ገዳ ትራንስፖርት እና ሎጀስቲክ አ.ማ የተለያዩ Sitrak ደረቅ ጭነት ተሽከርካሪ መለዋእጫዎች ከክምችት ያላቸውን እና በዘርፉ ከተሰማሩ ድርጅቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል ስለሆነም በጨረታው መወዳደር የምትፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተመለከቱትን መስፈርቶች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለ።
ገዳ ትራንስፖርት እና ሎጀስቲክ አ.ማ የተለያዩ Sitrak ደረቅ ጭነት ተሽከርካሪ መለዋእጫዎች ከክምችት ያላቸውን እና በዘርፉ ከተሰማሩ ድርጅቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል ስለሆነም በጨረታው መወዳደር የምትፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተመለከቱትን መስፈርቶች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለ።
1.በዘርፉ የተሰማሩ የዘመኑ ግብር የከፈሉ እና የታደሰ ንግድ ፍቃድ እዲሁም ንግድ ምዝገባ ምስክር እና አስፈላጊውን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
2. ማንኛውም ተወዳድሪ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 16 ቀን አየር ላይ የሚውል ሲሆን እንጋተራ ንግድ ስራ ኪሌጅ ለፊት ቢፍቱ አዱኛ ህንጻ 12ኛ ፎቅ ከጠዋቱ 2፡30 ሰዓት እስከ 11፡00 ሰዓት በመምጣት የማይመለስ 200 /ሁለት መቶ / ብር በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መግዛት መወዳደር ይችላሉ።
3. ማንኛውም ተጫራች በገዛው የጨረታ ሰነድ ላይ ከብ ማህተም በማድረግ እና በመፈርም በታሸገ ፓስታ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የሚወዳደሩት ጠቅላላ ዋጋ 2% በሲፒኦ ወይም በሁኔታላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማቅረብ ያለባቸው ሲሆን የሞሉትን ጨረታ ሰነድ ፋይናሺያል እና ቴክኒካል ሰነድ ኦርጅናል እና ፎቶ ኮፒ እንዲሁም ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በተለያዩ ፓስታ በማሸግ ማቅረብ አለባቸው።
5.አሸናፊ ተጫራቾች አሽናፊነታቸው ከተረጋገጠ ቀን ጀምሮ ባሉት 5 ተከታታይ ቀናት የዋጋውን ውል ማስከበሪያ 10% ባማስያዝ ውል መፈረም ይኖርባቸዋል።
6. ተጫራቾች በሚያቀርቡት ዋጋ የጨረታ መግቢያ ሰዓት ከተጠናቀቀ በሁኋላ ማሻሻያ ማድረግ እና እራሳቸውን ከጨረታ ማለል አይቻልም።
7. በሌላ ተጫራች ላይ ተንተርሶ ዋጋ መስጠት አይቻልም።
8. በጨረታ ሰነዱላይ የተሰረዘ እና የተደለዘ ሆኖ ለመለየት የሚያስቸግር ዋጋ ተቀባይነት አይኖረውም።
9. ለተሸናፊ ተጫራቾች ጋር ውል እደተፈፀመ ተመላሽ ይሆናል።
10. ጨረታው የሚከፈትበት ቀን የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 16ቀን አየር ላይ የሚውል ሆኖ በ16ኛው ቀን በ8፡00ሰዓት ተዘግቶ በዛው እለት 8፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች እና ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ይሆናል።
11. የጨረታ መክፈቻ ቀናት ቅዳሜ እና እሁድ እንዲሁም በበዓላት ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል።
12. ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውብ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
