Tender Detail

Tender Details

  • Deadline13 Aug 2023, 5:18 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Accounting & Auditing

በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የከተማ ልማት ኮሚሽን ቢሮ በ2016 በጀት ዓመት በክልሉውስጥ ለሚገኙ ከተሞች ለመንገድ ግንባታ ሥራ ፕሮጀክቶች የሚውል የኮንስትራክሽን መሳሪያ ዎች 1. ግሬደር 2 ሩሎ. 3. ኤክስካቫተር እና 4. ሎደር መስፈርቱ ከሚሟሉ አቅራቢዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መከራየት ይፈልጋል


1. ኮንስትራክሽን ማሽነሪ አቅራቢዎች የሆኑ ተጫራች ከስራው ጋር አግባብነት ያለውን ለ2015 ዓ.ም የታደሰ የንግድ ወይም የአገልግሎት ሣራ ፈቃድ የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ምዝገባ ሰርተፍኬት የመንግስት የግብር ግዴታ መወጣቱን የሚያመለክት ወቅታዊ ማስረጃ /current Tax Clearance/ ከሚመለከተው ገቢዎች ቢሮ የመንግስት መ/ቤቶች በሚያወጡት ጨረታ ላይ መሳተፍ የሚያስችል የምስክር ወረቀት እዲሁም ታክስ ከፋይ መሆናቸውን የሚገልጽ /TIN/ ማስረጃ ከጨረታ ሰነዳችውጋር አያይዘው ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።

2. የጠጠር  መንገድ ግንባታ ሥራ ለመስራት መ/ቤቱ የሚፈልገውን የማሽን  ብዛት በአንድ ፓኬጅ ውስጥ የተገለጸውን ማቅረብ የሚችል።

3. አቅራቢው ለውድድር ያቀረበው የብቃት /ቴክኒካል/ መወዳደሪያ ሰነዶች ዋና /ኦርጅናል/ ሲጠየቅ አቅርቦ ማመሳከር አለበት ይህ ተጣርቶ ኮፒው ከቅዋናው ጋር ተመሳክሮ ትክክለኛ ካልሆነ አቅራቢው ከውድድር ውጪ ይሆናል።

4.የጨረታ ማስከበሪያ /bid security/ብር 100,000.00 /አንድ መቶ ሺህ/ በባንክ በተረጋገጠ ዋስትና /BANK GURANTEE/ ወይም የክፍያ ማዘዣ /CPO/ ከመጫረቻ ሰነድ ጋር ማቅረብ የሚችሉ።

5. ተጫራቾች በተጫራች መመሪያ ደንብ መሠረት  ህጋዊ ፈቃዳቸውናና ተ.እ.ታ /VAT/ የተመዘገቡበትን ሠርተፍኬት ታክስ ክሊራንስ በማቅረብ ተጫራቾች ለሥራው የተዘጋጀውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 16 /አስራ ስድስት / ተከታታይ የስራ ቀናት የማይመለስ ብር 300.00  ሦስት መቶ ብር/ በሲዳማ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ ግዥ ፋይናስ በመክፈል ሰነዱ መውሰድ ይችላሉ።

6. የጨረታ ሰነድ በተጫራች መመሪያ መሰረት ተሞልቶ የጨረታ ማስከበሪያ /bid bond/security/ ፋይናሺያል አንድ ዋና /ኦርጅናል/ ሁለት ሁለት ኮፒዎች እዲሁም የቴክኒካል አንድ ዋና /ኦርጅናል/ ሁለት ሁለት ኮፒዎች ሰነድ በተለያየ  ኤንቨሎፕ  በሰም በማሸግ ለየብቻችው ታሽገው በአንድ ዋና /ኦርጅናል/ ሁለት ሁለት ኮፒዎች ስበተለያየ ኤንቨሎፕ በማሸግ ለየብቻ ታሽገው በአንድ ትልቅ ፖስታ ውስጥ ተከተውና በሁለት ዶክመንት ላይ ስምና አድራሻቸው በመፃፍ ህጋዊ የሆነ ማህተም በመምታት ይህ ማስታወቂቅያ ከወጣቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት እስከ 6፡00 ሰዓት በሲዳማ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የከተማ ልማት ኮንስትራክሽን ቢሮ ግዥ/ፋይናስ አስተዳደር ክፍል ለዚሁ አገልግሎት በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

7. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙብት ከላይ በተጠቀሰው ቀንና ቦታ 6፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ ከቀኑ 8፡00 ሰአት ላይ ይከፈታል። የተጫራቾች አለመገኘት የጨረታውን መከፈት አይገደውም።

8. አሰሪው መ/ቤት የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው.

9. አንድ ተጫራች ከሁለት ጨረታ ሰነድ በላይ መወዳደርም ሆነ የጨረረታ ሰነዱን መግዛት አይቻልም ።

10. የጨረታ መዝጊያ መክፈቻ ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከላይ በተገለጸው ቦኦታና ሰዓት ይሆናል።

ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር ፦ 0462124356

የመ/ቤቱ አድራሻ ከሀዋሳ ገብራኤል ቤተክርስቲያን ጀርባ ከሀዋሳ ቤተሰብ መምሪያ ጎን ነው።

Save Tender