Tender Detail

Tender Details

  • Deadline07 Jun 2023, 11:45 PM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Accounting & Auditing

በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የሞጃ ጉምሩክ ቅርጫፍ ጽ/ቤት አስመጪዎች በጉምሩክ አዋጅ 859/2006 አንቀታአ 51፤ንዕስ አንቀፅ 1እና በተሻሻለው የጉምሩክ አዋዐጅ 1160/2011 አንቀፅ 13 ንዕስ አንቀፅ 1 መሰረት ዕቃቸውን የጉምሩክ ሥነ_ሥርዓት ፈጽመው ባለመውሰዳቸው ተቆጥረው ። ስለሆነም በገቢዎች ሚኒስቴር ጉምሩክ ኮሚሽን የሞጆ ጉምሩክ ቅርጫፍ ጽ/ቤት በጉምሩክ ቁጥጥር ስር ያሉ ንብረቶች ስለሚወገዱበት ስርዓት በአወጣው መመሪያ ቁጥር 167/2012 አንቀጽ 9 መሰረት የተወረሱ ንብረቶች ጥሬ ዕቃ /MAGNESIUM SULPHALE ካርቶን የድርጅት አርማታ የታተመበት /2PLY CORRUGALED/፤PAPER WRAPPERS PRINTED/ ድርጅት አርማታ ያለው የዘመን መቁጠሪያ TABEL CALENDER WHITE AND BLUE/እና የካርቶን ሳጥን የድርጅት አርማታ የታተመበት /CORRUGATED PRINTED PACKING BOX/ በግልጽጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።


በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የሞጃ ጉምሩክ ቅርጫፍ ጽ/ቤት አስመጪዎች በጉምሩክ አዋጅ 859/2006 አንቀታአ 51፤ንዕስ አንቀፅ 1እና በተሻሻለው የጉምሩክ አዋዐጅ 1160/2011 አንቀፅ 13 ንዕስ አንቀፅ 1 መሰረት ዕቃቸውን የጉምሩክ ሥነ_ሥርዓት ፈጽመው ባለመውሰዳቸው ተቆጥረው ። ስለሆነም በገቢዎች ሚኒስቴር ጉምሩክ ኮሚሽን የሞጆ ጉምሩክ ቅርጫፍ ጽ/ቤት በጉምሩክ ቁጥጥር ስር ያሉ ንብረቶች ስለሚወገዱበት ስርዓት በአወጣው መመሪያ ቁጥር 167/2012 አንቀጽ 9 መሰረት የተወረሱ ንብረቶች ጥሬ ዕቃ /MAGNESIUM SULPHALE ካርቶን የድርጅት አርማታ የታተመበት /2PLY CORRUGALED/፤PAPER WRAPPERS PRINTED/ ድርጅት አርማታ ያለው የዘመን መቁጠሪያ TABEL CALENDER  WHITE AND BLUE/እና የካርቶን ሳጥን የድርጅት አርማታ የታተመበት /CORRUGATED PRINTED PACKING BOX/ በግልጽጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል። በዚህ መሰረት ጫረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለመጫረት የሚፈልጉና ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መሳተፍ የሚችሉ መሆኑን እንገልጻለን።

1. ተጫራቾች የዕቃው ዝርዝር ዓይነት ብዛት የጨረታ ሰነድ እና መመሪያ መግለጫ እዲሁም የጨረታ ዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ ዘወትር ከሰኞ እስከ ሐሙስ ከጠዋት 2፡00 እስከ ቀኑ 6፡00 ከሰዓት  በኋላ ከቀኑ 7፡00 እስከ ቀኑ 10፡30 እና ዓርብ ከጠዋት 2፡00 እስከቀኑ 5፡00 ሰዓት በኋላ ከቀኑ 7፡30 ኧስከ 10፡30 እዲሁም ቅዳሜ ከጠዋቱ  2፡00 እስከ 5፡30 የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል ከቅርጫፍ ጽ/ቤቱ ገቢ ሂሳቦች ቡድን መውሰድ ይችላሉ።

2. ተጫራቾች በጨረታ ከሚሸጠው ዕቃ ጋር በዘርፉ የፀና ንግድ ፈቃድ ያላቸው የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር 15% የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ምዝገባ ሰርተፍኬት እና የዘመኑ  ግብር የከፈለ ለመሆኑ ከግብር ሰብሳቢ መ/ቤት የተስጠ ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው። ሆኖም ግምታዊ ዋጋቸው ከብር 500,000.00 በታች የሆኑ ማንኛውንም ዕቃ ለመግዛት  የ15% ተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ ሳያስፈልግ መወዳደር ይችላሉ።

3. ማንኛውም ተጫራች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን የሚጫረትበት ጠቅላላ ዋጋ 5% ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ CPO ጨረታ ከመክፈቱ በፊት በቅድሚያ ማስያዝ ይኖርበታል። ተሸናፊ ተጫራቾች ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ አሸናፊው እደታወቀ በ3 /ሶስት/ የስራ ቀን ውስጥ የሚመለስ ሲሆን አሸናፊው ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ካሸናፊው ዋጋ ላይ የሚታሰብላቸው ይሆናል። ተጫራቾች የሚያሲዙት CPOበቅርጫፍ ጽ/ቤቱ ስም ETHIOPIAN CUSTOMA COMMISSION MODJO BRANCH OFFICE በሚል ሲሆን የግል ባንክ ከሆነ አዲስ አበባ አስተዳደር ቅርጫፎች በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከሆነ ደግሞ ከአዲስ አበባ አዳማና ሞጆ ቅርጫፍ መዘጋጀት አለበት ተሳታፊዎች ዋጋ  መሙላት የሚችሉት በቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ተዘጋጅተው ማህተም ያረፈበት ሠነድ ላይ ብቻ መሆን ይኖርበታል።

4. ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ በመግዛት የሚወዳደሩበትን ዕቃ አስቀድሞ ማየት ያለባቸው ሲሆን ዕቃውን ሳያዩ ለሚሞሉት ዋጋ ቅ/ጽ/ቤቱ ኃላፊነቱ  አይወስድም።

5. የግልፅ ጨረታ ተሳታፊ ተጨራቾች እያንዳዱን ዕቃዎች ለመግዛት የሚያቀርቡት  የመጫረቻ ዋጋ የሞሉበት  ሠነድ በተራ ቁጥር  2 የተገለፁትን ማስረጃዎች ኮፒ እና ያቀረቡት የመጫረቻ ዋጋ 5% ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ባንክ በተረጋገጠ CPO በኤንቨሎፕ ወይም በፖስታ በማሸግ የጨረታ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ከወጣ በቅ ቀን ጀምሮ ለ8 ተከታታይ ቀናት ጠዋት 4፡45 ድርረስ በቅርጫፍ ጽ/ቤቱ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይችላል።

6. የጨረታ ሳጥን ከታሸገ በኋላ የሚመጡ የመጫረቻ ሰነዶች ተቀባይነት አይኖራቸውም።

7.የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ የወጣ ቀን ጨምሮ በ8ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡45 ታሽጎ በዚሁ ዕለት ጠዋቱ 5፡00 ላይ ተጫራቾቹ ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቅርጫፍ ጽ/ቤት ለጨረታ ባዘጋጀው ቢሮውስጥ ይከፈታል።

8. ማንኛውም በግልጽ ጨረታ  የሚሳተፈው ተጫራች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ዋጋ መቀይር ቀይንም የተጫራቾች ዋጋ ተተርሶ ዋጋ አሻሽሎ ማቅረብ አይቻልም።

9. ህጋዊ ባልሆነ መንገድ ጨረታውን ለማሸነፍ ሲል መደለያ የሰጠ ወይም ለመስጠት የሞከረ ማንኛአውም ተጫራች ከጨረታ ይወገዳል። ጨረታው ከተካሄደ በኋላም ቢሆን ጨረታው አሸናፊው  ጨረታውን  ያሸነፈው በህግ  ወጥ  መንገድ መሆኑ ከተረጋገጠ የጨረታ  ውጤት ይሰረዛል።

10. ማንኛውም የጨረታ ሽያጭ የዕቃ አስመጪ ወይም ባለቤት እና ቤተሰብ የነበሩ ሰዎች በጫረታው መሳተፍ አይችሉም።

11.ማንኛውም ትየጫራች  ጨረታው ከተከፈተ በሁስላ  እራሱን ከጨረታው ከተከፈተ በኋላ እራሱን ከጨረታ ውድድር ማግለል አይችለም።

12  ማንኛውም ተጫራች የሰጠው የመወዳደሪያ ዋጋ የጨረታ ግምገማ ተጠናቆ ቅርጫፍ ጽ/ቤቱ የጨረታውን ውጤት እስከሚያሳውቅ ድረስ ፀንቶ ይቆያል።

13. የግልፅ ጨረታው አሸናፊ ጨረታው ስለማሸነፋቸው ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በ5 ቀናት ውስጥ የአሸነፉበት ዕቃ ዋጋ ገቢ በማድረግ ዕቃውን መረከብ አለበጥ በ5 ቀናት ውስጥ ገንዘቡን ገቢ ካልተደረገ ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ CPO ያስያዙት ገንዘብ ለምንግስት ገቢ ይደረጋል። ያሸነፉት ዕቃ በድጋሚ ለጨረታ ሽያጭ ይቀርባል።

14. በተራ ቁጥር 12 በተቀመጠው ጊዜውስጥ ያሸነፉበት ዕቃ ዋጋ ገቢ እድርጎ ዕቃውን ያነሳል /ያልተረከበ እንደሆነ ለሚቆይበት ለተጨማሪ ጊዜ የመጋዘን ኪራይ ይከፍላል ሆኖም ዕቃው በ2 ወራት ውስጥ ካልወጣ አደተተወ ተቆጥሮ በጨረታ ሽያጭ ይወዳደራል።

15. አሸናፊው ተጫራች ዕቃዎችን ለመረከብ ለማጓጓዝ የሚያስፈል ወጪዎችን ሁሉ እራሱ ይሸፍናል።

16 ቅርጫፍ ጽ/ቤት ለጨረታ የቀረበውን ዕቃ ብዛት ለመጨመርም ሆነ ለመቀነስ ሙሉ መብት አለው።

17. ቅርጫፍ ጽ/ቤቱ ዕቃዎቹን ለመሸጥ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ወይም ዘዴ ከአገኘ ጨረታው በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

18. ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 022-236-90-94ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።

Save Tender