በጉምሩክክ ኮሚሽን የአ/አ ኤርፖርት ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት የልዩ ልዩ ንብረቶች የግልጽ ጨረታ እና የሃራጅ ጨረታ ቁጥር 04/2016 05/2016 06/2016፤07/2016 እና 08/2016 የጨረታ ማስታወቂያ።
በአዲስ አበባ ኤርፖርት ጉምርኩ ቅ/ጽ/ቤት በተለያዩ ጊዜያት የጉምሩክ ሥነ፟ሥርዓት ባለመፈፀመ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ሞባይሎች የተሽከርካሪ ሞተር ተሽከርካሪ መለዋወጫዎች አልባሳት የቅየሳ መሳሪያ የብር ጌጣጌጥ እና ሌሎች እቃዎችን በሃራጅ ጨረታ እና ግልጽ ጨረታ ቁጥር 04/2016 በቀን 18/12/2015 ዓ.ም ጨረታ ቁጥር 07/2016 በቀን 25/12/2015 ዓ.ም እና ጨረታ ቁጥር 08/2016 በቀን 02/13/2015 ዓ.ም የሚካሄድ በመሆኑ የቀጣይ 2016 በጀት ዓ.መት ዕቅድ በተፈለገው መጠን ለማሳካት ዝርዝር መረጃ ከዚህ በታች በተራ ቁጥር 1-12 እንገልፃለን።
በመሆኑ፦
1. በቅ/ጽ/ቤቱ ለሚካሄደው ጨረታ ተጫራቾች በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ የክብር ከፋይ መለያ ቁጥር የተጨማሪ እሴት ታክስ ሰርተፍኬት እና የዘመኑን ግብር የተከፈሉ ለሞናቸው ከግብር ሰብሳቢ መስሪያ ቤት የተሰጠ ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
2. ማንኛውም የግልጽ ጨረታ ተጫራቾች ጨረታው አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ የጨረታውን ሰነድ ዘወትር በስራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ ከ2፡00 -6፡00 ሰዓት ከሰዓት በኋላ 7፡00- 11፡00 ሰዓት እዲሁም ቅዳሜ ጠዋት ከ2፡00 -6፡00 ሰዓት የማይመለስ ብር 100.00 /አንድ መቶ ብር/ብቻ በመክፈል አዲስ አባ ኤርፖርት ጉምሩክ መጋዘን ቅጥር ግቢ የውርስ ዕቃዎች አወጋገድ ቡድን በመምጣት የጨረታ ሰነድ መግዛት ይችላሉ።
3. በግልጽ ጨረታ ለመሳተፍ ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው ዕቃዎች የሰጡትን ዋጋ አምስት በመቶ /5%/ ዋስትና /CPO/ CUSTOMS COMMISSION ADDIS ABABA AIRPORT CUSTOM BRANCH OFFICE ስም ማሰራት ይኖርባአቸዋል።
4. ተጫራቾች የዕቃዎቹን ናሙና በአዲስ አበባ ኤርፖርት ጉምሩክ ካርጎ መጋዘን እና ገርጂ መጋዘን እስከ ሐምሌ 04/2015 ዓ.ም ሐምሌ 11/2015 ዓ.ም ሐምሌ 18/20115 ዓ.ም ሐምሌ 25/2015 ዓ.ም እና ጷጉሜ 2/2015 ዓ.ም ከቀኑ በ8፡00 ሰአት ተዘግቶ በዛው ቀን በ8፡20 ሰዐዐት የሚከፈት ይሆናል።
5.. በጨረታው የሚወዳደሩ ተጫራቾች ለጨረታው የሚሰጡትን ዋጋ የተጫራቾች ስም አድራሻ ፊርማ ና የጨረታ ማስከበሪያ ሲ.ፒ.ኦ /CPO/እን አከላይ በተ.ቁ1 የተገለጹትን ሰነዶች ኮፒ በታሸገ ኤንቨሎፕ ላይ በመፈረም አዲስ አበባ ኤርፖርት ጉ/ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ገርጂ የውርስ ዕቃዎች አወጋገድ ቡድን ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
6. ማንኛውም ተጫራች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ በጨረታ ሰንዱ የሰጠውን መግዣ ዋጋና መግለጫ መለወጥና ማሻሻል አይችልም።
7.ማንኛውም ተጫራች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ በጨረታው ግምገማ ተጠናቆ የጨረታው ውስጤት እስከሚታወቅ ድረስ ፀንቶ ይቆያል።
8. የጨረታው አሸናፊዎች ጨረታን ስለማሽነፋቸው ከትገለፀበት ጊዜ ጀምሮ በ05 /አምስት/ ቀናት ውስጥ ያሸነፊትን ዕቃ ዋጋ ገቢ ብ4እማድረግ እቃውን መረከብ አለባቸው።
9. ከላይ በተ/ቁ 8 በተገለጹት ቀናት ውስጥ ከፍያውን ገቢ ያላደረገ እና ንብረቱን ተረከቦ ያልወሰደ ተጫራች ለጨረታ ማስከበሪ ያስያዘው ሲፒኦ /CPO/ እና ለንብረቱ የከፈለው ዋጋ ለቅ/ጽ/ቤቱ ገቢ ሆኖ ዕቃው በድጋሚ ለሽያጭ ይቀርባል።
10. በተራ ቁጥር1-09 የተገለፀው እንደተጠበቀ ሆኖ በተጨማሪም ሃራጅ ጨረታ ቁጥር 04/2016 በቀን 04/12/2015 ዓ.ም ጨረታ ቁጥር 05/2016 በቀን 25/12/2015 ዓ.ም እና ጨረታ ቁጥር 08/2016 በቀን 02/13/2015 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በትገኙበት የምናካሄድ መሆኑንበዚሁ አጋጣመ እናሳውቃልን ናሙና በአዲስ አበብ ኤርፖርት ጉምሩክ ገርጂና ካርጎ ውርስ መጋዘን በመገኘት መመልከት ይችላሉ።
11. በሃራጅ ጨረታ የሚወዳደሩ ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ 50,000.00 /ሃምሳ ሺህ ብር/ ለየዘርፉ በጉምሩክ ኮሚሽን የአ/አ ኤርፖርት ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት ስም ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
12 ቅ/ጽ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታው ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር ቦሌእ ኤርፖርት 0116-68-45-37; 0116-68-52-47 &0116-62-88-68-ይጠይቁ።
