በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ የወረዳ 13 አስተዳደር ፋይናስ ጽ/ቤት የግዥ ቡድን
- የፅህፈት መሳሪያዎች
- የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች
- የጽዳት እቃዎች
- አላቂ የቢሮ እቃዎች
- የደንብ ልብስ
በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
በዚህም መሰረት ተጫራቾች፦
1 በዘርፉ የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድ ያላቸው
2. የቫት ተመዝጋቢ መሆፕናቸውን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
3. በጥቃቅንና አነስተኛ የተደራጁ ከሆነ ከጥቃቅንና አነስተኛ ተቋማት የተፃፈ የድጋፍ ደብዳቤ ማቅረብ የሚችሉ።
4። በኢትዮጵያ ግብር ህጎች በተሰነገገው መሰረት የግብርና የታክስ ግዴታ መወጣቱን የሚያመለክቱ ሰነዶች ማቅረብ የሚችሉ።
5. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ የተጫረቱበትን ከአጠቃላይ ዋጋ 2% /ሁለት ፐርሰንት/ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦአ ጨረታው ከመክፈቱ በፊት ለብቻው በታሸገ ፖስታ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
6. ተጫራቾች የማይመለስ 100.00 ብር/ አንድ መቶ ብር/ በቻ በመክፈል ዝርዝር ጉዳዩን የያዘው ሰነድ ከጽ/ቤቱ መግዛት ይችላል።
7. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በገዙበት ሰነድ ላይ ባለው የዋጋ ማቅረቢያ ቦታ ላይ በግልጽ በመሙላትና በእያንዳንዱ ዋጋ ማቅረቢያ ላይ ድርጅቱን የሚገልጽ ፊርማና ማህተም በማድረግ ኦርጅናሉናና ኮ[ፒውን በተለያያኡ ፖስታ በማሸግ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉበት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት ለዚሁ ጨረታ ለማገልገል በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ በጽ/ቤቱ በመቅረብ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
8. ተጫራቾች በሚወዳደሩበት ለእያንዳንዱ እቃ ናሙና ማቅረብ አለባቸው።
9. ጨረታው በ10ኛው የስራ ቀን ከቀኑ 11፡30 ሰዓት ጨረታው ተዘግቶ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ11ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 4፡#0 ሰዓት ይከፈታል።
10. መስሪያ ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፦ አቃቂ ቃሊቲ ክፍል ከተማ ወረዳ 13 አስተዳደር ኤጀካ ኢትዮጵያ ህንጻ አርሴማ አደባባይ ዝቅ ብሎ ገብራኤል በተክርስቲያን ፊትለፊት
ለበለጠ መረጃስልክ ቁጥር 0912807618 ወይም 09211711351
