የጎንደር ዩንቨርሲቲ ምንትዋብ ንግድና ኢንዱስትሪ ኢንተርፕራዝ በ2016 ዓ.ም በተፈቀደ መደበኛ በጀት መድኋኒቶች የህክምና ግብዓቶች ግዥ መፈፀም ይፈልጋል።
1. በዘርፉ የወጣውና ለዘመኑ የንግድ ሥራ ፈቃድ ኮፒ ግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ክፒ የተጨማሪ እሴት ታክሲ ባለሰልጣን የተሰጠ ድጋፍ ደብዳቤ ኮፒ ፍርመውና በድርጅታቸው ማህተም አረጋግጠው ዋናውን ማቅረብ አለባቸው።
2. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሚሆን የጠቅላላ ዋጋውን 1% ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር በማያያዝ ማቅረብ ይኖርባቸዋል። በጥሬ ገንዘብ ወይም ከታወቀ ባንክ በሚሰጥ ሲፒኦ ወይም በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ ቼክ ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና በእቴጌ ምንትዋብ ንግድና ማማከር ኢንተርፕራዝ ስም አሰርተው ማቅረብ አለባቸው በሁኔታ ላይ ያልተመሠረት ዋስትና ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ቢያንስ ከ90 ቀን በታች መሆን የለበትም።
3 ተጫራቾች በተ.ቁ 1እና 2 የተጠቀሱትን ማስረጃዎች በአንድ ፖስታ እንዲሁም የዋጋ መወዳደሪያ ሰነዳቸውን ኦርጅናል ኮፒ በማለት በተለያየ ፖስታ በማሸግና በማያሻማ ሂኔታ በጀርባው ላይ ኦርጅናል ኮፒ በሚል ቃል በጽሑፍ በማመላከትና በድርጅታቸው ማህተም በማረጋገጥ ማቅረብ አለባቸው።
4. ሁሉም /ሶስቱም/ ፖስታዎች በአንድ ትልቅ ፖስታ ተጠቃለው ታሽገውና በድርጅቱ ማህተም ተረጋግጠው መግባት አለባቸው።
5. ማንኛውም ተጫራች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ጎንደር ዩንቨርሲቲ እቴጌ ምንትዋብ ንግድና ማማከር ኢንተርፕራዝ ፍያናስና አስተዳደር ገንዘብ ያዝ ቢሮ ቁጥር 06 እንዲሁም አዲስ አበባ ከሚገኘው የዩንቨርሲቲው ጉዳይ ማስፈጸሚያ ጽ/ቤት ዘወትር በሥራ ሰዓት በመምጣት በማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል መውሰድ ይችላሉ።
6። ተጫራቾችች የጨረታ ማወዳደሪያቸውን በጎንደር ዩንቨርሲቲ እቴጌ ምንትዋብ ንግድናማማከር ኢንተርፕራዝ ልዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ይህ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር እስከ 16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይችላሉ። ጭዕረታውም ታዛቢዎችና ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተግኙበት በዚሁ እለት 4፡01 ታሽጎ በእለቱ 4፡30 እቴጌ ምንትዋብ ንግድ ማማከር ኢንተርፕራዝ ይከፈታል። ሆኖም 16ኛው ቀን የሕዝብ ወይም በዐዐል ከሆነ በሚቀለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓትና ቦታ ይከፈታል።
7. ተጫራች የሚያቀርቡት ጨረታ ከተእተ ቀን ጀምሮ ቢያንስ ለ90 ቀን ድረስ ጽንቶ መቆየት አለበት።
8. ማንኛውም ተጫራችዋጋ ሲሞላ ቫትንና ሊሎችን ታክስ እዲሁም የትራንሥፖርት ዋጋ ጨምሮ መሆን አለበት። የታክስ ሁኔታ ያልተገለፀ ከሆነ የተሞላው ዋጋ ማንኛውም የመንግስት ታክስና ወጪ አካቶ እደተሞላ ተደርጎ ይቆጠራል።
9. ኢትርፕራይዙን የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፈል የመሠረዝ መብት የተጠበቀ ነው።
10. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 05 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 0908085555 በመደወል ማግኘት ይችላሉ።
8.
