የገዋብኔ ግብርና ቴ/ሙያ ስልጠና ኮሌጅ በ2016 በጀት ዓመት ለመጠጥ ውሃ አቅርቦት የፍሳሽ ጫኝ ከባድ ተሽከርካሪ /ቦቴ / ከሀገር ውስጥ አቅራቢዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመከራየት ይፈልጋል።
በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ አቅራቢዎች ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች ማሟላት ይኖርባቸዋል።
- በስራ መስኩ መስማራሩ የሚገልፅና የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው
- የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት
- የዘመኑ ግብር ለመክፈላቸው ከግብር ሰብሳቢው መስሪያ ቤት ጊዜው ያላለፈበት ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
- የግብር ከፋይ ምዝገባ ሰርተፍኬት የተሰጠ ማስረጃ
- የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ የምስክር ወረቀት
- የታደሰ የባለቤትነ ማረጋገጫ መታወቂያ
- ሶስተኛ ወገን የምድህን ዋስትና ሽፋን ያለው።
— በመንግስት ግዥ ንብረት አስተዳደር የአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ የድረ_ ገጽ ማስረጃ
♦ ተጫራቾች የጨረታ ዋስትና ብር 7,000.000 /ሰባት ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ /CPO/ብቻ በገዋንኔ ግብርና ቴ/ሙያ ስልጠና ኮሌጅ ስም ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
♦ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ለመግዛት የምትፈልጉ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ከኮሌጁ ግዥና ሽያጭ ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ብር 300.00 /ሦስት መቶ ብር/ በመክፈል መወሰድ የምትችሉ መሆኑን እና ለበለጠ መረጃ ሰነዱን ለማግኘት በስልክ ቁጥር 09 91 78 58 20 በስራ ሰዓት መደውል የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።
♦ ጨረታው ሃምሌ 11 ቀን 2015 ዓ.ም በገዋኔ ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ታሽጎ በ5፡00 ሰዓት ይከፈታል።
♦ መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ በማንኛውም ጊዜ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
