ንብረታቸው የዋሊፍ ንግድና ኢንዱስትሪ አ.ማ ያገለገሉ ገልባጭ ሲኖ ትራክ መኪናዎች ባሉበት ሁኔታና ቦታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል። ስለሆነም ተጫራቾች ከዚህ በታች የተመለከቱትን ነጥቦች በማሟላት ቀርበው መወዳደር ይችላሉ።
1.በጨረታው የሚወዳደሩበት ተጫራቾች ኢትዮጵያዊ ዜኘት ያላቸው ሆኖ ሠነድ ለመግዛት ሲመጡ ይህንኑ የሚያረጋጥግጥ ሰነድ ወይም መታወቂያ ይዘው መቅረብ ይኖርባቸዋል።
2. በዋሊፍ ንግድ ኢንዱስትሪ አ.ማ በሚገኝበት አራት ኪሎ ንብ ባንክ ህንፃ ቁጥር 2 ቢሮ ቁጥር 212 በመምጣት የንብረቶችን ዝርዝር መረጃ የያዘ የተጫራች መመሪያ እና የዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ የማይመለስ ብር 1000.00 /አንድ ሺህ ብር/ ከፍለው መውሰድ ይችላሉ።
3. ተጫራቾች ሰነድ ገዝተው ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ቀናት ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት እስከ 10፡00 ሰዓት ባለውጊዜ ውስጥ ያገለገሉ ግልባጭ ሲኖ ትራክ መኪናዎች በቡራዩ አሸዋ ሜዳ በሚገኘው ዋሊፍ ቡናና ሻይ ፋብሪካ በመሄድ መመልከት ይችላሉ።
4.ተጫራቾች የሚገዙትን ያገለገሉ ንብረቶችን የጨረታ መነሻ ዋጋ 10 በመቶ /10%/ የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ከጨረታ ሰነዱ ጋር በማያያዝ በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ በዋሊፍ ንግድና ኢንዱስትሪ አ.ማ አስተዳደር ቢሮ ቁጥር 212 ለዚህ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ጨረታው ከመዘጋቱ በፊት ማስገባት ይኖርበታል።
5. የጨረታ ሳጥኑ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10ንዐው ቀን ከጠዋቱ በ4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚያው ቀን 4፡15 ሰዓት ተጫራች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት አራት ኪሎ ንብ ባንክ ህንፃ ቁር 2 ቢኦሮ ቁጥር 212 ይከፈታል። ሆኖም የመክፈቻ ቀኑ ቅዳሜና እሁድ ወይም የበዓል ቀን ላይ ከዋለ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል። እንዲሁም ተጫራቹ በራሱ ምርጫ ጨረታው በሚከፈትበት ጊዜ ሳይገኝ ቢቀር የጨረታውን መከፈት አያስተጓጉልም።
6. በጨረታው አሸናፍወ ተጫራቾች አሸናፊነታቸው ከተገለፀላቸው ከ7 የሥራ ቀናት በኋላ ባሉት ተከታትይ የሥራ ቀናት ውስጥ ያሸነፉትን ዋጋ በሙሉ መክፈል ይኖርባቸዋል። ሆኖም ሙሉ ክፍያውን በተጠቀሰው ጊዜ ገደብ መክፈል ከቻላቹ ያስይዙትን የጨረታ ማስከበሪያ አክሲዮን ማህበር ገቢ ይደረጋል።
7. የጨረአው መገምገሚያ መስፈርት ዋጋና የተሟላ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ሲፒኦ/ እንዲሁም በሰነዱ የተገለፁትን አሟልቶ መገኘት ነው። የሚወዳደሩበትን ያገለገሉ ንብረቶች የመነሻ ዋጋ 10 በመቶ /10%/ ያላስያዘ እና በሰነዱ የተቀመጡ ሌሎች ነጥቦች ያላሟላ ተጫራቾች ከጨረታው ውድቅ ይደረጋል። የሚዘጋጀው የጨረታው ማስከበሪያ ሲፒኦ ከአዲስ አበባ ውጭ ከሆነ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርጫፍ ብቻ መሆን ይኖርበታል።
8. አገልግሎት ባወጣው ጨረታ ሰነድ በስሙ ሳይገዛ የተወስዳዳረ ማንኛውም ተጫራቾች ከተገኘ ከውድድር ውድቅ ይደረጋል።
9. በጨረታ አሸናፊ የሆኑ ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን ንብረቶች ሙሉ ክፍያ ከፍሎ እስከሚወስድ ድረስ ለውል አተገባበር ዋስትና የሚሆን የጠቅላላ ዋጋውን 10 በመቶ በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ማስያዝ አለበት።
10. አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉበትን ገንዘብ አጠቃለው በመክፈል ንብረቶቹን በ10 ቀናት ውስጥ የማንሳት ግዴታ አለባቸው።
11. ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ በስልክ ቁጥር 0118-12-30-93 ወይም 0118-12-30-98 ደውለው መጠየቅ ይቻላል።
12. አገልግሎቱ ጨረታውን ለመቀበል ወይም ላለመቀበል የሚችል ሲሆን በማንኛውም ጊዜ ጨረታውን ለመሰረዝ መብቱ የጠጠበቀ ነው።
