Tender Detail

Tender Details

  • Deadline24 Jun 2023, 2:03 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Accounting & Auditing

በቤ/ጉ/ክ/መንግስት የግብር ቢሮ ስራ የሚገኘው የስደተኞች ተፅኖ ምላሽ ፕሮጀክት የክልል ማስትባበያ ፕሮጀክት በስሩ በሚገኙት አምስት ወረዳዎች እና ሁለት ከተማ አስተዳደሮች ስርለሚገኘው ቀበሌዎች ተቋማትና ማህበረሰብ አገልግሎት የሚውል አማራጭ የሃይል ምንጭ ባለ20ዋት የቤተሰብ ሶላር ብዛት 540 ግዥ በ2015 በጀት ዓመ ግዥ ለአምከናወን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል። ስለዚህ የሚከተሉት መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑ ይጋብዛል።


1. በዘርፉ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN /የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ የምስክር ወረቀት የዘመኑ ግብር የከፈሉ እና ግብር የመክፈል ግዴታቸውን የተወጡ መሆኑኘሚያረጋግጥ በግብር ሰብሳቢ ባለስልጣን የተሰጠ ማስረጃ።

2. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተጠቀሱትና የሚመለከታቸው ማስረጃዎች ዋናና ቅጂ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።

3. የሚገዙ የዕቃዎች ዓይነት ዝርዝርዝ መግለጫ /ስፔሲፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ።

4. የመልካም ስራ አፈጻፅም የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው።

5. በጨረታ ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱ የማይመለስ ብር 200.00/ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ30 ተከታታይ ቀናት በአየር ላይ የሚቆይ በ31ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓትለስደተኞች ምላሽ የልማት ፕሮጀክት ክልል ማስተባበሪያ ዩኒት ግቢ ውስጥ ተዘግቶ በዚሁ ሰዓት በ4፡30 በዚሁ ማስተባበያ ዩኒት ይከፈታል።

6. የመክፈቻ ዕለት /31ኛው ቀን/ ቅዳሜና እሁድ ላይ የሚውል ከሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን በ4፡00 ላይ የሚከፈት ይሆናል።

7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ቢያንስ ለ90 ቀን የሚቆኦይ /ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩበት ብር 121,500,000 /አንድ መቶ ሃያ አንድ ሺህ አምስት መቶ ብር ብቻ/ በባንክ በተረጋገጠ ክፍያ ተዛዝ /ሲፒኦ/ ማስያዝ አለባቸው።

8.  ማንኛአውም ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱ በተናጠል ወይም አንድ ወጥ በሁለት ፖስታዎች ቅጂዎች ማለትም ዋናና ቅጂ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ አንድ ዋናና ሁለት ቅጂ ለቤንሻንጉል ጉምዝ ክልላዊ መንግስት የስደተኞች ተፅኖ ምላሽ የልማት ፕሮጀክት ክልል ማስተባበሪያ ዩኒየን ግዥ ስራ ክፍል ማስገባት ይኖርባቸዋል።

9.የዘገየ ጨረታ ተቀባይነት የለውም።

10. ጨረታው ተጨማሪ ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የስደትኞች ተፅኖ ምላሽየልማት ፕሮጀክት ክልል ማስተባበሪያ ዩኒየን ግዥ ክፍል ይከፈታል።

11. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታው በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መቱ የተጠበቀ ነው።

12 ይጨረታ ሰነዱን በስሙ አስመዝግቦ ያልገዛ ማንኛውም ተወዳዳሪ በጨረታው መሳተፍ አይችልም።

13. የተጫራቾች የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ለ60 /ስልሳ/ ቅናት ፀኖ የሚቆይ መሆን አለበት።

14 በጨርታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ የስደተኞች ተፅኖ ምላሽ የልማት ፕሮጀክት ክልል ማስተባበሪያ ዩኒየን ግዥ ስራ ክፍል በአካል መገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 0572756289 በመደወል ማግኘት ይችላሉ።

Save Tender