Tender Detail

Tender Details

  • Deadline03 Aug 2023, 1:03 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Accounting & Auditing

የኔነህ ይልማ የቢዝነስ ልማትና ኢንቨስትመንት አማካሪ ድርጅት ከዋሊፍ ትራንስፖርት አ.ማ ጋር በመተባበር ድርጅቱ ይጠቀምባቸውም ግለሰቦች የነበሩ 33 ሱዚክ ድዛይነር ተሽከርካሪዎች በጨረታ ለመሸጥ ይፈልጋል።


1.በጨረታው መሳትፍ የሚፈልግ ማንኛውምግለሰብ/ ድርጅት በጨረታው የመሳተፍ መብቱ የተጠበቀ ነው።

2. ተጫራች የተሽከርካሪውን አይነት እና ዝርዝር መግለጫ ጨረታ ሰነድ ላይ ማግኘት ላይ ይችላሉ።

3.እያንዳዱ ተጫራች የማይመለስ ብር 500.00/አምስት መቶ ብር/ በመክፈል ስምን ስሙን እያስመዘገበ ከ ሰኔ 26/2015 ዓ.ም እስከ ሐምሌ 14 ቀን 2915 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡30 - 10:30 ሰዓት ከሰኞ እስከ ቅዳሜ ድረስ ብቻ የጨረታ ሰነድ መመሪያ እና የጨረታ ዋጋ ማቅረቢያ ቅፁን ተሽከርካሪዎች በሚገኙበት መጋዘን በር ላይ እየገዙ ተሽከርካሪዎች መጎብ ኘት ይችላሉ።

4.ማንኛውም ተጫራች የጨረታውን ማስከብሪያ ዋስትና ለእያንዳዱ ተሽከርካሪ 100,000/አንድ መቶ ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ተዛዝ ሲፒኦ በተጠቀሰው የድርጅቱ አድራሻ ስም በማሰራት ማስያዝ ይጠበቅበታል።

5. ማንኛውም ተጫራች የተሽከርካሪ ዋጋ የሞላበትን ገጽ ዋናውን ብቻ እና የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በአንድ ፖስታ ብቻ በጥንቃቄ በማሸግ ደበል አካባቢ አበሩስ ህንፃ ሶስተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 306 በሚገኘው የድርጅቱ ዋናው መስሪያ ቤት በኝባር በመቅረብ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ከሐምሌ 7ቀን 2015 ዓ.ም እስከ ሐምሌ 15 ቀን 2015 ዓ.ም ከጠእዋቱ 4፤00 ሰዓት ድረስ ብቻ ማስገባት ይጠበቅበታል።

6. የጨረታውን አሸናፊ ስም ዝርዝር የምናሳውቀው ሐምሌ 28ቀን 2015 ዓም ከቀኑ 5፡00 ሰዓት በድርጅቱ ዋናው መስሪያ ቤት ይሆናል። በጨረታው የተሸነፉ ሰዎች ወዲያውኑ ያስያዙት ሲፒኦ ተመላሽ ይሆናል።

7. ማናኛውም የጨረታ አሸናፊ የሆነው ግለሰብ ስሸናፊ መሆኑን ከተረጋገተበት ቀን አንስቶ ባሉት 10/አስር/ ተከታትይ ቀናት ውስጥ ማለትም እስከ ሐምሌ 28 ቀን 2015 ዓ.ም ቀሪውን ክፍያ ፈፅሞ ንብረቱን የማንሳት ግዴታ አለበት ከፊል ክፍያዎች ተቀባይነት አይኖራቸውም። በተጠቀሰው ጊዜ መክፈል ያልቻሉ ተጫራቾች ያስያዙትን ሲፒኦ ያጣሉ ድርጅቱ ሌሎች አማራጮችን የመውሰድ መብቱ የተጠበቀ ነው።

8. ድርጅቱ ከላይ የተቀመጡትን መስፈርቶች ሳያሟሉ ወይም ለቀረበው ጨረታ የተመጣጣኝ ዋጋ አልተሰጠም ብሎ ካመነ ከተጫራች የተሰጠውን ዋጋ ውድቅ የማድረግ መብቱ የተጨበቀ ነው።

9. የጨረታው አሸናፊ እሚሆን በተናጠል በተሰጣቸው የሰሌዳ ቁጥር ወይም መለያ ቁጥር መሰረትከፍተኛ ዋጋ ያቀረበ ተጫራች ይሆናል።

10. ተጫራቾች በፖስታቸው ላይ በግልፅ በሚታይ መልኩ ምስም ከነአያት ስልክ እዲሁም ፊርማ መፅሀፍ አለባቸው።

11. ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 09-73-42-42-24 ወይም07-13-48-76-76 በመደወል ማግኘት ይችላሉ

ተሽከርካሪዎች የሚገኙት መጋዘኖች አድራሻ ሜክሲኮ ወደሰጋተራ በሚወስደው መንገድ ላይ የውቤክ ህንጻ አለፍ ብሎ በተለምዶ የድሮ ሰንጋ ተራ ቶታል የነበረው ግቢውስጥ ይገኛል

የጨረታ ሰነድ ያልያዙ ማንኛውም ተጫራች መኪኖቹን ንብረት መጎብኘት አለባቸው።

Save Tender