የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን እቃዎች እና አገልግሎቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት/ለማሰራት ይፈልጋል።
| መድብ | የዕቃው አይነት | የጨረታ ማስከበሪያ |
| ሎት አንድ | የአይቲ እና ሌሎች የኤሌክትሮኒክስ መሳሪያዎች | 100,000 |
| ሎት ሁለት | የጽህፈት መሳሪያ | 5,000.00 |
| ሎት ሶስት | የፕሪንተር/ፎቶ ኮፒ ቶነር | 10,000.00 |
| ሎት አራት | የስራ መገልገያ ዣንጥላ | 3,000.00 |
| ሎት አምስት | የተለያዩ ህትመቶች | 2,000.00 |
| ሎት ስድስት | የተከርካሪ ጎማ | 30,000.00 |
| ሎት ሰባት | የተሽከርካሪ አልባሳት | 10,000.00 |
1. ተጫራቾች የዘመኑን ግብር የከፈሉና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
2.የቫት ተመዝጋቢ ሆነው ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉና መለያ ቁጥር /ቲም ነበር ያላቸው መሆን አለበት።
3. ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና በዘርፉ የተሰማሩ መሆን የኖርባቸዋል።
4. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ከላይ የተጠቀሰውን በሎቱ ለየብቻ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
5. የጨረታ አሸናፊዎች አሸናፊነታቸው ከተገለፀ በኋላ ያሸነፉበት ዕቃ ወይም አገልግሎት 10% የውል ማስከበሪያ ሲ.ፒ.ኦ ማስያዝ አለባቸው።
6. ተጫራቾች በግዥ አገልግሎት በአቅራቢነት ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡና የምስክር ወረቀት የሚያቀርቡ ብሎም ባሁን ሰዓት ያሉ መሆን አለባቸው።
7.ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ድረስ ከመንግስት ግዥ ዳይሬክቶሬት ፋይናስ ዳይሬክቶሬት ብር 100 በየሎቱ በመክፈል መውሰድ ይችላሉ።
8. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸው በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ እስከ 11ኛው የስራ ቀን 3፡45 ሰዓት ድረስ ለዚህ ተብሎ በተዝጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
9. መ/ቤቱ ባዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ላይ ዋጋ ሞልተው የድርጅቱ ህጋዊ ማህተብና ፊርማ አድርጎ ያላቀረበ ተጫራች ተቀባይነት አይኖረውም።
10. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን የመጫረቻ ሰነድ ፋይናሺያ ዋና እና አንድ ኮፒ እዲሁም ተክኒካል ዋና እና አንድ ኮፒ ለየ ብቻ በማድረግ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
11. ቢሮው በጨረታ ሰነዱ በተገለጸው ዕቃ/የአገልግሎት ፍላጎት መጠን የጨረታ ሰነዱ ላይ ከውል በፊት 20% ሊጨምር ወይም ሊቀንስ ይችላል።
12. ጨረታው ጸንቶ የሚቆይበት ጊዜ 60 ቀናት ነው። አንድ ተጫራች ባቀረበው ዋጋ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም ።
13. ጨረታው የሚዘጋበት ቀን የጨረታ ማስታወቂያ በወጣው 11 ቀን ጠዋት 3፡45 ታሽጎ በዕለቱ 4፡15 ሰዓት በመ/ቤቱ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።ይህ ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓትና ቦታ ይሆናል።
14. ቢሮው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙልም የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው ።
አድራሻ፦ መገናኛ ቦሌ ክከተማ ወረዳ 5 የቤት ቁጥር 71 ላንሴት ሆስፒታል የሚገኝበት ጊቢ ውስጥ በጀርባው ባለው ህንፃ 2ኛ ፎቅ የመንግስት ግዥ ዳይሬክቶሬት
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፦ 011-8-33-25-01
