Tender Detail

Tender Details

  • Deadline03 Jul 2023, 2:35 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Health Care, Medical Industry

ድርበር የለሽ የሀኪሞች ቡድን ወይም Miedical Sans Holland /MSF-H/ የድርጅትቱ ንብረት የሆኑ ያገለገሉ የተለያዩ የብረት ውጤቶችን /Scrap Metals/ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።


1. ተጫራቾች ያገለገሉ የተለያዩ የብረታ ብረት ውጤቶችን /Scrap Mateals/ ዝርዝር ዓይነት ብዛት የጨረታ ሰነድና መመሪያ እንዲሁም የጨረታ ዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ የማይመለስ ብር 300.00 /ሶስት መቶ ብር/ እየከፈሉ አዲስ ኮሌጅ አጠገብ ከሚገኘው ዋና መስሪያ ቤት የሎጀስቲክ ቢሮ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከሰኔ 23 ቀን 2015ዓም ድረስ መግዛት ይችላሉ።

2. ተጫራቾች ለሽያጭ የተዘጋጁትን ያገለገሉ የብረታ ብረት ውጤቶችን /Scrap Mateals/ጃክሮ ዓእምሮ ጋራዥ ወረድ ብሎ ከሚገኘው የድርጅቱ መጋዘን በመሄድ /በመገኘት ብስራ ሰዓት ከቀኑ 8፡00 እስከ ቀኑ 10፡30 ጨረታው ከወጣበት ቀዕን ጀምሮ መመልከት ይቻላል።

3. ተጫራቾች ያገለገሉ የተለያዩ የብረታ ብረት ውጤቶች /Scrap Mateals/ዝርዝር የያዘው ሰነድ ላይ ተጫራቾች የሰጠው ዋጋ በሚለው በአምድ /COLUMN/ሥርየሚገዝይበተን ዋጋ በአሃዝ በፊደክል ያለ ስርዝ ድልዝ ገልፀው በታሸገ ኤንቨሎፕ በድርጅቱ እንግዳ መቀበያ /Reception/ክፍል በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ እስከ አእኔ 27 2015 ዓ.ም ከጠዋት 4፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት አለባቸው።የሚሰጡት ዋጋ ላይ ስርዝ ድልዝ ካለ ከጎኑ በተጫራቹ መፈረም አለበት።

4. የጨረታ መነሻ ዋጋ ፦ በኪሎ ብር 65.00 /ስልሳ አምስት ብር/ የመነሻ ዋጋ ሆኖ ተጫራቾች የሚገዙበት የአንዱ ኪሎ ዋጋ በግልፅ በመፃፍ በታሸገ ኤንቨሎፕ ማስገባት የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን።

5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋጋ 572,0000 /አምስት መቶ ሰባሁለት ሺH/ በኤም ኤስ ኤፍ ሆላድ ስም በተዘጋጀው በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ማቅረብ አለባቸው። አሸናፊ ለሆኑት የጨረታ ማስከበሪያ በሚከፍሉት ዋጋ ውስጥ የሚታሰብ ይሆናል። ለተሸነፉት ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በሚከፍሉት ዋጋ ውስጥ የሚታሰብ ይሆናል። ለተሸነፉ ተጫራቾች ግምገማ ውጤት ከተገለፀ በኋላ ሲፒኦ ተመላሽ ይደረጋል።

6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ከሞሉ በኋልዝ ኦርጅናል ሰነዱን እና ሲ.ፒ.ኦ ተመላሽ ይደረጋል። በሌላ ሁለተኛ ፖስታ  በማሸግ በመፈረምና የድርጅቱን ማህተም በማድረግ በሰነዱ ከተጠቀሰው ጊዜ በፊት ወደጨረታ ሳጥኑ ማስገባት አለባቸው።

7.ተጫራቾች በጨረታ ሠነዱ ላይ ስማቸውንና ፊርማቸውን እንዲሁም የስልክ ቁጥራቸውን መፃፍ አለባቸው።

8. ፖስታ /ኤንቨሎፑ/ ላይ ስማቸውንና ያገለገሉ የተለያዩ የብረታ ብረት ውቴቶችን  /Scrap Mateals/ ጨረታ በሚል መፃፍ አለባቸው።

