በአብከም ሰ/ሸዋ ዞን የመንግ ጌራ ምድር ወረዳ እንሣት ሀብት ልማት ጽ/ቤት ለእንሣት ጤና አገልግሎት የሚውል የተለያዩ የእንስሳት መድሀኒቶች እና የህክምና መሳሪያዎቭ ለመግዛት ተጫራቾች አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል። በመሆኑ በጨረታው ላይ የሚሳተፉ በዘርፉ ህጋዊ ፈቃድ ያላቸው ተወዳዳሪዎች የሚከተሉትን ቅድመ ሁኔታዎች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል።
1.በዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ የብቃት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት የስራግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን ነምበር/ የቫት ተመዝጋቢ ከሆኑ የተጨማሪ እሴት ታክስ መረጃዎች አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
2. ተጫራቾች የቫት ተመዝጋቢ ከሆኑ ከቫቱ መሙላት አለባቸው።
3. ታጫራቾች የሞሉበትን ጠቅላላ ዋጋ በማስላት ቫት ጨምሮ የጨረታ ማስከበሪያ 2% ማስያዝ ይኖርባቸዋልያስያዙት ደረሰኝ ወይም CPO ዋናውን ማቅረብ አለባቸው።
4. የእያንዳዱን መድሃኒት ነጠላ ጠቅላላ ዋጋበትክክል መሙላዎን ያረጋግጡ።
5. የዘርፉ ንግድ ፈቃድ የመሳሰሉ መረጃዎች ከኦርጅናል ዶክሜንት ጋር የተያያዙ በፖስታ ታሽገው መቅረብ አለባቸው።
6. በፖስታ በውጪ ገጽ እና በዋጋ መሙያ የጨረታ ሰነድ ላይ ተጫራቾች ስማ ፊርማ ማህተም ሊኖር ይገባል።
7. በሌሎች ተጫራቾች ዋጋ ላይተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም።
8. በሚያቀርቡት የጨረታ ዋጋ ላይ የጨረታ መዝጊይዝ ከተጠናቀቀ በኋላ ማሻሻያ ማድረግ ያሻቸውን ከጨረታ ማግለል አይችሉም።
9. የጨረታ ሰነዱ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በመንዝ ጌራ ምድር ወረዳ እንስሳት ሀብት ተተሪ ፅ/ቤት ድረስ በመምጣት የማይመለስ ብር 100.00 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል መግዛት ይችላሉ።
10. ጨረታው በአየር ላይ የሚቆይበት ጊዜ ከ15/09/2015 እስከ 30/09/2015 ዓ.ም ለ15ተከታታይ ቀናት ሲሆን በ16ተኛው ቀን የጨረታ ሳጥኑ ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ ወዲያውንኑ 4፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በፅ/ቤታችን ይከፈታል።
11.ጨረታው የሚከፈትበት ቀን የህዝብ በዓል ወይም ቅዳሜና እሁድ ላይ ከዋለ በቀጣዩ የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል።
12. አሸናፊው የሚለየው በተናጠል ወይም በጥቅል መ/ቤቱ በሚያወጣው መሰረት ነው።
13. ተጫራቾች አሸናፊነታቸው በተገለፀላቸ በ5 ተከታታይ የስራ ቀናት በኋላ ባሉት 5 ተከታታይ ቀናት ውስጥ በፅፈት ቤታችን በመገኘት የውል ማስከበሪያ ያሸነፉበትን ተቅላላ ዋጋ 10% በማስያዝ ውል መፈፀም አለባቸው በተሰጠው የጊዜ ገደብ ውስጥ ቀርበውል ካልፈፀሙ በግዢ መምሪያ መሰረት የጨረታ ማስከበኢያውን ውርስ በማድረግ ለመንግስት ገቢ ይደረጋል።
14. ተጫራቾች በጨረታ አፈፃፀም ሂደት ላይ ቅሬታ ካላቸው በግዥ አዋጁ መሰረት በተከታታይ በ5 የስራ ቀን ውስጥ ቅሬታቸውን ማቅረብ ይችላሉ።
15. ለተሸናፊ ተጫአራች ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት ብር ከአሸናፊ ተጫራች ጋር ውል እደተፈፀመ ተመላሽ ይደረጋል።
16. አሸናፊው ላቀረባቸው መድሀኒቶች እና የህክምና መሳሪያ ዋጋየሚከፈለው በውል መሰረት መድሀኒቶችን እና የህክምና መሳሪያዎቸን ከፅ/ቤታችን መድሀኒት ቤት ድረስ በራሱ ወጪ አጓጉዞ አጠናቆ ገቢ ማድረጉ ሲረጋገጥ ነው።
17. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታው ሙሉ በሙሉ ውይም በከፊም ሆነ ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
18. ተጨማሪ ማብራሪያ ሲፈልጉ በስልክ ቁጥር 0116850139/0601/0052 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
ማሳሰቢያ፦ የእያንዳዱ ማድሃኒትና እቃ ጠቅላላ ዋጋ በትክክል መሙላትዋን ያረጋግጡ።
