በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ በስሩ ላሉ ተሽከርካሪዎች እና ሞተር ሳይክሎች የጠገና እና ሰርቪስ አገልግሎት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
- ሎት አንድ-የተሽከርካሪ ጥገናና ሰርቪስ /ቢሮው ያሉት የተለያዩ ሞዴል ያላቸው መኪናዎች/ ቲዮታ፣ኒሳን፣ማዝዳ፣ጄሊ፣ ሊፋን፣ቢሾፍቱ፣ፋዎ እና ሊንግፉን/እና ለማስጠገን እና የሰርቪስ ጊዜያቸው ሲደርስ ሰርቪስ ለማረግ።
- ሎት ሁለትብ- የሞተር ሳይክል ጥገናና ሰርቪስ /ቢሮው ያሉት የተለያየ ሞዴል ያላቸው ሞተር ሳይክሎች/ ለማስተገን እና የሰርቪስ ጊዜያቸው ሲደርስ ሰርቪስ ለማድረግ እዲቻል ይፈለጋል
1. ተቻራቾች በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፈቃድ /የሙያ ፈቃድ/ያላቸውና የዘመኑ ግብር የከፈሉ መሆን አለባቸው።
2. ተጫራቾች የሚያቀርቡበትን የቴክኒክ ኦሮፖዛል 'አንድ ኦርጅናል ኮፒ'የድርጅቱ ስም አድራሻና ማህተም እዲሁም የሚጫረቱበትን የአረታ አይነት ሎት በመጻፍ በታሸገ ኢኣንቨሎፕ በማቅረብ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 10ቀን ከቀኑ 11:30ድረስ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥማስገባት ይኖርባቸዋል። ጨረታው በዚሁ እለት ከቀኑ 11፡30 ታሽጎ ባስራአደኛው ቀን /በሚቀጥለው የስራ ቀን/ ከቀኑ 4:00 ሰዓት በግዥና ፋይናስ ዳይሬክቶሬተር ቢሮ ቁጥር 202 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል ።የጨረታው መክፈቻቀን እሁድ ወይም የበአል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይሆናል።
3.ተቻራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስታና ብር 10,000.00/ አስር ሺ ብር/ በባንክ በተመሰረተ ቼክ C.P.O ከጨረታ ሰነዱጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
4.ተቻራቾች በአማርኛ ቋንቋ በተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ማሰታወቂያ በወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ቅዳሜ 6:00 ሰዓት ጨምሮ በስራ ሰኣአት የማይመለስ ብር 100.00/አንድ መቶ ብር/ በመክፈል ከገነት ሆቴል ገባ ብሎ አፍሪካ ህብረት ፊት ለፊት አማራ ህንጻላይ በሚገኘው የአዲስ አበባ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ 2ተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 203 ግዥ አገልግሎት ቡድን በአካል በመቅረብ የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።
5.ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ተ.እ.ታ/ቫት/ ጨምሮ ወይም ተ.እ.ታ/ቫት/በፊት መሆኑ መግለጽይጠበቅባቸዋል።ያልተገልጹ ከሆነ ተ.እ.ታ/ቫት/ጨምሮ እደሆነ ይወሰዳል።
6.ተጫራቾች የጨረታው አሸናፊነቱ ከተገለጸባቸው በሃላ የውል ማስከበሪያ ባሸነፉበት ሎት ከጠቅላላዋጋ 10% በማስያዝ ውልመዋዋል ይጠበቅባቸዋል።
7.ተቻራቾች በመጫረቻ ሰነዱ የተገለጸው የመጨረሻ ሰነድ ማቅረቢያ የመጨረሻ ጊዜ ካለፈ በሃላ ወይም በጨረታ ሰነዱ በጨረታ ሰነዱ ጸንቶ የሚቆይበት ጊዜ ውስጥ እራሱ ከጨረታው ካገለገለ እና የጨረታው አሸናፊነቱ ከተገለጸ በሃላ በተገለጸላቸው ቀን ቀርበው ውለታ ካልፈጸሙና የውል የውል የማስከበሪያ ካላስያዙ ያስይሳዙት የጨረታ ማስከበሪያለመንግስት ገቢ ይሆናል።
8. አሸናፊ ተጫራቾች ጥገናና ስርቪስ አጠናቆ የሚጨርስበት ጊዜ እደተሽከርካሪው አይነት እና በሚፈልገው ጥገናና ሸርቪስ አይነት በጊዜ ገደብ ወስኖ ማስቀመጥ ይኖርበታል።
9.ለጨረታው ከቀረቡት አገልግሎት ዝርዝር ዉስጥ ቢሮ እስከ 20% /ሃያ ፐርሰንት/ ጨምሮ ወይም ቀንሶ የመግዛት መብቱ የተጠበቀነው።
10.መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ጨረታው ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊልም ሆነ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