9. በጨረታ ሠነዱ ላይ ተጫራቹ ወይም የሕጋዊ ወኪሉ ፊርማ ከሌለበት ዋጋ አይኖረውም።

10. ከጨረታው ሳጥን መዝጊያ ሰዓት በኋላ የሚደርሱት የመጫረቻ ሠነዶች ተቀባይነት አይኖራቸውም።

11. ጨረታው ሰኔ 27 ቀን 2015 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚያኑ ቀን ከጠዋቱ በ4፡30ሰዓት በድርጅቱ መሰብሰቢያ አዳራሽተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።

12. የጨረታው አሸናፊ የሚሆነው ከፍተኛ ዋጋ ያቀረበ ይሆናል የጨረታው አሸናፊ ያሸነፈውን ንብረት በሙሉ በሁለት ሳምንት ጊዜ ውስጥ በራሱ ተሽከርካሪና ማስጫኛ አጠቃሎ የማሳት ግዴታ አለበት።

13. ተጫራቾች ያሸነፈውን ንብረት በራሱ ተሽከርካሪ ማስጫኛና የብረት ክብደት ማስመዘኛ ወጪን አጠቃሎ በመሸፈን የሚያነሳ ሲሆን በማያነሳበት ወይም በሚያነሳበት ወቅት በሰውም ሆነ በንብረት ላይ ከጥንቃቄ ጉለት ለሚደርስ ማንኛውም ጉዳት ሙሉ ኃላፊነት ይወሰዳል።

14. አንድ ተጫራች ሌላው በሰጠው ዋጋ ተተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም።

15. ሁለት ተጫራች ለአንድ እቃ እኩል ዋጋ በመስጠት አሸናፊው ቢሆኑ እደገና በማወዳደር አሸናፊው ይለያል። 

16. ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ተካፋይ ሆኖ ጨረታው ከተፈተ በኋላ የሰጠውን ዋጋ መለወጥ ወይም ማሻሻል አይችልም።

17. ተጫራቾች ጨረታው ከተክፈተ በሃኡላ ከውድድሩ ሊወጡ አይችሉም።

18. ተጫራቾች አሸናፊ መሆናቸው ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በጨራው ያሸነፉትን ዕቃ ዋጋ በ5 ቀናት ከፍለው በከፈሉ በ10 ቀን ውስጥ ደግሞ ንብረቱን የማንሳት ግዴታ አለባቸው።

19. በጨረታ አሸንፈው ከፍለው ለማይወስዱ ተጫራቾች ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ለድርጅቱ ገቢ ይሆናል። በተጨማሪም በተጠቀሰው የጊዜ ገደብ ውስጥ ብረቶች የማይረከቡ  ከሆነ ድርጅቱ በሌላ በማንኛውም መልኩ ንብረቶች ማስወገድ መብቱ የተጠበቀ ነው።

20. ተጫራቾች የሙስና የማጭበርበር ድርጊት የማይፈፀሙ ስለሆናቸው ከዚህ መምሪያ ጋር ተያይዞ በቀረበው ቅጽ ላይ ሞልተው ከፈረሙ በኋላ ኮፒ በማድረግ ከነኮፒው ከዋጋ ማቅረቢያ ቅጹ ጋር በፖስታ በማሸግ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።

21. ተጫራቾች በሚሰጡት ዋጋ ላይ የዋጋ ማስተካከያ ወይም ስርዝ ድልዝ ካደረጉ በተስተካከለው ፊት ለፊት መፈርም አለባቸው።

በተጨማሪም የመጨረሽቻ ዋጋ በእርሳስ መሙላት አይቻልም።

22. የጨረታ ሰነዱን ያልገዛ ተጫራች በጨረታው ሊሳተፍ አይችልም። በኮፒው የጨረታ ሰነድ መጠቀም አይቻልም።

23. ለተጨማሪ ማብራሪያ ስልክ ቁጥር፦ 011 661 0011 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።

24. አንድ ተጫራች ለቁሳቁሶች ከአንድ ጊዜ በላይ የጨረታ ሠነዱ ማስገባት አይቻልም።

25. ድርጅቱ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

Save Tender