በአዳማ ጉምሩክ ኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤት ተወርሰው የሚገኙ የተለያዩ የመገናኛ እና የኮምፒውትውር እቃዎች /ሞባይሎች/ የፎቶ ግራፍና የእይታ መሣሪያዎች /መነጽር/ አዳዲስ አልባሳት ኮስሞቲክስ ኤሌክትሮኒክስ የኮንስትራክሽን እቃዎች እና 56 ሞተርሳይክሎችን በግልጽ ጨረታ እዲሁም የተሽከርካሪ መለዋወጫዎች የመገናኛ እና የኮምፒውተር እቃዎች አንድ ተሽከርካሪ እና 61 ሞተር ሳይክሎችን በሃራጅ ጨረታ ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል በሆኑም።
በአዳማ ጉምሩክ ኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤት ተወርሰው የሚገኙ የተለያዩ የመገናኛ እና የኮምፒውትውር እቃዎች /ሞባይሎች/ የፎቶ ግራፍና የእይታ መሣሪያዎች /መነጽር/ አዳዲስ አልባሳት ኮስሞቲክስ ኤሌክትሮኒክስ የኮንስትራክሽን እቃዎች እና 56 ሞተርሳይክሎችን በግልጽ ጨረታ እዲሁም የተሽከርካሪ መለዋወጫዎች የመገናኛ እና የኮምፒውተር እቃዎች አንድ ተሽከርካሪ እና 61 ሞተር ሳይክሎችን በሃራጅ ጨረታ ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል በሆኑም።
1. በአዳማ ጉ/ኮ/ቅ/ጽ/ቤት ለጨርታ በቀረቡት ዕቃዎች ላይ ለመወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ከሚሸጠው ዕቃ ጋር ተዛማጅነት ያለው የታደሰ ንግድ ፈቃድ የተጨማሪ እሴት ታክስ እንቅስቃሴዎችን ያሳወቁበት በቅርብ ጊዜ የተሰጣቸው የምስክር ወረቀት እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥሩን ከመጫረቻ ሰነዱ ጋር ተያይዞ በፖስታ በማሸግ ለግልጽ ጨረታ ብበተዘጋጀው ሳጥን እስጥ ማስገባት እና ለሃራጅ ጨረጨረታው በሚካሄድበት ቀን ማቅረብ ይኖርበታል።
2. በተራ ቁጥር 1 ላይ የተጠቀሰው ቢኖርም መነሻ ዋጋው ከ500 ሺህ ብር በታች የሆኑ ዕቃዎችን ለመግዛት የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ ያስፈልጋል።
3. በተራ ቁጥር 1 እና 2 የተጠቀሰው መስፈርቶች ቢኖርም ሞተር ሳክል እና ተሽለርካሪ ላይ ማንኛውም እድሜው ከ18 ዓመት በላይ የሆነ ኢትዮጵያዊ የቀበሌ መታወቂያ በመያዝ ያለ ቅድመ ሁኔታ ጨረታው ላይ መሳተፍ ይቻላል።
4. የግልጽ እና የሃራጅ ጨረታ ሰነዱ የጨረታ ማስታወቂአያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ ዘወትር ከሰኞ እስከ አርብ ሙሉ ቀን በስራ ሰዓት እና ቅዳሜ ጠዋት ከ2፡00_ 6፡00 ሰዓት በአዳማ ከተማ በከልቻ ትራንስፖርት አ.ማ ግቢ ውስጥ በሚገኘው የቅ/ጽ/ቤቱ የገቢ ሂሳብና ዋስትናዎች አስተዳደር ድን ቢሮ ቁጥር 11 የማይመለስ በር 100.00 /አንድ መቶ ብር/ በመግዛት በጨረታ የወጡትን ዕቃዎች ማየት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።
5. በግልጽ ጨረታ የሚሳተፉ ተእጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው ለእያንዳዱ ምድብ ለዕቃዎች የሰጡትን ዋጋ አምስት በመቶ /5%/ እና በሃራጅ ጨረታ ለምትወዳደሩ ማለትም ለምድብ 1 ተሽከርካሪ መለዋወጫ ብር 8,000.00 ለምድብ 2 የመገናኛ ና የኮፒውትር እቃዎች /ሞባይሎች/ 2,000.00 ምድብ 3 ሞተር ሳክሎ ለእያንዳዱ ብር 5,000.00 እና ምድብ 4 ተሽከርካሪ ብር 190,000 በባንክ በተመሰከረለት /CPO/ Customs Commission Adama Branch Office ስም በማሰራት በግልጽ ጨረታ በተራ ቁጥር 1 ላይ ከተጠቀሱት ሰነዶች ጋር በማያያዝ ሳጥን ውስጥ እድታስገቡ እንዲሁም ለሃራጅ ጨረታ ጨረታው በሚካሄድበት እለት ይዘው መቅረብ ይኖርባቸዋል።
