Tender Detail

Tender Details

  • Deadline10 Jul 2023, 2:12 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Other Sales

የፌደራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ለዋናው መ/ቤትና ለቅርጫፍ ጽ/ቤቶች የሚያገለግል ዘመናዊ የፍተሻ መሣሪያ /Walkthrough metal Detector/ bzat 01/አንድ/ እና የጣት አሻራ ማሽን ብዛት 10/ አስር/ ግዥ በጨረታ መለታ ቁጥር FHC/NCB/PG/34/10/2015 ተጫራቾችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።


1. የፌደራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ለዋናው መ/ቤትና ለቅርጫፍ ጽ/ቤቶች የሚያገለግል ዘመናዊ የፍተሻ መሣሪያ /Walkthrough metal Detector/ bzat 01/አንድ/ እና የጣት አሻራ ማሽን ብዛት 10/ አስር/ ግዥ በጨረታ መለታ ቁጥር FHC/NCB/PG/34/10/2015 ተጫራቾችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

2. ለኮርፖሬሽን ዋናው መ/ቤቱና ለቅርጫፍ ጽ/ቤትቶች የሚያገለግል ዘመናዊ የፍተሻ መሣሪያዎች / Walkthrough metal Detector/ እና የጣት አሻራ ማሽን ግዥ ተጫራቾች የመወዳደሪያ ቴክኒካል ሰነዳቸውንና ዋጋቸውን በተለያዩ በታሸጉ ኤንቨሎፖች ማቅረብ አለባቸው።

3. ጨረታው የሚከናወነው በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ ሥነ ስርዓትና ይሄንኑ አስመልክቶ ለኢትዮጵያ ጌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግስት በወጣው የመንግስት ግዥ አዋጅ መሠረት ሲሆን ከሚፈለገው አገልግሎት ጋር የተዛመደ የታደሰ ፈቃድ ያላቸውን አየግብር ከፋይ ማስረጃ የሚያቀርቡ መሆን ይኖርባቸዋል።

4. የተሟላ የአማርኛ የጨረታ ሰነዶችን ማንኛውም ፍላጎት ያለው ተጫራች ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15 ተከታታይ ቀንቅት ውስጥ የማይመለስ ብር 300.00 /ሦስት መቶ ብር/ በመክፈል የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ለገሀር በሚገኘው በተለምዶ የስነ ምግባር ፀረ_ ሙስና ኮሚሽን ህንፃ 2ኛ ፎቅ ቁጥር 201 በኮርፖሬሽኑ ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት በአካል በመቅረብ መግዛት ይችላሉ።

5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዶችን በኮርፖሬሽኑ ግዥ ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 201 ለዚሁ ታሽጎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ጨረታው በመጀምሪያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ወይም ሐምሌ 3 ቀን 2015 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ እዲያቀርቡ ሆኖ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ብር 40,000.00 /አርባ ሺህ ብር/ በባንክ በተመሰከረለት ቼክ ወይም ሲፒኦ በፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ስም ከጨረታ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው። ዘግይቶ የቀረበ የጨረታ ሰነድ ውድቅ ይደረጋል ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ሐም ሌ 3 ቀን 2015 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 4፡15 ሰዓት የኮርፖሬሽኑ ግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት 2ኛ  ፎቅ በሚገኘው የስብሰባ አዳራሽ ይከፈታል።

6. ኮርፖሬሽኑ በሚያወጣው ፕሮግራም መሠረት አሸናፊው ተጫራች የዕቃዎችን ግዥ በኮርፖሬሽኑ ቅጥር ግቢ ያስረክባል።

7. ኮርፖሬሽኑ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ  ነው።

Save Tender