በምስራቅ ሐረርጌ ዞን የጎሮጉቱ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2016 በጀት ለቢሮ ስራ አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ የጽሕፈት መሳሪያዎች ቋሚ እቃዎች የኤሌክትሪክስና የመኪና መለዋወጫ እቃዎችን የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
ተጫራቾች ማሟላት ያለባቸው መስፈርቶች።
1. የ2015 ዓ.ም ግብር የከፈሉና እና ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው።
2. የ2015 ዓ.ም ግብር የከፈልሉ እና የታደሰ የንግድ ፈቃድ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
3. የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ተመዝጋቢ መሆናቸውን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
4. በአቅራቢዎች ዝርዝርዝ ተርታ የተመዘገቡና ማስረጃ ያላቸው።
5. ያሸነፍበትን እአቃ እስከ ጎሮጉት ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት መጋዘን ድረስ በራሱ ወጪ ማቅረብ የሚችል።
6.ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /BID BOND/ የሚመለስ ገንዘብ በንግድ ባንክ የተረጋገጠ ቼክ ሲ.ፒ.ኦ 15,000.00 /አስራ አምስት ሺህ ብር ከጨረታ ሰነዱጋር ጨረታው ከመዘጋቱ በፊት ማስያዝ ኖርባቸዋል።
7. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የስራ ቀናት የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል መግዛት ይችላሉ።
8. ተጫራቾች እያንዳዱ የጨረታሰነድ ዋናውና ፎቶ ኮፒውን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
9. ማንኛውም ተወዳዳሪ የተወዳደረበትን እቃ ዝርዝር እራሱ ግምጃቤት ውስጥ ያለው መሆን አለበት።
10. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታው በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