6. በጨረታ ሽያጭ የእቃው አስመጪ ወይም ቤተሰብ የነበሩ ሰዎች መሳተፍ አይችሉም።
7. በገልጽ ጨረታ ለሽያጭ ለቀረቡት እቃዎች የጨረታ ሳጥኑ በሚገኝበት የቅ/ጽ/ቤቱ የውርስ መጋዘን አስተዳደር የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 21 ድረስ በመሄድ በጨረታው ለመሳተፍ የሚያስፈልገውን የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተመሰከረለት CPOየጨረታ ሰነዱን እና በተራ ቁጥር 1 ላይ ከተጠቀሱት ሌሎች ሰነዶች ጋር በፖስታ በማሸግ ሳጥኑ ከመዘጋቱ በፊት ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
8. በጨረታው ለመሸጥ የወጡት እቃዎች በአዳማ ከተማ በከልቻ ትራንስፖርት አ.ማ ግቢ መጋዘን ቁጥር 5 እና መጋዘን ቁጥር 10/ሜዳ ላይ/ በሚገኘው በቅ/ጽ/ቤቱ ስለሚገኙ ማስታወቂአይው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለግልጽ ጨረታ ባሉት 7 ተከታታይ ቀናት ላይ ከዋለ ሳጥኑ በስምንትእኛው ቀን ይሆናል። ለሃራጅ ጨረታ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 5 ተከታታይ ቀናት ቅየር ላይ ከዋለ በኋላ በስድስትኛው ቀን 4፡00 ሰዓት ላይ የሚከፈት ሲሆን ስድስተኛው ቀን በዓል ወይም እሁድ ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን የሚካሄድ ይሆናል።
9.የግልጽ ጨረታ ሳጥኑ የሚከፈትበት ቦታ ቅ/ጽ/ቤቱ መሰብሰቤያ አዳራሽ ሲሆን ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት ይከፈታል ሆኖም ተጫራቾች ካልቀረቡ ታዛቢዎች ባሉበት የጨረታ ሳጥኑ ይከፈታል።
10. አሸናፊው ተጫራች ለጨረታው ዋስትና ያስያዙት /CPO/ ከሚከፍሉት ዋጋ ጋር የሚታሰብላቸው ሲሆን ለአሸናፊ ተጫራች ደግሞ የጨረታው ውጤት በተገለፀ በ3 /ሶስት/ የስራ ቀናት ውስጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል።
11. አሸናፊው ተጫራች ማሸነፋቸውን በማስታወቂያ ከተገለፀላቸው ቀን ጀምሮ በ5 ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ገንዘብ ገቢ በማድረግ እቃውን መረከብ ይኖርባቸዋል።
12. ለጨረታ የቀረቡት እቃዎች ሽያጫቸው የሚፈፀመው ባሉበት ሁኔታ ስለሆነ ተጫራቾች ሌላ ተመሳሳይ ወይም ተጨማሪ እቃ መጠየቅ ይችሉም።
13. ከላይ በተ/ቁቅቅ ላይ በተገለትጹት ቀናት ውስጥ ክፍያውን ገቢ ያላደረጉ እና ንብረቱን ያልወሰዱ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት /CPO/ ለመ/ቤቱ ገቢ ሆኖ ዕቃው በድጋሚኢ ለሽያጭ ይቀርባል።
14. ማንኛውም ተጫራች 100 ብር ሰነድ የገዛበትን ደረሰኝ ለግልጽ ጨረታ ከሌሎች ሰነዶች ጋር አያይዞ በጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ሲሆን ለሃራጅ ጨረታ ጨረታው በሚካሄድበት ዕለት ከሌሎች ሰነዶች ጋር ይዞ መገኘት አለበት።
15. ቅ/ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥሮች፦ 022-111-84-29እና 022-211-89-25ደውለው መጠየቅ ይቻላል።
