መ/ቤታችን የቢሮ አገልግሎት ግዥ ለሁለት አመት ማዕቀፍ የውል ስምምነት ከመንግስት በተፈቀደ በጀት በብሄራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
| የሚገዛው የአእገልግሎት አይነት | |
| የቢሮ አገልግሎት ግዥ ለሁለት አመት በማቀፍ የውል ስምምነት ለመግዛት የወጣ ጨረታ |
በመሆኑም ተጫራቾች
1.የጨረታ ሰነዱን ከላይ በተጠቀሰው የኢትዮጵያ እስታቲክስ አገልግሎት ደብረብርህን ቅ/ጽ/ቤት በመምጣት የማይመለስ ብር 100.00/ብር አንድ ምቶ/ ከፍለው መውሰድ ይችላሉ።
2. የይዞታ ማረጋገጫ ፈቃድ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር /TIN NO/ ከግብር እዳ ነጻ ስለመሆናቸው ከግብር ሰብሳቢ መ/ቤት የድጋፍ ደብዳቤ የተ.እ.ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት እዲሁም የማጭበርበር ድርጊት ላለመፈጸም ቃል የሚገባበትን ቅጽ በመሙላት ፊርማና ማህተም በማድረግ ከመጫረቻ ሰነድ ጋር ማቅረብ አለባቸው።
3. ለጨረታ ማስከበሪያ /Bid Bond/በባንክ የክፍያማዘዣ /CPO/ወይም የባንክ ዋስትና ብር 5,000.00/አምስት ሺ ብር/ የኢትዮጵያ እስታቲክስ አገልግሎት ደብረ ብርሀን ቅ/ፅ/ቤት ትክክለኛ አድራሻ ከጨረታ ሰነዱ ላይ በማየት የጨረታ ማስከበሪያ ከጨረታ መዝጊያ ስዓት አስቀድሞ ከመቻረቻ ሰነዳቸውጋር አያይዘው ማቅረብ ያለባቸው ሲሆን ከመጫረቻ ሰነድ ጋር ተያይዞ ያልቀረበ ወይም ከጨረታ መዝጊያ ሰዓት አስቀድሞ ያልቀረበ የጨረታ ማስከበሪያ ተቀባይነት የለውም።
4 ተጫራቾች የሚጫረቱበት የቢሮ አገልግሎት በሚሸጠው የጨረታ ሰነድ ክፍል 6ላይ ከተመለከተው የቴክኒክ ፍላጎት ጋር መጣጣም ይኖርበታል።
5. የሚወዳደሩበትን ሰነድ አንድ ኦርጅናል አንድ ኮፒ ለየብቻ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ለመጀመሪያ ጊዜ ታትሞ ከወታበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠረው 16ኛው ቀን 8፡00 ሰዓት ድረስ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ ጨረታው በዚሁ ቀን 8፡00ስዓት ተዘግቶ በዚሁ እለት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ተጫራቾች በሚወዳደሩበት በኢትዪጵያ እስታቲክስ አገልግሎት ደብረ ብርሀን ቅ/ፅ/ቤት በዚህ ሰዓት ይከፈታል። ሆኖምይህ ቀን ቅዳሜ እና እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከዋለ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተሰጠው ሰዓት የጨረታ መዝጊያ ይሆናል።
6።መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
