የጉምሩክ ኮሚሽን ድግጅጋ ቅ/ጽ/ቤት በኮትሮባንድ የተያዙ የተለያዩ አልባሳት ኮንስትራክሽን ኤለኢክትሮኒክስ የቤት እቃ የቤት ማስዋቢያ ጫማዎች የጽዳት እቃ እና ልዩ ልዩ በግልጽ እና በሀራጅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
1.በግልጽ እና በሐራጅ ጨረታ በዘርፉ የፀና የንግድ ፈቃድ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት እና የዘመኑ ግብር የከፈለ ለመሆኑ ከገብር ሰብሳቢ መሥሪያ ቤት የተሰጠ ማርሰጃ ማቅረብ የሚችል እንዲሁም የነዋሪነት መታወቂያ ያለው ማንኛውም ኢትዮጵያዊ።
2. በሀራጅ ጨረታ ለመሳተፍ እቃውን ለመግዛት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና 50,000 /ሃምሳሺህ ር/ ሲ.ፒ.ኦ /CPO/ማቅረብ የሚችል።
3. ለገልፅ ጨረታ ለመሳተፍ ዕቃውን ለመግዛት የሚያቀርበው የመጫረቻ ዋጋ አምስት በመቶ /5%/ ሲ.ፒ.ኦ /CPO/ ማቅረብ የሚችል።
4.በሀራጅ ጨረታ ተጫራቾቹ የሚገዛበት መነሻ ዋጋ እራሱ ያቀርባል።
5. በግልፅ ጨረታ ቅ/ጽ/ቤቱ ካስቀመጠው መነሻ ዋጋ ተነስቶ ዋጋ በመሙላት በተጠቀሰው ሳጥን ውስጥ ማስገባት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።
6. ተጫራቾ በጨረታ አሸንፎ የገዛውን እቃዎች ወዲያውኑ ከፍሎ በ05 ቀን ውስጥ የሚረከብ መሆን አለበት።
7. እቃዎቹን አሸንፎ የገዛ ተጫራች የሚፈልግበትን ዋጋ ወዲያውኑ ከፍሎ በ᎔ ቀን ውስጥ ካልተረከበ ያስያዘው ሲ.ፒ.ኦ /CPO/ ለመንግስት ገቢ ይሆናል።
8. በጨረታው ያላሸነፉ ተጫራቾች ያስያዙት ሲ.ፒ.ኦ /CPO/ ወዲያውኑ ይመለሳል።
9. ማንኛው ተጫራች የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጅግጅጋ ቅርጫፍ ሲ.ፒ.ኦ /CPO/ አሰርቶ ማምጣት አለበት።
10. አሳማኝ የሆነ ምክኛት ከተገኘ እና በመ/ቤቱ ተቀባይነት ከላገኘ ጨረታውን መሰረዝ ይቻላል።
11. ማንኛውም ተጫራቾች እቃዎቹን ካሸነፉ ከጅግጅጋ ውጪ ለማጓጋኡዝ ቢፈልግ እደየ ቦታው እርቀት በቀን ገደብ መሸኛ ሲሰጣቸው ይችላል።
12 ተጫራቾች እዎቹን አሸንፎ ከተረከበ በኋላ መሽኛ ሳይዝ የትም ቦታ ቢያዝ መ/ቤቱ ኃላፊነቱን አይወስድም።
13. ተጫራቾች የሞሉትን የግልፅ ጨረታ ሰንድ በቀን 22/19/2015 ከጠዋቱ 2፤00 እስከ 3፡45 በጅግጅጋ ጉ/ኮ/ቅ/ጽ/ቤት ማሰገቢያ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል ጨረታው 3፡45 ተዘግቶ 22/10/2015 ከረፋዱ 4፡00 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ይሆናል።
14. የሀራጅ ጨረታ የሚካሄደው በቀን 22/10/2015 ከረፋዱ 4፡30 በቅ/ጽ/ቤቱ መሰብሰቢያ አዳራሽ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይሆናል።
N.B:- አሸናፊው ተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/15% አስራ አምስት ፐርሰንት የሚከፈል መሆኑን ይታወቃል/ ሳምፕል ሳያዩ የሚጫረቱ ተጫራች ቅ/ጽ/ቤቱ ሓላፊነቱን አይወስድ።
