የኢትዮጵያ መድ ድርጅት የተለያዩ ዓይነት የወረቀት ህትመት እና ብሮሸሮችን በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
1.በጨረታ የሚወዳደሩ ተጫራቾች በዘርፉሕጋዊየታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና በመንግስት ግዥ ንብረት አስተዳድር ኤጀምሲ የአእቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ ለመመዝገባቸው ከድረገጹ /Wabsite/ አትመው ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማያያዝ ይኖርባቸዋል።
2. ተቻራቾች ተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ከፋይነት የተመዘገቡ እና የግብር መለያ ሰርተፍኬት ያላቸው መሆኑን የሚያረጋገጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው።
3. ተቻራቾች የማይመለስ ብር 300.00/ ሶስት መቶ ብር ብቻ/ በመክፈል የጨረታ ሰነዱ ይህ ማስታወቂያ በጨረታ ከወጣእት ቀን ጀምሮ ለገሃር በሚገኘው የድርጅቱ ዋና መስሪያ ቤት 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 108 ድረስ በመቅረብ መግዛት ይችላሉ።
4. ተቻራቾች ብር 100,000.000 /አንድ መቶ ሺ ብር/ የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ ክፍይ አማዘዣ /CPO/ ወይም ለዘጠናቀን የሚቆይ ቅድመ ሁኔታ ያላስቀመጠ የባንክ ዋስትና ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
5. ተቻራቾች መወዳደሪያ ሰነዳቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ለገሀር በሚገኘው የድርጅቱ ዋና መስሪያ ቤት 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 108 በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ሰኔ 07 ቀን 2015 ዓ.ም እስከ ቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል። ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዕለቱ ማለትም ረቡዕ ሰኔ 07 ቀን 2015 ዓ.ም በፋስሊስት ማኔጅመንት የስብሰባ አዳራሽ በ8፡30 ይከፈታል።
6. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታው በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
7. ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁትር 011 _ 5512400 የውስጥ መስመር 217/262 ወይም በቀጥታ 011 ፟ 5504931 መጠየቅ ይችላሉ።
