Tender Detail

Tender Details

  • Deadline01 Aug 2023, 3:44 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Accounting & Auditing

የሚንስቴሩ መ/ቤቱ ግብር ከፋዮች የሚጠበቅባቸውን የታክስ ዕዳ በታክስ ህጉ በተፈቀደለት የጊዜ ገደብ ባለመከፈላቸው ምክኛት በታክስ አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 983/2008 በተሠጠው ስልጣን መሠረ የግሪን ላንድ ሓ/የተ/የግ/ማህበር ኤመራልድ ሪዞርት ንብረት የሆነ በጋሞ ዞን አርባምንጭ ከተማ በ30,000.00 ካ/ሜ ላይ የተገነቡ በርካታ የመኝታ ክፍሎች ሬስቶራንትስ መዋኛ ኩሬዎች የህፃናት መጫወቻዎች የመሰብሰቢያ አዳራሾች የአስተዳደር ቢሮዎች እና ሌሎች ለሪዞልቱ አስፈላጊ የሆኑ ዕቃዎች የተሟሉበት ለበርካታ ለአገር ውስጥ እና የውጭአገር ዜጎች ምቹ በመዝናንዐነት ያገለገለ እና በቀጣይ የሚያገለገል የሪዞርቱ ንብረት ሁኔታ በድጋሚ በግልፅ ጨረታ አቅርቦ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።


  የሚንስቴሩ መ/ቤቱ ግብር ከፋዮች የሚጠበቅባቸውን የታክስ ዕዳ በታክስ ህጉ በተፈቀደለት የጊዜ ገደብ ባለመከፈላቸው ምክኛት በታክስ አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 983/2008 በተሠጠው ስልጣን መሠረ የግሪን ላንድ ሓ/የተ/የግ/ማህበር ኤመራልድ ሪዞርት ንብረት የሆነ በጋሞ ዞን አርባምንጭ ከተማ በ30,000.00 ካ/ሜ ላይ የተገነቡ በርካታ የመኝታ ክፍሎች ሬስቶራንትስ መዋኛ ኩሬዎች የህፃናት መጫወቻዎች የመሰብሰቢያ አዳራሾች የአስተዳደር ቢሮዎች እና ሌሎች ለሪዞልቱ አስፈላጊ የሆኑ ዕቃዎች የተሟሉበት ለበርካታ ለአገር ውስጥ እና የውጭአገር ዜጎች ምቹ በመዝናንዐነት ያገለገለ እና በቀጣይ የሚያገለገል የሪዞርቱ ንብረት ሁኔታ በድጋሚ በግልፅ ጨረታ አቅርቦ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

1. በግልጽ ጨረታ ለመሳተፍ የሚፈልጉ ማንኛውም ተጫራቾች ማንነቱን የሚገልፅ የነዋሪነት መታወቂያ /ፓስፖርት/ ከጨረታ ሰነዱ አያይዞ በኤንቨሎፕ በማሽግ ለግልጽ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርበታል።

2. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ይህ የግልጽ ጨረታ በጋዜጣ  ከወጣበት ቀን ጀምሮ በስራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ እና ቅዳሜ ጠዋት ከ2፡00 ሰዓት ህንፃ '''መ'' 3ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር  301 ከግዥ ፋይናስ አስተዳደር ዳይሬክቶሬት የማይመለስ ብር 100.00 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ህንፃ '''ሀ''' 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 201 ከታክስ ዕዳ አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ መውሰድ ይኖርበታል።

3. በግልፅ ጨረታ ለመሳተፍ ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው ንብረቶች የሰጡትን ዋጋ 1/10ኛውን ብቻ ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /CPO/ በገቢዎች ሚንስቴር ስም /Minstry of Revenue/በባንክ አሰርተው ማስያዝ ይኖርባቸዋል።

4. ተጫራቾች በሚከተለው የጨረታ ቀናት /ስኬጁል/ መሰረት ሰነድ ገዝተው መጫረት ይችላሉ።

ተ.ቁ የመ/ቤቱ ስም ለጨረታ የቀረበው የንብረት ዓይነት የንብረቶች መመልከቻ ቀን የጨረታው የመዝጊያ እና የመክፈቻ ቀንና ሰዓት
1 ገቢዎች ሚኒስቴር 30,000.00 ካ/ሜ ላይ ያረፈ የኤምራልድ ሪዞርት ድርጅቶች ንብረት እና ሙሉ ይዞታ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ30 ቀናት ማስታወቂያው በጋዜትዐ ወጥቶ 30ቀን ከተጠናቀቀ በኋላቀጥሎ ባለው 31 ኛ ቀን 3፡45 ሰዓት ተዘግቶ በዚያኑ ቀን በ4፡00 ሰዓት ይከፈታል።

5. የጨእረታ መክፈቻ ቦታ መገናኛ በሚገኘው በሚኒስቴር መ/ቤቱ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ተጫራቾች /ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት //ወይም በታዛቢዎች ፊት ይከፈታል።

6. የግልፅ ጨርታው መክፈቻና መዝጊያ 31ኛው ቀን የመ/ቤቱ የሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ ቀን የግልፅ ጨረታው መክፈቻና መዝጊያ ቀን ይሆናል።

7. ለጨረታው አሸናፊ ተጫራቾች ለጨረታው ማስከበሪያ ዋስትና ያስያዙት  /CPO/ከሚከፍሉት ዋጋ እንደ አስፈላጊነቱ የሚታሰብላቸው ሲሆን ለተሸናፊ ተጫራቾች ድግሞ የግልጽ ጨረታ ኮሚቴው መረጃውን አጣርቶ እደጨረሰ በ5 የስራ ቀናት ውስጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል።

8. የሪዞርቱን እና የተሽከርካሪ ጨረታ ለሚያሸንፉ ተጫራቾች ከስመ-ንብረት ዝውውር ጋር ተያያዥነት ያላቸውን ወጪዎችን ።የቦሎና ሌሎች ተጓዳኝ ወጪዎች/ ሻጭን አይመለከትም።

9. አሸናፊ ተጫራቾች ማሸነፋቸው በደብዳቤ ከተገለፅላቸው ቀን ጀምትሮ ባሉት 15 ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ጠቅላላ ዋጋ መ/ቤቱ በሚሠጠው አድራሻ ገቢ በማድረግ ያሸነፉበትን ሀብት/ ንብረት መረከብ ይኖርባቸዋል።

10. ከላይ በተ/ቁ.9 በተግለጹ ቀናት ውስጥ ክፍያውን ገቢ በማድረግ ንብረታቸውን ያልተረከቡ ተጫራቾች የግልጽ ጨረታው ተሠርዞ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት የዋስትና  ገንዘብ ለሚኒስቴሩ መ/ቤቱ ገቢ ሆኖ ንብረቱ እዳልተሸጠ ተቆጥሮ በቀጣይ በድጋሚ ለመሸጥ ይቀርባል።

11. ሚኒስቴር መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ የግልፅ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 011 617 84 90 ኮድ/2044/ /2045/ /2046/ የውስጥ መስመር /EXT/ 2044 ደውለው መጠየቅ ወይም የተቋሙን ዊብሳይት WWW.MOR.Gov.et መመልከት ይቻላል።

Save Tender