Tender Detail

Tender Details

  • Deadline13 Jun 2023, 4:31 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Accounting & Auditing

ቡና ባንክ አ.ማ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ በወጣው መመሪያ ቁጥር FIS/01/2016 መሰረት የውጭ ሀገር ዜኘት ካላቸ ውትውልድ ኢትዮጵያዊያን ባለአክሲዮኖች የተረከባቸውን በቁጥር 6,956 የሆኑ አክሲዮን ዋጋ ብር 100 ሆኖ ጠቅላላ ዋጋቸው ብር 695,600.00 የሚያወጡ አክሲዮኖችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።


  ቡና ባንክ አ.ማ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ በወጣው መመሪያ ቁጥር FIS/01/2016 መሰረት የውጭ ሀገር ዜኘት ካላቸ ውትውልድ ኢትዮጵያዊያን ባለአክሲዮኖች የተረከባቸውን በቁጥር 6,956 የሆኑ አክሲዮን ዋጋ ብር 100 ሆኖ ጠቅላላ ዋጋቸው ብር 695,600.00 የሚያወጡ አክሲዮኖችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

በመሆኑም የአንድ አክሲዮን የጨረታ መነሻ ዋጋ ብር 100.00 ሲሆን ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟላ ማንኛውም ትየጫራች በጨረታ ለመሳተፍ የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን።

1. ኢትዮጵያዊ ዜኘት ያለው ግለሰብ ወይም ሙሉ በሙሉ ዜኘት ባላቸው አክሲዮኖች የተያዙ ድርጅቶች በጨረታ መሳተፍ ይችላሉ።

2. ተጫራቾች ማንነታቸውን የሚያረጋግጥ የታደሰ የቀበሌ መታወቂያ የታደሰ መንጃፍቃድ ወይም ፓስፖርት ዋናውንና ፎቶ ኮፒ ወይም ተጫራቾች ድርጅቶች ከሆኑ ድርጅቱ በሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ጽ/ቤት የፀደቀ የመምስረቻ ጽሁፍ እና የመተዳደሪያ ደብ ውይም ሌላ ተቀባይነት ማስረጃ ዋናውንና ኮፒውን አያይዞ ማቅረብ አለባቸው።

3. ተጫራቾች አንዱን አክሲዮን የሚጫረቱበትን ዋጋ በመግለፅ መግዛት የሚፈልጉን ጠቅላላ የአክሲዮን ዋጋ 1/4ኛ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ የተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ አያይዘው ማቅረብ አለባቸው የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ሳይያያዝ የሚቀርብ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት አይኖረውም።

4. ተጫራቾች መግዛት የሚችሉት አነስተኛ የአክሲዮን ብዛት በቁጥር 500 እና የገንዘብ መጠኑ ደግሞ ብር 50,000 ሀምሳ ሺህ/ ሲሆን ከዚህ በታች የሆኖ አክሲዮኖች ለመግዛት የሚቀርብ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት አይኖረውም።

5. አክሲዮኖች የሚሸጡት በተጫራቾች የሚሰጠውን ዋጋ በማወዳደር ሲሆን የተሻለ ዋጋ የሚሰጡ ተጫራቾች ለመግዛት በገለጹት ዋጋ እና የተጠየቁትን አክሲዮን ብዛት ልክ በቅደም ተከተል ቅድሚያ ይሰጣል ። ተጫራቾች ተወዳድረው የጨረታውን አሸናፊ መሆናቸው በባኩ ሲገለጽላቸው የተሻለ ዋጋ የሰጠ ተወዳዳሪ የተረፈ አክሲዮኖች ባቀረበው ዋጋ የመግዛት ግዴታ አለባቸው።

6. ከአንድ በላይ ተጫራቾች ተመሳሳይ ዋጋ ቢሰጡ  እና ተራፉኢ አክሲዮኖች ሁለቱ ተጫራቾች ከጠየቁት የአክሲዮን ብዛት ቢያንሱ ቀሪዎቹ አክሲዮኖች ሁለት ተጫራቾች ከጠየቁት የአክሲዮን ብዝት ቀሪዮቹ አክሲዮን ተመሳሳይ ዋጋ ለሰጡ ተጫራቾች እኩል ይከፈላል።

7. ተጫራቾች ሌሎች ባቀረቡት ዋጋ ላይ ተመስርተው ዋጋ ማቅረብ አይቻልም።

8. የጨረታው አሸናፊዎች ያሸነፉበትን ጠቅላላ ዋጋ የጨረታ አሸናፊነታቸው በተገለፀላቸው በ15 ቀን /በአስራ አምስት ቀናት/ ጊዜ ውስጥ ለባንኩ ግቢ ማድረግ ይኖርባቸዋል። የጨረታው አሸናፊ በዚሁ ጊዜ ውስጥ ያሸነፉበትን ጠቅላላ ዋጋ ለባንኩ ገቢ ካ፤አደረጉ ጨረታው ተስርዞ ለጨረታ ማስክበሪያው ያስያዙት ሲ.ፒ.ኦ ለባንኩ ገቢ ይሆናል።

9. ለጨረታ የቀረቡት አክሲዮኖች በሙሉ ባሸናፊዎች ከተገዙ በኋላ በጨረታ ለተሸነፉት ተጫራቾች የጨረታ ውጤት እደታወቀ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት ሲ.ፒ.ኦ ይመለስላቸዋል።

10. ከላይ የተገለፁትን የሚያሟል ተጫራች የጨረታው የተዘጋጀውን ዋጋ ማቅረቢያ ቅፅ አስከ ሰኔ 07ቀን 2015 ዓ.ም ከጠዋቱ 4 ሰዓት ድረስ በስራ ሰዓት ቦሌ  ሩዋንዳ መዞሪያ በሚገኘው የባንኩ ዋና መስሪያ ቤት ህንፃ 4ኛ ፎቅ ፋይናስ ዳይሬክቶሬት ቀርበው በመውሰድ  እና በመሙላት በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ አሽገው ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።

11. ጨረታው ሰኔ 07ቀን 2015 ዓ.ም ከጠዋቱ 4ሰዓት ላይ ተዘግቶ በእለቱ 4፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው እንዲሁም የሚመለከታቸው ታዛቢዎች በተገኙበት ቦሌ ሩዋንዳ መዞሪያ በሚገኘው የባንኩ ዋና መስሪያ ቤት ህንፃ 4ኛ ፎቅ ላይ ይከፈታል።

12. በሌሎች ህጊችና በኤትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ መመሪያዎች የተደነገጉ ደንቦች በዚህ ጨረታ ላይ ተፈፃሚነት አላቸው።

13 ባንኩ ጨረታው በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

                                         ተጨማሪ ማብራሪያ ቢያስፈልግም በስልክ ቁጥሮች 

                          +251111 58 08 80 ወይም +251111 26 28 22 መደውል ይችላሉ

                                                       ቡና ባንክ

                                                     አዲስ አበባ 

Save Tender