የአማራ ክልል ኤሌክትሪክ አገልግሎት ለስልጠና ለስብሰባ አገልግሎት የሚውል መሰብሰቢያ አዳራሽ የምግብ ሻይ ቡና እና መጠጥ አገልግሎት ግዥ ባለ 3 ኮከብ /ሎት 1/ እና ባለ 4 /ወይም 5/ ኮከብ ያላቸው ሆቴሎች /ሎት2/ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለአንድ አመት አገልግሎት ማግኘት ይፈልጋል።
1. በዘርፉ ህጋዊ ፈቃድ ያላቸው የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆናቸውን የሚገልፅ ማስረጃ የሚያቀርቡ እና ተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ።
2. የጨረታ ሰነዱ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በአማራ ክልል ኤለኢክትሪክ አገል ግሎት ዋና መ/ቤት ኖክ ፊት ለፊት ከሚገኘው የክልሉ ቢሮ 2ኛ ፎቅ ቢሮቁጥር 15 ድረስ በመቅረብ በነጻ መውውሰድ ይችላሉ።
3. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን ብር 5,000.00 /አስት ሺህ ብር/ በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ ዋስትና ወይም በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ማስያዝ አለባቸው።
4. ጨረታው ሰኔ 09ቀን 2015 ዓ.ም 8፤00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን 8፡30 ሰዓት ይከፈታል።
5. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸው በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ጨረታ ቁጥር EELIAEU/NCB /032/2015 ሎት 1 ወይም ሎት 2 የሚል ምልክት በማድረግ እስከ ሰኔ 09ቀን2015 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
6. ሪጅኑ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
7. ተጫራቾች መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር ፡ 0582207469/0583201957 መጠየቅ ይችላሉ።
