የኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርት ሎጄስቲክ አገልግሎት ድርጅት የጥበቃ አገልግሎት ግዥ መሰጠት የሚችሉ ድርጅቶችን አወዳድሮ አገልግሎቱን መግዛት ይፈልጋል።
በመሆኑም በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ በዘርፉ የተሰማሩ ድርጅቶች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ሁኔታዎች በማሟላት መጫረታ የሚችሉ መሆኑን ይገልፃል።
1. በዘርፉ የተሰማሩ ድርጅቶች የታደሰ የንግድ ፈቃድ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው የሚያሳይ መረጃ /Tax Clearance/የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት እና የተጨማሪ እሴት ታክስ ሰርተፍኬት ማቅረብ አለባቸው።
2. የተለያዩ ቴክኒካል ሰነዶች እና ፋይናሺያል ሰነድ በተለያየ ፖስታ በማሸግ አንድ ላይ ከአንድ ኮፒ ጋር መቅረብ አለበት።
3. የጨረታ ሰነዱን ለመግዛት የማዛትት የማይለስ 250.00/ሁለት መቶ ሃምሳ ሺህ ብር/ በሲፒኦ ወይም በባንክ ጋራንቲ የኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጀስቲክ አገልግሎት ድርጅት በሚል ስም ባማሠራት ከጨረታ ፖስታው ጋር በማቅረብ መጫረት ይችላሉ።
4. የጨረታ ሰነዱን ለመግዛት የማይመለስ 250.00 /ሁለት መቶ ሃምሳ ብር/ በመክፈል ለገሀር በሚገኘው አዲሱ ህንፃ 3ኛ ፎቅ ፋይናስና አካውንትስ መምሪያ በመክፈል 10ኛ ፎቅ የጨረታ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ።
5. ጨረታው በኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርት ሎጀስቲክስ አገልግሎት ድርጅት አዲሱ ህንፃ 10ኛ ፎቅ ሰኔ 29ቀን 2015 ዓ.ም ከቀኑ በ8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ዕለት በ8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ፖስታው ይከፈታል።
6. ከጨረታ መክፈቻው ቀንና ሰዓት በኋላ ዘግይቶ የሚመጣ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት የለውም።
7. ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ስልክ ቁጥር፦ 011-554-9781/86
