የኢዱስትሪ ሚንስቴር በአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት አሚባራ ወረዳ እና በሶማልያ ክልላዊ መንግስት ሽንሌ ወረዳ ፓይለት ሳይቶሽን በመምረጥ አንደኛየተቀናጀ የባዮ ማስ ኢነርጂ ምርምር እና ቴክኖሎጂ ሽግግር ስራ ለማስፋት አዋጭነት ጥናት ለማሰራት አማካሪ ድርጅትን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል። በተጨማሪ ለዚህ ፕሮጀክት አላማ የሚውል ጄኔነተር ዌልዲን ኬብል ግራይንደር እና ሌሎች ተያያዥ እቃዎች አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
የኢዱስትሪ ሚንስቴር በአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት አሚባራ ወረዳ እና በሶማልያ ክልላዊ መንግስት ሽንሌ ወረዳ ፓይለት ሳይቶሽን በመምረጥ አንደኛየተቀናጀ የባዮ ማስ ኢነርጂ ምርምር እና ቴክኖሎጂ ሽግግር ስራ ለማስፋት አዋጭነት ጥናት ለማሰራት አማካሪ ድርጅትን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል።
በተጨማሪ ለዚህ ፕሮጀክት አላማ የሚውል ጄኔነተር ዌልዲን ኬብል ግራይንደር እና ሌሎች ተያያዥ እቃዎች አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
1. በዚሁ መሰረት ከላይ ለተገለፁት ግዥዎች በዘርፉ ሕጋዊ የታደሰ የንግድ ስራ ፍቃድ እና የምዝገባ ምስክር ወረቀት ያላቸው የዘመኑን ግብር ስለመክፈላቸው ማረጋገጫ የሚያቀርቡና ከዚሁ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተወዳዳሪዎች በጨረታ እዲሳተፉ ይጋብዛል።
1. የዘመኑ ግብር የከፈለበት ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
2. ተጫራቾችን የተጨማር እሴት ታክስ /VAT/ተመዝጋቢ የሆኑ።
3. በመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ ለመዝገባቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
4. ተጫራቾች የእያንዳዱን የሚወዳደሩበትን ጨረታ ሠነድ ላይ የተገለፀውን የምክር አገልግሎት ዝርዝር ም4እግለጫ /TOR/ የዕቃ ግዥ መገለጫ Specfication/መሰረት በማድረግ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
5. በጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር 10,000.00 /አስር ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ /cpo/ ማስያዝ አለባቸው።
6. በጨረታው አሸናፊ የሆኑ ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን ዕቃዎች ጠቅላላ ዋጋ 10% የውል ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ CPO በማስያዝ ውል የመዋዋል ግዴታ አለባቸው።
7. የጨረታ ሰነዱን በመ/ቤቱ web site:-www.moi.gov.et በtelegram ወይም በemail የምንልክላችሁ መሆኑን እናሳውቃለን።
8. ማንኛውም ተጫራች የጨረታውን ሰነድ ማስታወቂያውን ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት ፋይናንስና ግዥ ዳይሬክቶሬት 1ኛ ፎቅ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል።
9. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን ቴክኒካልና ፋይናሺያል ኦርጅናልና ኮፒዎች ን ለየብቻ በትልቅ ፖስታ እና የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ሲፒኦ ለብቻው በአንድ ፖስታ በማሸግና የድርጅቱ ማህተም በማድረግ ማስገባት አለባቸው።
10. የጨረታ ማስታወቂው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በመ/ቤቱ web site:-www.moi.gov.et እና በጋዜጣ ከወጣብት በኃላ ሐምሌ 4/2015 ዓ.ም ጠዋት 4፡00 ሰዓት ላይ ታሽጎ 4፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግልጽ ይከፈታል።
11. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
12. ለተጨማሪ መረጃ መ/ቤቱ የሚገኘው 4 ኪሎ ከቱሪስት ሆቴል ጀርባ 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 122 በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥሮች 011 858 31 51 በመደወል መረጃ ማግኘት ይቻላል።
