አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፈበትን ዕቃ በጥራት 1ኛ ደረጃ መሆን አለበት ። አቀላቅሎ የሚያቀርብ ካለ እንደ ተጨበረበረ ተቆቅጥሮ በክልል ግዥ ኤጀንሲና በህግ እርምጃ እድወስድበት ይደረጋል።

11. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብት አቅለው

         ለበለጠ መረጃ ፦ 0464570452/0916130084

 

Save Tender