የሸዋ ሮቢት ተሃ/ልማት/መ/ቤት የህግ ታራሚዎች ቀለብ የወጥ ማጣፈጫ ለመግዛት ይፈልጋል
1. የዘመኑ ህጋዊ የታደሰ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ።
2. ከሚያቀርቡት እቃ ወይም አገልግሎት ጋር በሙያው ዘርፍ የተመዘገቡ።
3. ከገንዘብ ሚንስቴር አቅራቢዎች የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል በጨረታው መሳተፍ ይችላል።
4. የግብይት መጠኑ ከ200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ለሚሆኑ ግዥ ከገቢዎች ሚንስቴር የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ ለመሆኑ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል እና ከገቢዎች ግብር መክፈሉን ማረጋገጫ ደብዳቤ ማቅረብ የሚችል መሆን አለበት።
5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 50.00 /ሃምሳ ብር/ በመክፈል የጨረታ ሠነዱን ሸዋሮቢት ተሃ/ልማት ማረ/ቤት ማዕከል ቢሮ ቁጥር 09 መግዛት ይችላሉ።
6. ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት ሠነድ ማስያዝ የሚገባቸው የጨረታ ማስከበሪያ ገንዘብ እደሚከተለው መሆኑ ማወቅ ይኖርባቸዋል።የተለያዩ የህግ ታራሚዎች ቀለብ የወጥ ማጣፈጫ ግዝ ብር 15,000.00 በባንክ በተመሰከረለት ሰርቲፋይድ ቼክ /ሲፒኦ/ ጨረታው ከመከፈቱ በፊት በጨረታው ማስከበሪያ ማስያዝ ይኖርበታል።
ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው የተለያዩ የህግ ታራሚዎች እና ቀለብ የወጥ ማጣፈጫ በተጥየቁት ላይ ናሙና ማቅረብ ይኖርባቸዋል አስፈላጊ መረጃዎችን ሁሉ በምካተት ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ16 ተክታትይ ቀናት በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ የጨረታ ሠነዱን ዋናውንና ኮፒውን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
1. ማንኛውም ተጫራች ናሙና ማስያዝ ያለበት ጨረታው ከመከፈቱ በፊት አንድ ሰአት ቀደም ብሎ መሆን አለበት።
2.የጨረታ ማስታወቂያ በወጣ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት ተዘግቶ በዚያኑ እለት 4፡00 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
3. የጨረታ አሸናፊ ሆነነው የተመረጡት ድርጅቶች የጨረታ ውጤት ከተገለፀላቸው ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ ቀናት ውስጥ የማረሚያቤቱ ሂሳብ ክፍል በመቅረብ ያሸነፉበት ዋጋ 10% የመልካምሥራ አፈፃፀም ማስያዝ ውል መፈፀም ይገባቸዋል።
4. ማረ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
5. ተጨማሪ ማብራሪያ በያስፈልግው ስልክ ቁጥሮች 033 664 0749 033 664 0765 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ
ፋክስ 033 664 0753
ማሳሰቢያ ፦ የዚህ ጨረታ ማስታወቂያ መክፈቻው ቀን በዓል ቀ ቅዳሜና እሁድ ላይ ከዋለ የሚቀጥለው የስራ ቀን ጨረታው ተዘግቶ ይከፈታል።
