ድርጅትቻን የኢትዮጵያ የደረጃዎች ኤጀንሲ ያወጣውን የጥራት መስፈርት የሚያሟላ ከሀገር ውስጥ አምራቾች ወይም መዳመጫ ፋብሪካ ካላቸው አቅራቢዎች 8,000.00 ኪንታል የተዳመጠ ጥጥ በግልፅ ጨረታ አወዳደሮ መግዛት ይፈልጋል።
በጨረታ መካፈል የሚፈልጉ ተጫራቾች ።
1. በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ሥራ ፍቃድ የዘመኑ ግብር ስለመክፈላቸው የሚያረጋግጥ ክሊራንስ የግብር ክፋይ ምዝገባ ሠርተፍኬት ያላቸው በግዥ ኤጀንሲ አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ መሆን አለባቸው።
2. ይተዳመጠ ጥጥ አቅራቢዎች አምራች ወይም የመዳመጫ ፋብሪካ ያላቸው መሆን አለባቸው።
3. ለጨረታ የተዘጋጀውን ዝርዝር የጨረታ ሠነድ 200.00 /ሁለት መቶ ብር /የማይመለስ በመክፈል ፒያሳ ከሊፋ ህንፃ ፊት ለፊት ቢስ መብራት ከሚገኘው የድርጅቱ ዋና መስሪያ ቤት የኢንዱስትሪ ግባቶች ግዥ ዳይሬክቶሬት ቢሮ በመቅረብ ዘወትር በስራ ሰአት ከሰኞ እስከ አርብ ከጠዋቱ 2፡00 _ 6፡30 ከ 7፡30_ 11፡00 መግዛት ይቻላል።
4.የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር 500.00 በኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ግባቶች ልማት ድርጅት ስም በተዘጋጀው ሲፒኦ ብቻ በጨረታ ሰነዱ ላይ በተጠቀሰው መእረት ለብቻው ብታሸገ ኢንቨሎፕ በማድረግ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
5.የጨረታ መወዳደሪያ ዋጋቸውና ከላይ ከተጠቀሱት ህጋዊ ሠነዶች ጋር በተለያዩ በታሸግእ ኤንቨሎፕ አንድ ኦርጅናል እዲሁም አንድ ኮፒ በማድረግ እስከ ሐምሌ 12ቀን 2015 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ በኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ግባቶች ግዥ ዳይሬክቶሬት ቢሮ ማቅረብ ይቻላል።
6. ጨረታው በተመሳሳይ ቀን ሐምሌ 12ቀን 2015 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡10 ተጫራቾች በተገኙበት ይከፈታል።
7. ከጨረታው መዝጊያ ሰዓት ውጭ የሚመጣ ተጫራቾች ተቀባይነት የለውም።
ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠርተዝ እንዲሁም ለማህበረሰቡ ይጠቅማሉ ያላቸውን ውሳኔዎች የመወሰን መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ ብስክ ቁጥር
0113-69-22-43/69-18-86
