Tender Detail

Tender Details

  • Deadline26 Jun 2023, 4:32 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Accounting & Auditing

የሚኒስቴር መዝገብ ቤቱ ግብር ከፋዮች የሚጠቨቅባቸውን የታክስ እዳ በታክስ ህጉ በተፈቀደው የጊዜ ገደብ ባለመክፈላቸው ምክኛት በታክስ አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 983/2008 አንቀእጽ 41 በተሰጠው ስልጣን መሰረት የግሪን ላንድ ሃ/የእ/የግ/ማህበር ኤመርሊድ ሪዞርት ንብረት የሆነ በጋሞ ዞን አርባምንጭ ከተማ በ 30,000 ካ/ሜ ላይ የተገነቡ በርካታ የመኝታ ክፍሎች ሬስቶራንትስ መዋኛ ኩሬዎች የህጻናት መጫዎቻዎች የመሰብሰቢያ አዳራሾች የአስተዳደር ቢሮ እና ሌሎች ለሪዞርቱ አስፈላጊ የሆኑ ዕቃዎች የተሟሉበት ለበርካታ ሀገር ውስጥ እና የውጪ ሀገር ዜጎች ምቹ በመዝናኛ ያገለገል እና በቀጣይ የሚያገለግል የሪዞርት ንብረት የሆነ ግምታዎ ዋጋቸው ተጨማሪ እሴት ታክስን ጨምሮ ብር 656፣341,287.14 የሆኑ እና 1 የጭነት ተሽከርካሪ በታክስ እዳ ምክኒያት ድርጅቱ እየተሰራ በነበረበት በታህሳስ ወር 2015 ዓ/ም የተያዙ ንብረቶች ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

1.በተጨማሪ ለመሳተፍ የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች በማንኛውም የስራ ዘርፍ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆነ እና የታደሰንግድ ፈቃድ ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዞ በኤንቨሎፕ በታሸገ ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

2. ተጫራቾች የጨረታው ሰነድ ዘውትር በስራ ሰዓት ከሰኞ አስከ አርብ እና ቅዳሜ ጠዋት 2፡30_ 6፡30 ሰዓት ህንጻ "መ" 3ተኛ ፎቅ 310 ከግዥ እና ፋይናስ አስተዳደር ዳይሬክቶሬት የማይመለስ ብር 100.00 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል የጨረታ ሰነዶች ህንፃ "ሀ" 2ተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 210 ከታክስእዳ አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ መውሰድ ይችላሉ።

3. በግልጽ ጨረታ ለመሳተፍ ተጫራቾች የሰጡትን ዋጋ 1/10 ኛውን ብቻ ለጨረታ ዋስትና /CPO/ በገቢዎች ሚኒስቴር ስም/Minsistry or Revenue/ በባንክ አሰርተው ማስያዝ ይኖርባቸዋል።

4. ተጫራቾች በሚከተለው የጨረታ ቀናት /ስኬጁል/ መሰረት መጫረት ይችላሉ።

ተ.ቁ የመ/ቤቱ የጨረታው ዓይነት የተሽከርካሪው መመልከቻ ቀን የጨረታ መዝጊያና መክፈቻ ቀን
1 ገቢዎች ሚኒስቴር 30,000 ካ/ሜ የኤመራልድ ሪዞርት ድርጅት ንብረት እና ሙሉይዞታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ 30 ቀናት ማስታወቂያው በጋዜጣ ወቶ 30ቀን ከተጠናቀቀ በኋላ ቀጥሎባለው 31ኛ ቀ 3፤45 ተዘግቶ በዚያኑ ቀን በ4፡00ሰዓት ይከፈታ

5 የጨረታ መክፈቻ ቦታ በሚኒስቴሩ መ/ቤቱ የስብሰባ አዳራሽ ወይም በዕለቱ በሚዘጋጀው ቦታ ተጫራቾች ህጋዊወኪሎቻቸው ባሉበት/ወይም በታዛቢዎች ፊት ይከፈታል።

6. የግልጽ ጨረታ መክፈቻ መዝጊያ 31ኛው ቀን የመ/ቤቱ የስራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ ቀን የግልጽ ጨረታ መዝጊያ ቀን ይሆናል።

7. ለጨረታ አሸናፊ ተጫራቾች ለጨረታ ዋስትና ያስያዙት /CPO/ከሚከፍሉት ዋጋ ጋር እደአስፈላጊነቱ የሚታሰብላቸው ሲሆን ለተሸናፊው ተጫራቾች ደግሞ በ5 የስራ ቀናት ውስትጥ ተመለሻ ይደረግላቸዋል።

8. አሸናፊ ተጫራቾች አሸናፊነታቸውን በደብዳቤ ከተገለፀላቸው ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ጠቅላላ ዋጋ መ/ቤቱ በሚሰጠው አድራሻ ገቢ በማድረግ ያሸነፉበትን ንብረት/ሀብት መረከብ ይኖርባቸዋል።

9.ከላይ በተራ በተ/ቁ 9 በተገለጹት ቀናት ውስጥ ክፍያው ገቢ ያላደረገ እና ንብረቱ ተረክቦ ያሎሰዱ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት ገንዘብ ለሚኒስቴር መ/ቤቱ ገቢሆነው ንብረቶቹ በድጋሚ እዳልተሸጥዕ ተቆጥሮ ለሽያጭ ይቀርባል።

10. ሚኒስቴሩ መ/ቢቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

Save Tender