የሐዋሳ ጉምሩክ ኮሚስኝ ቅ/ጽ/ቤት በሀዋሳ ማዕከላዊ መጋዘን እና በኮንሶ ጉምሩክ መቆጣጠሪያ ጣቢያ መጋዘን የተተወና ተወርሰው የሚገኙ የመገናኛ መሣሪያዎች የኤሌክቲክ እቃዎች አልባሳት ጨረቃጨርቅ የቤት የቢሮ መገልገያ እቃዎች የሞተር ሳይክል መለዋወጫ የመኪና መለዋወጫ የመዋቢያ የንፅህና መጠበቂያ ያገለገሉ ሞተር ሳክሎች የተለያዩ ዓይነት ውስኪዎችና ያገለገሉ ባዶ ጄሬክኪና ባሉበት ሁኔታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
1.የጨረታ ተሳታፊ ተጫራቾች በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያለው /ያላት የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ ከግብር ሰብሳቢ መ/ቤት የተሰጠ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ ግምታዊ ዋጋው ከብር 500 ሺህ ብር በታች የሆነን ማንኛውም ዕቃ ለመግዛት የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፊኬት ማቅረብ አያስፈልግም።
2. ማንኛውም ተጫራች የጨረታውን ሰነድ በጨረታ ማስታወቂያ ላይ ከተገለፀ ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት ከሰኞ እስከ ዓርብ ጠዋት ከ2፡00 ሰዓት እስከ 6፡00 ሰዓት ከ7፡00 ሰዓት እስከ 11፡00 ሰዓት ቅዳሜ ከ2፡00 ሰዓት እስከ 6፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ የማይመለስ ብር 100.00 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል በቅ/ጽ/ቤቱ ከገቢ ሂሳብና ዋስትና አስተዳደር ቢሮ መውሰድ ይቻላሉ።
3. ማናኛውም የግልፅ ጨረታ ተጫራች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን የሚጫረተትን ጠቅላላ ዋጋ 5% /አምስት በመቶ/ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የተመሰከረለት CPO የጨረታ ሰነድ እና አጠቃላይ መረጃ ዎችን ጨረታ ከመከፈቱ በፊት በጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
4. ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የጨረታ ሰነዱ በመግዛት እስከ 7ኛው /ሠባተኛ/ ቀን የንብረቶቹን ናሙና በመደበኛ የስራ ሰዓይ በሀዋሳ ማዕከላዊ መጋዘን ማየት የሚችሉ ሲሆን የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን በ8ኛው /ስምንተኛው/ቀን በግልፅ ጨረታ 4፡00 ሰዓት የጨረታ ሳጥኑ ታሽጎ በ4፡05 ሰዓት ማእከላዊ መጋዘን ይካሄዳል ነገርኝ ጨረታው በበዓል ወይም እሁድ ቀን የሚውል ከሆነ Xእረታ የሚካሄደው በተመሳስይ ሰዓት የሚቀጥለው የስራ ቀናት ይሆእናል።
5. ማንናውም የግልጽ ጨረታ ተጫራቾች የሚወዳደሩባቸውን ዕቃዎች ዋጋከጨረታ ሰነዱ ተያይዞ በቀረበው ቅጽ ላይ ተጫራቹ ያቀረበው ዋጋ በሚለው ርዕስ ስር በተሰጠው ክፍት ቦታ ከነቫት በሚለው ወይም መስመር በጨረታ ሰነዱ ግልጽ በምሆነ መልክ በመሙላት በታሸገ ኤንቨሎፕ ወይም ፓስታ መቅረብ አለባቸው። ከዚህ ውጭ ብሌላ ሰነድ ተሞልቶ የሚቀርብን ዋጋ ቅ/ጽ//ቤቱ ለመቀበል አይገደድም።
6. ማናኛውም ግልፅ ጨረታ ተጫራቾች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ በጨረታ ላይ የሰጠውን ዋጋና መግለጭዐ መለወጥ እና ማሻሻል አይቻልም።
7. ማንኛውም ተጫራች የሰውን መወዳደሪያ ዋጋ የጨረታ ሂደት ተጠናቆ ቅ/ጽ/ቤቱ የጨረታውን ዌት እስከሚያሳውቅ ድረስ ፅንቶ ይቆያል።
8. ማንኛውም ተጫራች ጨረታው ከተከፈት በኋላ እራሱን ከጨረታ ውድር ማግለለ አይቻልም።
9. በጨረታ ለተሸናፉ ተጫራቾች ያስያዙት cpo በሶስት የስራ ቀናት ውስጥ የሚመለስላቸው ሲሆን አሸናፊው ያስያዘው ዋስትና ኝ ከሽያጭ ጋር የሚታሰብለት ይሆናል።
10. ተጫራቾች ዕቃውን ሳያዩ ዋጋ ቢሰጡ ችግር ቢፈጠር ቅ/ጽ/ቤቱ ተጠያቂ አይሆንም።
11. ለጨረታው የቀረበ ዕቃ ሽያጭ የሚፈፀመው ባለበት ሁኔታ ነው።
12 አሸናፊው ተጫራች ማሸነፉን በውስጥ ማስታወቂአይ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ 05/አምስት/ ቀናት ውስጥ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ በማረግ ዕቃዎችን ማሳየት ይኖርባቸዋል ። ይህንን ባያደርጉ ጨረታ ተጫርተው ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለቅ/ታ/ቤቱ ገቢ ተደርጎ ዕቃው በድጋሚ በጨረታ ላይ ይወጣል።
13. ቅ/ጽ/ቤቱ ጨረታው በክፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱየተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር፦ 046 212 5396
