በደ/ብ/ብ ሕ/ክ/መ/ማ/ቤቶች አስር ኮሚሽን የባስኬቶ ልዩ ወረዳ ላስካ ማረሚያ ተቋም በ2016 በጀት ዓመት ለህግ ታራሚዎች ምግብ እህል እና ቅ/ቅመም የቢሮ ዕቃዎች በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
1.ለምግብ የሚውል ቀለብ የተበጠረ ቀጭ ቀጭ የሌለው ሰርገ ኛ ጤፍ/ነጭ በቆሎ አተር ባቄላና ስንዴ ።
2. ለምግብ ማጣፈጫ የሚውል ቅመማ ቅመም የተፈጨ በርበሬ የተፈጨ እርድ ነጭ ሽንኩርት ቀይ ሽንኩርት ዝንጅብል ጨው ጥቁር አዝሙድ ነጭ አዝሙድ አብሽ ስኳር ሻቅጠል እና የምግብ ዘይት
3. የቢሮ አላቂ ዕቃዎች
4. የምግብ ማብሰያ የሚውል ማገዶ እንጨት ከሐምሌ 1/2016እስከ ሰኔ 30/2016 ዓ.ም ድረስ በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
ስለዚህ ከዚህ በላይ የተዘረዘሩት የምግብ እህሎችን ቅ/ቅመምና የቢሮ ዕቃዎች በአቅራቢነት በጨረታው ላይ መሳተፍ የሚፈልጉ ድርጅቶች የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋ።
1. ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያለው/ያላት በአቅራቢዎች ዝርዝር የተመደቡ።
2. የዘመኑ ግብር ከፍሎ ያጠናቀቀ/ች ፍቃዳቸውን ያሳደሱና የአቅራቢነት የምስክር ወረቅት ያለው/ት
3. የተዘረዘሩት እህሎችን በጨረታው ለመወዳደር ቫት /VAT/ተመዝጋቢ የሆነ።
4. አሸናፊው ማንኛውም ወጪ በራሱ ሸፎ ዕቃውን ለላሰካ ማረሚያ ተቋም ቅጥር ግቢውስጥ ማቅረብ የሚችል።
5. የጨረታ ማስከበሪያው 30,000.00 /ሰላሳሺህ ብር/ በጥሬ ገንዘብ በኤትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ እውቅና ያለው ቼክ ሌተር ኦፍ ክሬዲት /CPO/ ማቅረብ የሚችል።
6. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን 2/10/2015 ዓ.ም ጀመሮ ባሉት ተከታታይ 15 ቀናት ውስጥ የሚወዳደሩበትን የጨረታ ሰነድ ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ የማይመለስ ብር በመክፈል ሰነዱ ከግዥ ፋይናስ ቢሮ ቁጥር 5 መጥተው መግዛት እደምትችሉ እንገልፃለን።
7. ተጫራቾች የዋጋ መወዳደሪያ ሂሳባቸው የሞሉት ሰነድ በስማቸው ፊርማ የድርጅቱ ማህተም በማድረግ ፍቃዳቸውንና ሌሎች ማበረታቻ የተሰጠው የምስጋና ምስክር ወረቀትና ኦርጅናል ኦርጅናል የማይመለስ ፎቶ ኮፒ በመያዝ 20/10/2015 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡30 ሰዓት እስከ 4፡30 ሰዓት ድረስ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
8. ጨረታው በ20/10/2015 ከጠዋቱ 4፡30 ታሽጎ በ4፡40 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተእገኙበት ይከፈታል 15ኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ውስጥ በተመሳሳይ ሰዓት የጨረታ ሂደት ይፈፀማል።
9. ተቋሙ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታው በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
10. ተቋሙ ከአሸናፊ ግዥ ኤጀንሲ በሚያስተካክለው የዋጋ ማስተካከያ መሠረት የዋጋ ማሻሻያ ተደርጎ ውሉ ይታደሳል።
ማሳሰቢያ፦ በሥራ ዕድል ፈጠራ የተደራጁ ህጋዊ መስፈርቶች ያሟሉ ማህበር እናበረታትለን።
ስልክ ቁትር፤፟ 0916 732364 ፋክስ፦ 46240073 ፖ.ሣ.ቁጥር 21
