ንፋስ ስልክ ቀለም ፋብሪካ ኃ/የተ/የገ/ማኅበር የተለያዩ አላቂ የፅሕፈት መሣሪያዎች በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
በጨረታው ለመሳፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች፦
1. ዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ የዘመኑ ብር የከፈሉ መሆኑን የሚያመለክት ማስረጃ አንዲሁም የግብር ከፋይ ምዝገባ ሰርተፍኬት እና የተጨማሪ እሴታ ታክስ የምዝገባ ምስክር ወረቀት ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
2. ሳር ቤት አካባቢ በሚገኘው የድርጅቱ ዋና መስሪያ ቤት JFK አፓርትመንት 9ኛ ፎቅ ግዥና ንብረት አስተዳደር መምሪያ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር፦ 011-5-52-82-06 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ።
3. ሳር ቤት ከሚገኘው የድርጅቱ ዋና መስሪያ ቤት JFK አፓርተማ 9ኛ ፎቅ ግዥ ንብረት አስተዳደር መምሪያ በሥራ ሰዓት በመጣት የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100.00 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል መውሰድ ይችላሉ።
4. ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ የዕቃዎች ዋጋ ማቅረቢያ ቅፅ ላይ ዋጋ ማቅረቢአ ቅፅ ላይ ዋጋ በመግለፅ ትክክለኛ አድራሻቸውንና ስማቸውን እዲሁም ፊርማና ማህተም በማድረግ በታሸገ ኤንቨሎፕ ለዚሁ ሥራ በዋናው መ/ቤት JKF አፓርትመንት 9ኛ ፎቅ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥኑ ውስጥ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት አስራ አምስት /15/ ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
5. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና 5,000.00 /ኣምስት ሺህ ብር/ በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /CPO/ ከመጫረቻ ሠነዱ ጋር በማያያዝ የጨረታ ሳጥኑ ውስጥ ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ማስገባት አለባቸው የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ያላቀረበ ማንኛውም ተጫራች ከውድድሩ ውጭ ይሆናል።
6. ጨረታው ነሐሴ 23 ቀን 2015 ዓ.ም ከጠዋቱኢ 4፡40 ሰዓት ተዘግቶ በዚያው ዕለት በ4፤30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በንፋስ ስልክ ቀለም ፍፋብሪካ ኃ/የተ/የግ/ማኅበር ዋና መ/ቤት JFK አፓርትመንት 9ኛ ፎቅ ግዥና ንብረት አስተዳደር መምሪያ ይከፈታል ሆኖም ከጨረታው መዝጊያ ሰዓት ዘግይቶ የቀረበ የመጫረቻ ሰነድ ተቀባይነት የለውም።
7. ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
