Tender Detail

Tender Details

  • Deadline11 Aug 2023, 5:44 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Accounting & Auditing

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ቀጥሎ ለተዘረዘሩት የግንባታ ስራዎች ብቁ የሆኑ ደረጃ 1 የጨረታ ሰነዱን ከኢትዮጵያ መንገድ ግሩፕ ስትራቴጂ ሶርሲንግ ክፍል በኢ.ሜል የህናጣ እና አጠቃላይ አማጅ=ካሪ ድርጅቶች ን በጨረታ አወዳድሮ የኮንስትራት አስተዳደር ማግኘት ይችላሉ።የዲዛይን ግምገማና የግንባታ ቁጥጥር /Design review Adminstration and Constraction Supervision/ ለማሰራት የፈልጋል።


  የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ቀጥሎ ለተዘረዘሩት የግንባታ ስራዎች ብቁ የሆኑ ደረጃ 1 የጨረታ ሰነዱን ከኢትዮጵያ መንገድ ግሩፕ ስትራቴጂ ሶርሲንግ ክፍል በኢ.ሜል የህናጣ እና አጠቃላይ አማጅ=ካሪ ድርጅቶች ን በጨረታ አወዳድሮ የኮንስትራት አስተዳደር ማግኘት ይችላሉ።የዲዛይን ግምገማና የግንባታ ቁጥጥር /Design review Adminstration and Constraction Supervision/ ለማሰራት የፈልጋል።

1. የጅማና የጋቤላ ኤርፖርት የተርሚናል እድሳትና የእሳት አደጋ መከላከያ ጣቢያ ግንባታ።

2. የአክሱም አውሮፕላን ማረፊያ የተርሚናል እና መንደርደሪያ ሜዳ ጥገና።

3. የመቅረሌ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ የመዳረሻ መንገድ ግንባታ የእሳት አደጋ መከላከያ ጣቢያ የሳይት ስራ እና ሌሎች መሰረተ ልማቶች ግንባታ።

4. አዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊ የአቪዬሽን ደህንነት እና የፖሊስ መኖሪያ ሕንፃዎች ግንባታ።

ስለሆነም ለስራው ብቁ የሆኑ ተጫራቾች የዘመኑን የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ተመዝጋቢ የሆኑ የዘመኑን ግብር የከፈሉ በመንግስት ጨረታዎች ለመሳተፍ ፍቃድ ያላቸው እና ከግብር እዳ ነጻ ስለመሆናቸው ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል።

ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት የስራ ቀናት በአቅራቢያቸው ከሚገኙ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርጫፍ የማይመልስ 100.00 ብር/ አንድ መቶ ብር/ በሂሳብ ቁጥር 1000006958277/E-99/ ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ጨረታ ቁጥር ssnt-t400በሚል ገቢ በማድረግና የከፈሉበት የገቢ ደረሰኝ ቅጅ /Deposit Slip Copy/ ከታች በተጠቀሰው የኢሜል አድራሻ በመልካ የጨረታ ሰነዱን ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ እስትራቴጂ ሶርሲንግ ክፍል በኢሜል ማግኘት ይችላሉ።

ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ብር 150,000.00 /አንድ መቶ ሃምሳ ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒኦ /CPO/ ወይም ለ150 ተከታታይ ቀናት የሚቆይ ምንም አይነት ውድመ ሁኔታ የሌለው የባንክ ዋስትና ማቅረብ ይኖርባቸዋል። ከማንኛውም ኢንሹራንስ የሚቀርብ ዋስትና ተቀባይነት አይኖረውም ። አሸናፊው ከተለየ በኋላ በጭዕረታው ለተሸነፉት ተጫራቾች ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ወዲያውኑ ተመላሽ ይሆናል ተጫራቾች በጨረታው ደንብ መሠረት የመጫረቻ ሠነዳቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ስትራቴጂክ ሶእሲንግ ክፍል እስከ ዓርብ ነሐሴ 12፣2015 ዓ.ም ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ድረስ ማቅረብ አለባቸው።

ጨረታው ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቦሌ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና መስሪያ ቤት በተመሳሳይ ሰዓት ቀን ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ይከፈታል።

ለተጨማሪ ማብራሪያ፦

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ

ቦሌ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ

ስትራቴጂክ ሶርሲንግ ክፍል

ስልክ ቁጥር 011-517-4918

ኢሜል፦Ashebir Te@ethiopianairlines.com

የኢትዮጵያ አየር ምነገድ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ ወይም የማሻሻል መብቱ የተጠበቀ ነው።   

Save Tender