Tender Detail

Tender Details

  • Deadline01 Jul 2023, 4:14 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Accounting & Auditing

በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ባህል ትሩዝምና ቢሮ በሎካ አባያ ወረዳ ሎካ አባያ ብሔራዊ ፓርክ በ2015 በጀት ዓመት ሊያሰራ ያቀደውን የሳፋሪ ሎጅ ግንባታ ሥራዎች ተጫራቾችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።


1.. derejacewn GC-5/Bc-5 እና ከዚያም በላይ የሆኑ የስራ ተጫራቾች የ2015 ዓመት የንግድ ፈቃዳእውን ያሳደሰ የዘመኑ ግብር የጅጀፈሉ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ ኮንስትራክሽን ሚንስቴር ወይም አግባብነት ካለው የመንግስት ተቋም የታደሰ የብቃት ማረጋገጫ ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።

2. አስፈላጊውን የግንባታ ዕቃዎች የሥራ መሳሪያዎች እና ሌሎች ሀብቶች በጋልቸው አቅርበው ግንባታውን መስራትና ማጠናቀቅ አለባቸው።

3. በሲዳማ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ውስጥ ፕሮጀክቶችን ሰርቶ ለማስረከብ ከአሠሪ እና ከሚመለከታቸው ተቋማት ጋር ህጋዊ ውል ገብተው እስራ ወቅት ከአሰሪ መስሪያ ቤት ወይም ከአማካሪ መሥሪያ ቤት ማንኛውም ዓይነት የሥራ አፈፃፀም ማስጠንቀቂያ የተሰጣቸው ስራ ተቋራጮች የጨረታ ሰነድ መግዛት ሆነ  መወዳደር አይችሉም።

4. በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በዋናው ውል ስምምነት ገብተው ሶስትና ከዚያም በላይ ስራ ጀምረው ያላጠናቀቁ /ያልጨረሱ/  ተቋራጮች ጨረታውን መግዛት ሆነ መወዳደር አይችሉም።

5. የስራ ተቋራጮች ለውድድር  ያቀረቡትን ብቃት /ቴክኒክ/ መወዳደሪያ ሰነዶች ዋና /ኦርጅናል/ ሲጠይቁ አቅርበው ማመሳከር አለባቸው ይህ ተጣርቶ ኮፒእ ከዋናው ጋር ተመሳክሮ ትክክለኛ ካልሆነ ተቋራጩ ከውድድሩ ውጭ ይሆናል።

6. የጨረታ ማስከበሪያው /bid security/ብር 90,000.00 /ዘጠና ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ ዋስትና /BANK GAURNITEE/  ወይም ክፍያ ማዛዣ /CPO/ ከመጫረቻ ሰነድ ማቅረብ የሚችሉ።

7. የሥራ ተቋራጮች በተጫራቾች መመሪያ  መሠረት ህጋዊ ፈቃዳቸውንና ተ.ዕ.ታ /vat/ የተመዘገቡበት ሠርተፍኬትና ታክስ ክሊራንስ በማቅረብ የጨረታ ዶክመንቶችን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን አንስቶ ለ21 /ለሃያ አንድ ቀናት/ የማይመለስ ብር 400 /አራት መቶ ብር/ በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በህል፣ቱሪዝምና ስፓርት ቢሮ ግዥ ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት በመክፈል  ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ።

8. የስራ ተቋራጮች ከጨረታው መዝጊያ ቀን በፊት የግንባታ ቦታ በራሳቸው ወጪ አይተው ማረጋገጥ አለባቸው።

9. የጨረታው ሰነድ በተጫራቾች መመሪያ መሠረት ተሞልቶ የጨረታ ማስከበሪያ /bid security/ፋይናሽያል አንድ ዋና /ኦርጅናል እና ሁለት ኮፒዎችን እንዲሁም ቴክኒካል አንድ ዋና /ኦርጅናል/ እና ሁለት ኮፒ ሰነዶች በታሸገ ኤንቨሎፕ በሰም ለየብቻቸው ታሽጎ በአንድ ትልቅ ፓስታ ውስጥ ተከተውና  በሁለም ዶክመንት ላይ ስማና አድራሻ በመፃፍ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀብ አንስቶ በ22ቀን ከጠዋቱ 4፤00 ሰዓት እስከ 6፡00 ሰዓት በሲዳማ ብሔራዊ ክልልላዊ መንግስት ባህል ቱሪዝምና ስፓርት ቢሮግ/ፋ/ን/አ ዳይሬክቶሬት ለዙሁ አገልግሎት በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል። የጨረታ ማስከበሪያው ከቴክኒካል ሰነድ ጋር አብሮ  መታሽግ አለበት ።

10.ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከላይ በተራ ቁጥር 9 ላይ በተገለፀው ቦታ ከቀኑ 6፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ ከቀኑ 8፤00 ሰዓት ላይ ይከፈታል።ተጫራቾች አለመገኘት ጨረታው ካለመከፈት አያግደውም።

11. የአሠሪ መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ወይም በሙሉ ተመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

12አሸናፊው ተጫራች የጨረታ ሰነዱ ላይ በተጠቀሰው  መሰረት ለቅድመ ክፍያ በእሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ ባንክ ዋስትና ማቅረብ ይኖርበታል።

13. የጨረታ መዝጊያቀን የሥራ ቀን ላይ ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከላይ በተገለፀው ቦታና ሰዓት ይሆናል

 

Save Tender