Tender Detail

Tender Details

  • Deadline10 Jul 2023, 2:26 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Accounting & Auditing

እሳት ውሃ ስራዎች ኃ/የተ/የግ/ማህበር ጢስ ውሃ ስራዎች ኃ/የተ/የግ/ማህበር ከታች የተዘረዘሩትን እቃዎች በግልልፅ ጨረታ አወዳድሮ ከአቅራቢዎች መግዛት ይፈልጋል።


ተ.ቁ ሎት የእቃው ዓይነት የጨረታ ማስከበሪያ ማቅረቢያ ቀን
1 ሎት1 የተሽከርካሪና ማሽነሪ መለዋወጫ 100,000.00 በ30-45ቀን
2 ሎት 2 የተሽከርካሪና ማሽነሪ ጎማዎች 100,000.00 በ30-45 ቀን
3 ሎት 3 ዘይት ቅባት 100,000.00 በ30- 45 ቀን
4 ሎት 4 ሀንድ ፓምፕ 1000,000.00 በ30-60 ቀን

ስለዚህ ማንኛውም በዘርፉ የተሰማራ በጨረታው መሳተፍ የሚፈልግ አቅራቢ ድርጅት ዝርዝር የጨረታ ሰነዱን ከድርጅታችን ድህረ_ ገጽ WWW.TISISAAIL.COM ማግኘት ይችላሉ።

1. ተጫራቾች የዘመኑን ግብር ከፍለው የታደሰ የንግድ ፈቃድ የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት ተጨማሪ እሴት ታክስ እና TINሰርተፍኬት በዘርፉ ለመሰማራት የተሰጣቸውን ፈቃድ እና ተያያዥነት ያላቸውን የመልካም ስራ አፈፃፀም ማስረጃዎች ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።

2. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ21ኛው ቀን ከቀኑ 10፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን ከቀኑ 10፡30 ሰዐዐት በባህር ዳር ከተማ አባይ ማዶቴዲ የተሽከርካሪዎች ማሰልጠኛ ጎን በሚገኘው ዋናው መ/ቤት ተጫራቾች እና ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል ። የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ ቀን የስራ ቀን ካልሆነ ጨረታው የሚቀጥለው የሥራ ቅን በተመሣሣይ ሰዓት ተዘግቶ ይከፈታል።

3. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ከድርጅታችን ድህረ_ ገፅ WWW.TISISAAIL.COMማግኘት ይችላሉ።

4. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ በሰንጠረዡ የተመለከተውን ገንዘብ በCPOወይም ያለ ቅድመሂኔታ /Uncodtional Bank Gurantee/ማስያዝ አለባቸው።

5. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ የሚያወጡት ወጪ በተጫራቹ የሚሽፈን ይሆናል።

6. ተጫራቾች የዋጋ ማቅረቢያቸውን ኧና ቴክኒካል ሰነዳቸውን ለየብቻ በተለያየ ፖስታ ማቅረብ ይኖርባቸዋል ተጫራቾች ድርጅቶች ለሚያቀርቡት ዋጋ ለውያንዳዱ እቃ ነጠላ ዋጋ እና ጠቅላላ ዋጋ በትክክል ሞልተው በግልጽ ማስቀመጥ አለባቸው።

7.ይህ ጨረታ በኩባኛችን የግዥ መመሪያ ነሐሴ /2013/ መሰረት ተፈፃሚ ይሆናል።

8. ኩባኒያው በጨረታ ሰነዱ ላይ ከተገለፀው መጠን 20% ቢጨምር ወይም ቢቀንስ የጨረታ አሸናፊው ውል የመያዝ ግዴታ ይኖርበታል።

9. የጨረታው አሸናፊ አሸናፊነቱ በፅሁፍ ከተገለፀ ቀን ጀምሮ በ10 ቀናት ውስጥ የጠቅላላ ዋጋውን 10% የውል ማስከበሪያ ያለቅድመ ሁኔታ ለገዥ የሚከፈል  /Uncodtional Bank Gurantee/በማሰራት ውል የመያዝ ግዴታ ይኖርበታል።

10. የማቅረብ ግዴታ ከላይ በሰንጠረዡ ላይ በተገለፀው መሠረት መሆን አለበት። ተአቅራቢዎች ዋጋ ቢያንስ ለ90 ቀናት ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ፀንቶ መቆየት አለበት።

11. ኩባኒያው የተሻለ አማራጭ ካገኘ በዚህ ጨረታ አይገደድም ወይም ጨረታውን በሙሉ ሆነ በከፈል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

12. ማሳሰቢያ፦ ውድድሩ የሚካሄደው እንደው እንደ ኩባኛችን ፍላጎት በሎት ወይም በነጠላ ዋጋ መሠረ ሊሆን ይችላል።

Save Tender