Tender Detail

Tender Details

  • Deadline24 May 2023, 12:13 PM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Cleaning And Janitorial Equipment

የወራቤ ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የ2015 በጀት ዓመት የሚያገለግሉ የጽዳት ዕቃዎች ለመግዛት ይፈልጋል


የጨረታ ማስታወቂያ

የወራቤ ኮምፕሬንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የ2015 በጀት ዓመት የሚያገለግሉ የጽዳት ዕቃዎች ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ስለዕቃዎች የሚገልፅ ሰነድ (ዶክመንት) በወራቤ ኮምርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ቢሮ ቁጥር 302 በመቅረብ የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ዘወትር በስራ ሰዓት በመምጣት የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡ 

  1. ተጫራቾች ተፈላጊ ዕቃዎችን ማቅረብ የሚያስችላቸውን የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸው ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ተመዝጋቢና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (Tin Number) ያላቸውና ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው፡፡
  2.  የዚህ ጨረታ ተካፋዮች በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚ/ር በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡና የምስክር ወረቀት ያላቸውና ኮፒውን ማቅረብ አለባቸው፡፡
  3. ተጫራቾች ከሚያቀርቡት ዋጋ 10,000 በባንክ በተመሰከረ C.P.O /ሲፒኦ/ የጨረታ ዋስትና ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ አለባቸው፡፡
  4. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በጨረታ ሰነድ ላይ በመሙላት በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15 (በአስራ አምስት) ተከታታይ ቀናት ውስጥ ዘወትር በስራ ሰዓት 2፡30 - 6፡30 ሰዓት ከሰዓት ከ7፡30-11፡30 ሰዓት ከላይ በተጠቀሰው አድራሻ በግዥ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ክፍል ለዚህ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡
  5. ጨረታው በ15ኛው ቀን በ08፡00 ተዘግቶ በ15ኛው ቀን ከሰዓት በኋላ 8፡30 ተጫራቾች ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው ይከፈታል፡፡ የመክፈቻውም ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም በህዝባዊ በዓላት ላይ ከዋለ በሚቀጥለው ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
  6. ሆስፒታሉ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 046 329 9263 ደውሉ መጠየቅ ይችላሉ፡፡

የወራቤ ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል

Save Tender